November 19, 2017
27 mins read

የፖለቲካዉን መስቅልቅል ተረድተህ ጽንፈኛ : ቁርጠኛ ብሎም ጦረኛ እስክትሆን ሀገር እና ህዝብም ከቶም አይኖርህም

ሸንቁጥ አየለ

———–

የፖለቲካዉ ምስቅልቅል

———-

አሁን ያለዉ የፖለቲካ ምስቅልቅል እዉነትና ገጽታዉ ምን ይመስላል?የጠላት አቋሙስ ምን ይመስላል? ወያኔ ምን እየሰራች ነዉ? አጠቃላይ የፖለቲካዉ ትርምስምሱ እንዴት ይገለጻል ብለህ እራስህን ጠይቅ::ከአንድ እስከ አስር ያሉትን ነጥቦች አንድ በአንድ በስፋት እያብራራህ ከእዉነተኛ የትግል አጋሮችህ ጋር ብቻ እጅግ ጥልቅ ዉይይት አድርግባቸዉ::እዚህ በደምሳሳዉ የተሰጡትን ነጥቦች በምሳሌ እያሰፋፋህ የፖለቲካዉን ምስቅልቅል መጀመሪያ አጥብቀህ ተረዳ::

ወያኔ ድርጅቶችን ጠልፋ በመጣል: የህዝብን አመጽ ጠልፋ በመደምሰስ: ዉዥንብር እና ሀሰተኛ ተቃዋሚዎችን በማፍራት የተዋጣለት ስትራቴጅ ትከተላለች:: አሁንም ወያኔ በብዙ አቅጣጫ የህዝቡን ትግል የመጠለፍ እና ትግሉን የመቆጣጠር ስልት ነድፋለች::እጅግ ብዙ ቢሊዮን ብሮችም ወደ ተቃዋሚ መሰል አምታች ሀይሎች ኪስ እየፈሰሰ ነዉ::

1ኛ. ኦህዴድ እና ብአዴን የሚባሉ አሽከሮቿን የኢትዮጵያዊነት ፕርፖጋንዳ አልብሳ ወደ አደባባይ አዉጥታቸዉ አንድ ሰሞን ልፍስፍስ ተቃዋሚዎችን ልባቸዉን መማረክ ችላለች::ወያኔ ግን መቼም ቢሆን ጸረ ኢትዮጵያዊ ስራዋን እንደማትዘነጋዉ በወያኔ ላይ ጽንፍ የያዙ እና ቁርጠኛ ጠላትነት የመሰረቱ ብቻ ያዉቁታል::መሃል ሰፋሪዎች የሀሰት ከበሮ በተመታ ቁጥር እስክስታ መች ናቸዉ እና ህዝባዊ ጠላት ናቸዉ:: በወያኔ ፕሮፖጋንዳ ያለ ምክንያት አይወሰዱም ልባቸዉ በከፊል ከወያኔ ጋር ስለሚተባበር ነዉ::

2ኛ. በአሁኑ ወቅት በዉጭ ሀገር የሚኖሩ ( በተለይም በአሜሪካ የሚኖሩ) እና ከወያኔ ሰፋፊ ፕሮጀክቶችን እየተኮናተሩ አብረዉ የሚሰሩ ሰቃጢ እና አስመሳይ ፕሮፌሰሮች በተቃዋሚዎች እና በወያኔ መሃከል ድርድር እናደርጋለ እያሉ የሀሰት ሽንገላ ለዋላላ እና ደንበርባራ ተቃዋሚዎች በሀገር ቤትም በዉጭ ሀገርም ተስፋ እየሰጡ ነዉ:: ወያኔ ሁሌም ይሄን ነገር ማድረግ በደንብ የተካነበት አሰራሩ ነዉ::ልክ የደርግን ሰንካላ ጀነራሎችን ሻቢያዎች እና ወያኔዎች ሆነዉ “እንቅፋት የሆነብን መንግስቱ ሀይለማሪያም እና ደርግ ናቸዉ::እነሱን ከጣልን ዲሞክራሲ እንዲሰፍን እናደርጋለን:: ህዝባዊ መንግስት እንመሰርታለን” እያሉ እንዳታለሏቸዉ መሆኑ ነዉ::በአሁኑ ሰዓትም እነዚህ አደራዳሪ ፕሮፌሰሮችም: ምሁራን ተብዬዎች እና የሀሰተ ተቃዋሚዎች አሁን ዲያስፖራዉ እና ሀገር ቤት የሚኖረዉ ተቃዋሚ መሃከል መደናገርን እንዲፈጥሩ ወያኔ ልኳቸዋል::እጅግ ብዙ ብርም ተመድቦላቸዉ እየሰሩ ነዉ::

