ከዘረኛው ሰርዓት የሚጠቀሙ ኢህአዴግ ምን ያድርግህ? ሲሉ እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር ወንጀል ነው! – በቶማስ ሰብሰቤ

በኢህአዴግ ደጋፊነት የተቀመጡ ፣ የኢህአዴግ ጉርሻን የለመዱና በፖለቲካ ፖሮፓጋንዳ ኢኮኖሚና መሰል የኢህአዴግ ወሬ የደነዘዙ ሰዎች ብዙ ጊዜ “ኢህአዴግ ምን ያድርግህ” ብለው ያደነዝዙሃል።ዛሬ ከሶስት አመት እስር በኋላ የተፈታው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የመለስ አምልኮ” በሚል  መፅሃፍ ላይ ካነሳቸው አንዱ ጉዳይ ይህ ርዕስ ይገኝበታል።በተደጋጋሚው ጋዜጠኛው በሚሰጠው በሳል ትችት የተማረሩና ኢህአዴግ አይነካብን ባዮች ኢህአዴግ ምን ያድርግር?  እያሉ ያዝጉት እንደነበር አልደበቀም።
ጋዜጠኛ ተመስገን ዳሳለኝ ለስራ ወደ ኬንያ ባመራበት ወቅት አዲስ አበባ ላይ ኢህአዴግ ያወራለትና ናይሮቢ ያያው ሀቅ መለያዮትን በተናገረበት በዚህ ርዕስ ላይ ኢህአዴግ በፕሮፓጋንዳ የፖለቲካ ስልት ብቻ እራሱን የሚያጀግን መንግስት መሆኑን አሳይቶናል።11 በመቶ ፈጣን ኢኮኖሚ የሚለውን ዘፈን የሰማ ደጋፊው …… …ኢህአዴግ ምን ያድርግህ ይልሃል? ከኢህአዴግ ጋር የጋራ የብሄር ፣የሀብትና የስልጣን ክፍፍል ወይም ትስስር ያለው…… ኢህአዴግ ምን ያድርግህ ይልሃል? መልሱ አንድ ነው !ስለ ኢህአዴግ የማወራው ኢትዮጵያን እየመራ ሰለሆነ ብቻ ነው!
ስለ ኢህአዴግ የትኛው ትችት ሳቀርብ ኢትዮጵያን እየመራ ሰለሆነ ነው እንጂ ከስልጣን ቢወርድ የምተችበትና ያገባኛል የምልበት ምክንያት የለኝም የሚለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ማንም ሰው ኢህአዴግን የሚሰራው ጭቆናና ኢ_ፍትሃዊነት የሚቃወመው ሀገሩን ሰለሚወድ ነው ይላል።ማንም ሀገሩን የሚወድ ከሆነ የትኛውን በደል መቃወም አለበት።ጭቆናን ለመቃወም መጨቆን የለብህም።አርጄንቲናዊው ቼኩሼራ ኩባን ነፃ ለማውጣት የታገለው ጭቆና ደርሶበት አይደለም ፤ ወደ ቦሊቪያ ሄዶ ለቦሊቪያ ነፃነት ህይወቱን ያጠው የዚች ሀገር ሰው ሆኖ አይደለም።ቼ አርጄንቲናዊ ሆኖ ለጎረቤት ሀገራት ታግሎ ህይወቱን የሰጠው “ጭቆናን በማንም ላይ ማየት ሰለማይፈልግ ነው”።
ስለዚህ በኢህአዴግ የተዘረጋው የብሄር ፖለቲካ ፣ፀረ_ኢትዮጵያዊነትና ኢ ፍትሃዊነት ለመታጋል ወይም እምቢ ለማለት በሌሎች ኢትዮጵያኖችና በሀገር ላይ በሚፈጥረው የህልውና ጥያቄ ላይ መሰረት ያደረግ ነው።ኢህአዴግ ለመቃወም ሆነ ለመደገፍ ባለፊት 26 አመታት የሰራውና ወደ ፊት ሊሰራው ስላሰበው ነገር ተመልክተህ መሆን አለበት።ይህ ሳይሆን ግን በዝምድና ፣በዘር ፣በጥቅም ፣በፍርሃት ፣በምናገባኝነት ውስጥ ሆን ኢህአዴግ ምን አደረገ ማለት እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር ወንጀል ነው።
በስመ ፌደራሊዝም የመከፋፈልና የክልል ፍቅር እየሰራው …ኢህአዴግ ምን አደረግህ?  ዜጎች ስለተቃወሙ ብቻ ንፁሃን እየገደለ… ኢህአዴግ ምን አደረገህ? ሀሳብን በነፃነት እየገደበ… ኢህአዴግ ምን አደረገህ? ኢ_ፍትሃዊነትና እኩልነት እያጠፋ… ኢህአዴግ ምን አደረገ? የሀገሪቱን የቀጣይ አንድነት ህልውና እያጠፋ…ኢህአዴግ ምን አደረገህ ወደጄ? …… …የምትል ኢህአዴግ መስተፋቅር አሰርቶብሃል አልያም በጤናህ አይደለም።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ዋጋ እየከፈለ ያለህ ህዝብ ፣ተቃዋሚ ፓርቲዎች ፣የሰበዓዊ መብት ተሟጋቾች ፣ጋዜጠኞች ፣ደራሲናን ፣ጦማሪዎች ፣አክቲቪትሶችና ሌሎች አካላት ለሀገር የሚታገሉት በኢትዮጵያ ፍትህ ፣ነፃነት ፣እኩልነት ፣ሀሳብን በነፃነት ለመግለፅና አንድና አንድ የሆነች ሀገራቸው ለመጠበቅ ነው ።ይህ በሆነበት ሀቅ ኢህአዴግ ምን ያድርግ የምትል በመንገድ፣በህንፃና ቁሳዊ መጠነኛ ልማት ዓይንህ አሳውረህ ኢትዮጵያ እየፈራረሰች ዝም ያልክ በሀገር ክህደት ወንጅል የሚያስጠይቅ ሰራ ነው።
ከኢትዮጵያ የሚበልጣ ልማት ሆነ እድገት የለም።መጀመሪያ ሀገርን ማስቀደም ነው፤ ከዛን የጠነባ ሰርዓትን በመቀያየር ልማት ይመጣ።ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም ሆነ ሌሎችን በእስር ፣በእንግልት ፣በጭቆና እየተሰቃዮ ዋጋ የሚከፍሉት ስለ ሀገራቸው ነው እንጂ ሌላ አንዳችም ጥቅም ኖሮቸው አይደለም። ለሀገር የሚቆሙትን ማክበር ፣ መልካም አርያነታቸው መውሰድ የጨዋ ኢትዮጵያዊ ባህሪው ነው። ክብር ለእናተ!!
ተጨማሪ ያንብቡ:  ይድረስ ለሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ቦርድ አባላት - ''ለእውነት አብረን እንቁም"

