ታሪክ የወረሰ ትውልድ፣ ያልተወለዱ ህልሞችና የማዋለጃው መንገድ – አንዷለም አራጌ
የዛሬ 150 ዓመት በሕይወት ብንኖር ኑሮ ብዙዎቻችን ምንአልባት ሁላችንም በዘመኑ ከኖሩት አባቶቻችን ጋር በአንድ የአስተሳሰብና የኑሮ ዘይቤ ምህዋር ላይ እንደምንተም እገምታለሁ፡፡ የነበረውን የህይወት ከባቢ እንደዘላለማዊና የማይቀየር እውነት በመቁጠር እንደምንመላለስ አስባለሁ፡፡ ፈጣሪ በማይቋረጠው