3ኛ. ወያኔ በአሁኑ ሰአት በሀገር ቤት የለበጣ ድርድሩን እራሱ ከጠፈጠፋቸዉ የተቃዋሚ አመራሮች ጋር በማስመሰል እያከናወነዉ ሲሆን መሃል ሰፋሪዎች እና አስመሳይ ተቃዋሚዎች እንዲሁም ወደ ጽንፍ መምጣት ያልቻሉት ተቃዋሚዎች የሚዋልል አቋም ይዘዉ ወያኔ በሰላማዊ መንገድ ስልጣን ይለቃል የሚል ለበጣን እያራመዱ ነዉ::

4ኛ. ወያኔ በአንድ መልኩ ኢትዮጵያዊነትን አራመድኩ ሲል ቢደመጥም በሌላ መስመር ደግሞ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከተሰለፉ ሀይሎች ጋር እጅግ ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ዉስጣዊ ድርድር እያደረገ እና ሀገሪቱን አፈራርሶ እንደሚያስረክባቸዉ ቃል እየገባ ነዉ::ወያኔ ማንኛዉንም አይነት ድርድር ያደርጋል::ማንኛዉንም አይነት ማታለያ እና ማዘናጊያ ስልት ይጠቀማል::ግን ወያኔ አንድም ጊዜ አላማዉን አይስተዉም::

5ኛ. አንዳንዱ መሃል ሰፋሪ እና ዋላላ ተቃዋሚ ወያኔ እርስ በርሱ ተባላ : መስማማት አቃተዉ: የወያኔዎች ስብሰባ ልዩነት በመሃላቸዉ ፈጠረ በማለት ወያኔን በፕሮፖጋናዳ እና በግርግር ሊጥላት እንዲሁም ህዝቡንም በከንቱ ተስፋ ሊሸነግል መከራዉን ያያል::ሆኖም ይሄ ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ህዝቡን በማይሆን ተስፋ በመሙላት እዉነቱ እየተገለጸ ሲመጣ ህዝቡ ተስፋ እንዲቆርጥ እና ለመራራ ትግል እንዳይዘጋጅ በማድረግ የአቋራጭ አሸናፊነት እንዳለ በማሰመሰል ነገሮችን ያለዝዛቸዋል::መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅ “ኢህ አዴግ የሾላ ፍሬ አይደለም::በድንጋይ አይወርድም” ያለዉ በጦር እንደመጣን የምንወርደዉ እና የሚያወርደን እዉነተኛ ጦረኛ ብቻ ነዉ ማለቱ ነዉ::

6ኛ. የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እርስ በራሳቸዉ መባላትን አሁንም እንደመረጡ ነዉ::እርስ በራሳቸዉ ከመተማመን ይልቅ የኢትዮጵያን ጠላቶች በማመን የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ በኢትዮጵያ ጠላቶች እጅ ላይ አኑረዉታል::ሌላዉ ቀርቶ ከአንድ ጎሳ ወጣን በአንድ ጎሳ ስም ድርጅት መስርተናል የሚሉ የተቃዋሚ ሱቅ በደረቴ ፓርቲዎች ጮህዉ በአደባባይ እንደሚናገሩት ወያኔን አምርረዉ ከመጥላት ይልቅ እርስ በርሳቸዉ በመራራ ጥላቻ ታንቀዋል::