7 Comments

  1. AHUNIM EHADIG MIN YADIRGIH .

    SERTEH TIREH GIREH BILA . KE SEMAY MENA ATITEBIK !!!

    EHADIG IS TRYING HARD TO CLEAN THE MESS LEFT BY HODAM NEFTEGNAS FOR THOUSANDS OF YEARS .

    POVERTY, BACKWARDNESS , IGNORANCE AND ANTI DEMOCRACY – LEGACY OF OLD RULERS

    • ኢህአዴግ መስተፋቅር አሰርቶብሃል አልያም በጤናህ አይደለም።
      አንተም እንደ ጌቶችሕ ካንሰር ነህ
      You don’t get it or you are one of them I am not surprised.
      A narrow mind and a small brain.

      • goraw

        EHADIG IS CLEANNING THE MESS OF YOUR FATHERS.
        BUT , I THINK IT WILL TAKE MORE THAN A CENTURY TO CLEAN AND WHITE WASH THEIR DIRT AND FILTH .

        EHADIG MIN YARGIH ? ABATHI YABEKETEWIN BATEBE ???

  2. በስመ ፌደራሊዝም የመከፋፈልና የክልል ፍቅር እየሰራው …ኢህአዴግ ምን አደረግህ? ዜጎች ስለተቃወሙ ብቻ ንፁሃን እየገደለ… ኢህአዴግ ምን አደረገህ? ሀሳብን በነፃነት እየገደበ… ኢህአዴግ ምን አደረገህ? ኢ_ፍትሃዊነትና እኩልነት እያጠፋ… ኢህአዴግ ምን አደረገ? የሀገሪቱን የቀጣይ አንድነት ህልውና እያጠፋ…ኢህአዴግ ምን አደረገህ ወደጄ? …… …የምትል ኢህአዴግ መስተፋቅር አሰርቶብሃል አልያም በጤናህ አይደለም።

  3. የዘር ነገር! የሚዘረዝር!!
    ለኔ የሚል ሁሉን ነገር!
    ብልጠት ያለበት የሚያደናግር!
    ለመሆኑ መቼ ተጀመረ ይኸ ነገር??
    መብት ጥየቃ ሲጀመር
    ዘረኛ ተባልን ለማደናገር????

Comments are closed.

Share