7ኛ. ተቃዋሚዎች በአንድ ጉዳይ ላይ በጥለቀት እና በትእግስት ከመከራከር እና ከመወያዬት ይልቅ በግልብልብ እና በግብታዊነት እንዲሁም ኢትዮጵያዉያን ከመተማመን እና እርስ በርስ ከመምከር ይልቅ በዉጭ ሀገራት ምክር ላይ የመንጠልጠል አባዜ ዉስጥ ተቀርቅረዋል:: ይሄም አልበቃ ብሎ የኢህአፓነት: የደርገነት: የመኤሶንነት: የንጉሳዊነት ማንነት እየመዘዙ እርስ በርሳቸዉ አሁንም ለመጠፋፋት የሚያደቡት ምሁራን ብዙ ናቸዉ::ከዉጭ ሀገር እስከ ሀገርቤት ያላቸዉ የፖለቲካ ተሳትፎም ቀላል አይደለም::ሀገር ለማዳን እና ህዝብን ለመታደግ ከቶም ይቅር ለእግዚአብሄር ለመባባል ምንም ፍላጎት የላቸዉም::ከኢትዮጵያ ህመም እና መከራ ይልቅ የእነሱ የግል የልብ ቂም እርስ በርስ እንዲጠፋፉ አሁንም እንዲጠላለፉ አሁንም ቁርጠኛ አድርጓቸዋል::እርስ በርሳቸዉ አብረዉ ቆመዉ ሀገሪቱን እና ህዝቡን ከመታደግ ይልቅ አንዳንዱ ከወያኔ አሁንም እንደወገነ ሌላዉ ደግሞ አሁንም ከሻቢያ እንደተተለለ ብሎም እርስ በርስ ለመጠፋፋት እንደወሰነ አሁንም ሀገሪቱ መራራ የፖለቲካ አዘቅት ዉስጥ እንድትወድቅ አድርገዉ ያንኑ ዲያቢሎሳዊ ስራቸዉን ቀጥለዋል::ጥላቻ ወደ ቀዉስነት ደረጃ አድርሷቸዋል ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያዊነት ማማም ላይ አዉርዷቸዋል::ከነዚህ አጋር ከቶም ሚስጢር መስራት አይቻልም::

8ኛ. ኩርፊያ; እኔ ያልኩት ካልሆነ: እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ የሚለዉ የኢትዮጵያ ምሁራን አባዜ እንዳለ ሆኖ በርካታ የኢትዮጵያ ምሁራን የአሜሪካ መንግስት እና የምዕራብ ሀገራት ወያኔን ታግሎ እንዲጥሉላቸዉ ወይም ደግሞ የአሜሪካ መንግስት እንዲያነሳላቸዉ እና እነሱን እንዲሰይማቸዉ የመማለል ከንቱ የትግል ስልት ላይ ተንጠልጥለዉ ቀርተዋል::ሆኖም ይሄ አካሄድ ከቶም የህልም እሩጫ መሆኑን የሚያዉቁት ምሁራን ድምጻቸዉን ከማሰማት እና ተሰባስቦ ወደ መራራ እርምጃ ከመሄድ ይልቅ በነዚህ የምዕራብ መንግስታ አጎብዳጅ ምሁራን ጮህት ተደናግረዉ ዝም ብለዋል::

9ኛ. የወያኔ ተላላኪዎችን ወደፊት ለማምጣት እና ተቃዉሞዉን ለመቆጣጠር እዉነተኛ እና ቁርጠኛ ታጋዮችን በህዝብ ተቀባይነት እንዳይኖራቸዉ አጠብቀዉ ይሰራሉ:: ከዚያም ዘለዉ በዉጭ ሀገር በሚንቀሳቀሱ : በሀገር ቤት በሚንቀሳቀሱ እና ወያኔ በሚስጢር በቀጠራቸዉ ተቃዋሚዎች እዉነተኛ ተቃዋሚዎችን የማስጠፋት ስራ በስፋት ይሰራል:: እነ እከሌን እንዴት እናጥፋቸዉ? ለነገ እንቅፋት ናቸዉ በማለት ብዙ ጥናቶች ይደረጋሉ:: እዉነተኛ ተቃዋሚዎች በአንድ በኩል በወያኔ ይሳደዳሉ: ይገደለላሉ: ይታሰራሉ: በረሃብ ይጠበሳሉ: ብዙ መከራዎችን ይቀበላሉ::ሆኖም አስመሳዮች : ተገለባባጮች : የወያኔ አገልጋይ የነበሩ መርህ አልባ ፖለቲከኞች ደግሞ ወደ ሰማዬ ሰማያት ከፍታ ላይ በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ ይሰቀላሉ::ህዝቡ እራሱ ማስተዋሉን የተነጠቀ ይመስል ድል እና አሸናፊነት ከእንደዚህ አይነት አስመሳዮች ይጠብቃል::ለነገሩ ኢትዮጵያ ልማዷ ነዉ::በላይ ዘለቀን ሰቅላ ባንዳዎችን የምትሾም::ህዝቡም አይገርመዉም::ያረዱትን : ያስገደሉትን: ያሳደዱትን እና የሰደቡትን መልሶ ነጻናት እና ብልጽግናን ያመጡለት ዘንድ አንጋጦ ያስተዉላቸዋል::ተስፋም ያደርጋቸዋል::

10ኛ. አሁን ያለዉን የፖለቲካ ምስቅልቅል በተጨባጭ ለመረዳት ጎንደርን እንደማሳያ እንዉሰዳት እና አንድ አስቀያሚ እዉነትን እንመልከት::የተቃዋሚ ፖለቲከኛዉ የእርስ በርስ መከፋፈሉን ጥልቀት ለማዬት በአሁኑ ሰአት ከጎንደር የተሻለ ማሳያ የለም:: ሰባት የጎንደር ተወላጆችን ብትወስድ እና ሰባቱም ሰዎች ሰባት ድርጅት ዉስጥ እንደሆኑ ብታዉቅ ብሎም ከሰባቱም ጋር በጋራ ስለመታገል ምክክር ብታደርግ የሚገርም እና የሚያስደምም እዉነታን ታገኛለህ::ምናልባትም አራቱ ሰዎች አማራ ድርጅቶች የሚባሉ ፓርቲዎች ዉስጥ አራት ቦታ መሽገዋል ብለህ አስብ::እንዲሁም ምንአልባትም ሁለቱ ሰዎች ደግሞ ህብረ ብሄራዊ እሆኑ ሁለት ፓርቲዎች ዉስጥ መሽገዋል::አንዱ ደግሞ በጎንደር ስም እተዋቀር ድርጅት ዉስጥ የመሸገ ነዉ ብለህ አስብ::እነዚህ ሰባት ድርጅቶች ዉስጥ የመሸጉ ሰባት ሰዎች ወያኔን እንደሚታሉ ቢነግሩህም ዋናዉ ጥላቻቸዉ ግን እርስ በርሳቸዉ ነዉ:: በመሃላቸዉ ያልተጨበጠ እና የተወናበደ አሉባልታ እንደጉድ ይርመሰመሳል::

ምናልባትም ሰባቱም ድርጅቶች በትጥቅ ትግል የሚያምኑ እና ወያኔን በሀይል መወገድ አለበት የሚሉህ ሊሆኑ ይችላሉ:: ሆኖም እነዚህን ሀይሎች ጠጋ ብለህ የመረመርሃቸዉ እንደሆነ ስለህዝቡ ማዘንህ አቀርም:: ጉልበት እና አቅም ቢኖራቸዉ ምናልባትም ልክ ቀይ ሽብር እና ነጭ ሽብር በማለት በደርግ ድንቁርና እንዲሁም በሻቢያ እና በወያኔ ተንኮል እንደተቀነባበረዉ የእርስ በርስ ፍጅት አሁንም በጎንደር ህዝብ ላይ ከማምጣት የማይመለሱ መሆናቸዉ ቀስ ብሎ ይገለጽልህ ይሆናል:: እርስ በርስ በጣም ስለሚጠላሉም እነሱ እርስ በርስ ለመጠፋፋት በሚወስዱት እርምጃ አንተ እገሌን ትደግፋለህ እያሉ ህዝቡን እና ወጣቱን እንደሚያጠፉት ግልጽ የሚሆንልህ ሁሉንም በጣም ደጋግመህ የሚሰሩትን ስራ ቀርበህ የመረመርህ እንደሆነ ነዉ:: የሚገርመዉ ደግሞ እነዚህ ከአንድ አካባቢ የወጡ ሰዎች አንዳንዶቹ የኢትዮጵያ ጠላትም የአማራ ህዝብ ጠላትም የሆነዉን ኢሳያስ አፈወርቂን እንደ ፈጣሪያቸዉ እና እንደ አምላካቸዉ በመዉሰድ የራሳቸዉን የጎንደር ሰዉ እና ታጋይ ግን መደምሰስ እንዳለበት የሚሰብኩ ሆነዉ ታገኛቸዋለህ::እድሉ የቀናቸዉ እንደሆነም አቢዎታዊ እርምጃ እርስ በርሳቸዉ ከመወሳሰድ እንደማይመለሱ በደንብ ይገባሃል::

————–

ጽንፈኛ : ቁርጠኛ ብሎም ጦረኛ እስክትሆን ከቶም ትግል እንዳልጀመርክ እወቅ::ሀገር እና ህዝብም ከቶም እንደማይኖርህ ተረዳ

————–

እናም በዚህ ሁሉ ትርምስምስ ዉስጥ እዉነተኛ ህዝባዊ ትግል የያዘዉ ህዝብ በበርካታ ዉስብስብ ሁኔታዎች ዉስጥ በሚሸረብ እና በሚከወን ፖለቲካ ታንቆ ተይዟል:: እና መፍተሄዉ ምንድን ነዉ ብለህ ከጠየቅህ ጠላትህን እወቅ: ጽንፈኛ ተቃዋሚ ሁን ብሎም ለመስዋዕትነት እራስህን ከመሰሎችህ ጋር ብቻ ሆነህ አዘጋጅ የሚል ነዉ::ሀገር እና ህዝብ እንዲኖርህ ከፈለግህ መስዋዕትነት ወሳኝ ነዉ::በጦር የመጣዉ ወያኔ ያለ መራራ ዉጊያ ከቶም ስልጣኑን ለህዝብ አያስረክብም::መራራ ጦርነት ደግሞ መራራ አሰራሮችን እና መራራ መርሆችን መከተልን ይጠይቃል::በየትኛዉም የትዉልድ ፍሰት ዉስጥ ይሄ ሀቅ ነዉ::ጽንፈኛ እና ቁርጠኛ እስክትሆን ጠላትህን አታጠፋዉም:-ሀግር እና ህዝብም አይኖርህም::እናም የሚከተሉትን ነጥቦች በልብህ እያንሰላሰልህ ወደላቀ ድርጅታዊ መርህ አሳድጋቸዉ::

1ኛ – የጠላት ረድፉ እና መደቡ አንድ ነዉ:: ጠላትህን ያለ እርህራሄ ለይተህ ካላወቅህ ከቶም ህዝብህን ነጻ አታወጣዉም::ሌላዉ ቀርቶ ይሄን እስክታደርግ ትግል እንዳልጀመርክ እወቀዉ::

2ኛ- የወዳጅ ረድፉ እና መደቡ አንድ ነዉ::ወዳጆችህን እና የመደብ አጋሮችህን ማስተባበር እስክትችል ከቶም ጠላትህን መደምሰስ አትችልም:: የወዳጆችህን ጥንካሬ መቁጠር ካልጀመርህ ደግሞ ከቶም ወዳጆችህን ወደ አንድ ልታመጣቸዉ አትችልም::መሃል ሰፋሪዎቹ ጠላቶችህ መሆናቸዉን እስክታዉቅ እና ከለዘብተኞች ጋር መሞዳሞድህን እስክትተዉ ድረስ ከቶም ትግል እንዳልጀመርክ እወቅ::የገጠመህ ጠላት እጅግ ጽንፈኛ እና ቁርጠኛ ብቻ ሳይሆን በመራራ ጥላቻ ተረግዞ በመራራ ጥላቻ ዉስጥ እየኖረ ያለ መሆኑን ለማወቅ መከራ የተሸከመዉን ህዝብ ቀርበህ አነጋግረዉ::

3ኛ- ህዝብ እና ሀገር እንዲኖርህ ከፈለግህ ጠላቶችህን መደምሰስ አለብህ::ከዋናዉ ጠላትህ በላይ ደግሞ መሰረታዊ ጠላቶችህ ከጠላትህ ጋር ተባባሪዎቹ እና መሃል ሰፋሪዎቹ መሆናቸዉ እስካላወቅህ ድረስ በጠላት ወጥመድ ዉስጥ የመያዝ እድልህ ሰፊ ነዉ::ጠላት ለመደምሰስ ከመሃል ሰፋሪዎች ጋር የቆምክ እለት ተደምሳሽ ነህ:: በተለይም አማራ ነኝ ብለህ በወያኔ የተጠፈጠፈ ብአዴንን ዉስጥ የሚልከሰከስ/የተልከሰከሰ/ አማራ ያመንክ እንደሆነ ወይም ኦሮሞ ነኝ ብለህ ኦህዴድ ዉስጥ የተልከሰከሰ/ወይም የሚልከሰከስ/ ኦሮሞ ያመንክ እንደሆነ ያኔ ፈጽሞ በወያኔ መረብ ዉስጥ እንደወደቅህ እወቅ:: ትግሉ የብሄሮች ትግል ብቻ ሳይሆን የመደብ ትግል ባህሪም እንዳለዉ አልገባህም እና እራስህን መርምር:: እንኳን የአለም ስነ መንግስት የሰማዩ ስነመንግስት ያለ ተጋድሎ አይወረስም::ስነ መንግስትን መመስረት : ህዝብህንም ነጻ ማዉጣት እና ሀገር እንዲኖርህ ከፈለግህ እጅህን ወደ ቀስቱ ላይ ዘርጋዉ::ስልጣን የጨበጠን ሀይል በሀሜት: በሀሰት እና በፕሮፖጋንዳ ማዉረድ ከቶም አይቻልም:: የአንዲት ሀገር ህዝብ ምድራዊ ሰቀቀን እና መከራ እንዲፈወስ ለመሰዋዕትነት እራሳቸዉን የሚያቀርቡ ጀግኖች ወሳኝ ናቸዉ::እነዚያን ጀግኖች ፈልገህ እስክታገኝ ከቶም ህዝብህን ነጻ እና የተከበረ ህዝብ ማድረግ አትችልም

4ኛ. በዚህ ዘመን ዶክትሬት እና ፕሮፌሰርነት አንጠልጠልጥለዉ የአንድ አርሶ አደር ያህል የፖለቲካ ስሌት ማንሰላሰል የማይችሉ ሆኖም ዶክተር እና ፕሮፌሰር ስለተባሉ መሪ: የፖለቲካ አማሳይ: አስታራቂ: እና የፖለቲካ ፈራጆች መሆን ያለባቸዉ የሚመስላቸዉ በርካታ ቀዉሶችን ህዝባችን ማፍራቱን አትርሳ::እነዚህ የህዝባችን ዋና ህመም እና ስቃይ ናቸዉ::ስለሆነም እዉነተኞቹን እና ቁርጠኞቹን ምሁራን: ዶክተሮች እና ፕሮፌሰሮች ፈልገህ እስግታገኝ በስመ ምሁር አብረሃቸዉ አትግበስበስ::

5ኛ. አስመሳይ እና ሀሰተኛ አዎንታዊነት አነብናቢ ምሁራን : ተናጋሪዎች: የሀይማኖት ሰዉ ነን የሚሉ ሀሳዉያን እና በገንዘብ ልባቸዉ የነቀዘ ባለ ሀብቶች ኢትዮጵያን ተብትበዉ ይዘዋታል::ስያፍሩ ወያኔን በአደባባይ ላይ እድሜ እንዲሰጠዉ የሚጸልዩ ሞልተዋል::ግን የሚነግዱት በሀይማኖት ስም ነዉ:: ሆኖም ስለሚፈሰዉ ህዝባዊ ደም: ስለወገናቸዉ መከራ : ስደት ; ርሃብ እና ጭቆና ከቶም ግድ አይሰጣቸዉም:: ነገ በኢትዮጵያ ምድር የሚከሰተዉ የርስ በርስ ፍጅት እና ትርምስ ከቶም አያሳስባቸዉም::የወያኔን ጎሰኝነት እየባረኩ: በአዳራሾቻቸዉ በጌታ ስም ወያኔን እየባረኩ እየጮሁ የሚለፈልፉ ሞልተዋል:: ስለዚህም የሀሰትኛ አዎንታዊ እና ጠጋጋኝ ቅላት እና የአረፍተ ነገር ኳኳታ ሲያሰሙ የሰማህ እንደሆነ ከነዚህ እራቅ:: እንኳን የምድሩ ስነ መንግስት:እና ህዝብ ድህነት ቀርቶ የሰማዩ መንግስት ዉርስ በመራራ መስዋዕትነት እንጅ በሀሰተኛ አዎንታዊ የቃላት ለበጣ አይገኝም እና::

6ኛ. ነገሮች በጣም ተስፋ አስቆራጭ ሆነዋል::የኢትዮጵያም ህልዉና እጅግ አሳሳቢ እና ፈታኝ ሆኗል::ሆኖም እዉነተኛ ህዝባዉያንን የምታገኛቸዉ በመከራዉ ሰዓት መሆኑን አትርሳ:: እሳቱ በጣም ሲግፈጠፈጥ ወርቁ እየነጠረ እንደሚመጣዉ ማለት ነዉ:;እናም በተስፋ አስቆራጩ በዚህ ዘመን ጀግኖቹን በርትተህ ማሰስህን ቀጥል::

7ኛ. ኢትዮጵያ ከቶም አትጠፋም ብለህ እመን::ሆኖም መራራ መስዋዕትነት ከፊት ለፊትህ እንዳለ አትርሳ::ታላቁን ባለ ራዕይ ንጉሰ ነገስት አጼ ቴዎድሮስን በዚህ ዘመን አስበዉ::ኢትዮጵያ ለ179 አመታት ተከፋፍላ ኖራ ሳለ ታላቁ ባለ ራዕይ ቴዎድሮስ ግን ከቲንሿ አንዲት የጎንደር ቀበሌ ዉስጥ ሆኖ እንዲህ ሲል አለመ::”የኢትዮጵያ ባል: የእየሩሳሌም እጮኛ እኔ አጼ ቴዎድሮስ ተከፋፍሎ መከራ እየወረደበት ያለዉን ህዝቤን በአንድ አደርገዋለሁ”:: እናም የተከፋፈለዉን ህዝብ አንድ አደረገዉ::ሀገር እና ህዝብ በሀይል ይሰበሰባል::መጸሃፍ እንደሚልም በጥበብ ይጸናል::ሀያሉ ንጉሰ ነገስት ቴዎድሮስ በሀይል የሰበሰበዉን ሀገር እና ህዝብ ጠቢቡ ንጉሰ ነገስት ምኒልክ ደግሞ በጥበብ አጸናዉ::አንተ የነዚህ ነገስታቶች ልጅ መሆንህን አትርሳ::በመክራ እና በእሳት መሃከል የሚራመዱ::ሽህ አመታት የተዋጉ::ሽህ አመታት በነጻነት የኖሩ::በመከራ እና በጠላት ብዛት ተበትኖ እና መክኖ ያልቀረ የሀያላን ምድር ያፈረሃ መሆንህን እመን :: ሀያል ኢትዮጵያዊ መሆንህን አንዳትረሳ:: ይሄን ጽንፍ ያዝ::በዚህም ጽንፍ ጠላትህን ሁሉ ደምስስ:: ያኔም ሀገር እና ህዝብ ይኖርሃል::

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop