ግንቦት7 እና ኦዴግ ምንና ምን ናቸው ……….!!! ከታምራት ይገዙ

 

ፋሲል የኔዓለም

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የጋሼ ሌንጮ ነገር በሚለው መጣጥፉ “አርበኞች ግንቦት7 እንደ ኦዴግ አይነቶችን እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል። ኦዴግ ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት የሚታገለውን ድርጅት “አላማህን ወድጀዋለሁና አብሬህ ልስራ” ቢል “ተወዳጁ” ድርጅት “እምቢ” ማለት ይቻለዋል? አይመስለኝም። እንዲህ ካለማ ከራሱ አላማ ጋር ተጋጨ ማለት ነው።”  እንደ እውነቱ ከሆነ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም “እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል ሲል ይህ ወንድማችን አንድም የግንቦት 7 አባል አሊያም አፍቃሪ መሆኑን ነው የሚያሳብቀው ምክንያቱም ግንቦት ሰባት እንከን የማይወጣለት ድርጅት አድርጎ ለመሳል በማሰቡ::

በሌላ በኩል በኔ እይታ ኦዴግ ከግንቦት ሰባት ጋር ለመስራት ሃሳብ ያቀረብ አይመስለኝም ምክንያቱም ከዛ ቀደም ብሎ ኦዴግና ሸንጎ አብረው ሊሰሩ እንደተስማሙ በአዲስ ድምጽ ሬዲዮ ላይ ዶ/ር ቡሻ  የሸንጎ አባልና ዶ/ር ዲማ  ነጎ ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት አደርገው ነበር::  በኔ ግምት ይህንን የሰሙ የግንቦት ሰባት አመራሮች አገራዊ ንቅናቄ የሚባል ህብረት እንዲፈጠር ለዚህም ታዋቂ ግለሰቦችን ሲፈልጉ ለሸንጎ ጥሩ አመለካከት የሌላቸውን ፕ/ር ጌታቸው በጋሻውና ሻለቃ ዳዊትን ያገኛሉ እነዚህም ታዋቂ ግለሰቦች በስድስት ወር ውስጥ አዋክበው  አገራዊ ንቅናቄ የተባለውን በሲያትል ከተማ መሰረቱ::  ፕ/ር ጌታቸውም  በእለቱ በአንደበታቸው ሲናገሩ “ይህንን የመሰለ ጠንካራ ህብረት ለመመስረት እኔና ሻለቃ ዳዊት ስድስት ወር ነው የፈጀብን ብለው ነበር”::  እኔም የንን ምስረታ ከተመለከትኩ ቦሃላ የተረዳሁት አግላይ ከመሆኑ በላይ ያ ድርጅት እንዲቆቆም የታሰበውአንድም  ግንቦት ሰባት በመውደቅ ላይ ስለነበረ ለመታድግ አሊያም የግቦት ሰባት የቀን ቅዥት የነበረውን አውራ ድርጅት ሆኖ የመውጣት አባዜ ለማሳካት  መሆኑን በግልጽ ይታወቅ ነበር::  እኔም ያን አይነት የተኮላሸ አካህኣድ በመመልከት በዛ ሰሞን መጣጥፊ

<< የአሜሪካ ሰዎች ኑ ጠላ ቅመሱ

የካናዳ ሰዎች አውሮፓም ያላችሁ ኑ ጠላ ቅመሱ

እንደ መምህሩ አንደ ጌታቸው በጋሻው አንደ ሻለቃ ዳዊት እንድትጠነስሱ>> የሚል ትዝብቴ የያዘ ጹሁፍ አስነብቤ ነበር::

ሰሞኑን ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም “የጋሼ ሌንጮ ነገር በሚለው መጣጥፉ “አርበኞች ግንቦት7 እንደ ኦዴግ አይነቶችን እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት መሆኑን አስመስክሯል” ይለናል እንደ ኤውነቱ ከሆነ የጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ጹሁፍ ፈረንጆች እንደሚሉት”ከነጭ ውሸትነት” ያለፋ አይደለም;;

በኔ እይታ የግንቦት ሰባትን አካሄድን ስመለከትው ከዚህ ቀደም እንደከተብኩት ይህ ግንቦት ሰባት ከተመሰረተ ጀምሮ ህልምና  የቀን ቅዠቱ ” አውራ ድርጅት” ሆኖ ህወሀት/ኢህኣዴግን  ድርጅት ለመተካት ነበር ሲቅበዘበዝ የነበረው እንጂ ኢትዮጵያንና ህዝቦቾን ለመታደግ አልነበረም የሚል እምነት አለኝ:: ይህንን እምነቴን የሚያጠናክርልኝ ግንቦት ሰባት ከተመሰረተ ጀምሮ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ማለትም  በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ድርድር አያስፈልግም የሚሉ ድርጅቶች አብረን እንስራ ሲሉት ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ ድርጅት እንደነበረ እኔ በግሌ በተወሰነ ደረጃ አውቃለው ሌሎችም ያውቃሉ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህወሓት “ከቡና ጠጡ” ወደ “መርዝ ጠጡ” ከታደሰ ብሩ

በ2012 በምንርብርት ከተማ ከዶ/ር በርሀኑ ጋር ቁርስ እየበላን ውይይት አድርገን ነበር በዛ ውይይት ላይ ከቀረበው  ጠያቂ ለምንድን ነው ግንቦት ሰባት እንደ ታሰበው ወደ ፊት በፍጥነት ሊጎዝ ያልቻለው የሚል ጥያቄ  ከአንዲት እህት ቀርቦ ነበር ዶ/ር ብርሃኑም ሲመልሰ ” ኤርትራ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ድርጅቶች ለአራት ለአምስት ስለተከፋፈሉ እነርሱን ስናስማማ ነው የከረምነው አሉን:: እኔም በዛላይ ያለኝን ጥያቄ ለመጠየቅ እጄን አነሳው ነገር ግን ዶ/ር ሌላ ቀጠሮ ስለነበራቸው የኔን ጥያቄ ለመቀበል ግዜ አልነበራቸውም::  ከስብሰባ ስንወጣ አንድ ሰው ቀረብ ብሎኝ ለዶ/ር ብርሃኑ የነበረህ ጥያቄ ምን ነበር ብሎ ቢጠይቀኝ የመለስኩለት “በኢትዮጵያዊነት የማያምኑ ድርጅቶችን ለማስታረቅ ከማሰብና ግዜ ከማጥፋት ይልቅ በኢትዮጵያዊ ሉአላዊነት ላይ ምንም ጥያቄ ውስጥ የማይገቡ ድርጅቶች አብራን እንስራ እያሉ እነሱን ወደ ጎን አድርገው  ከኢትዮጵያ እንገንጠል ከሚሉ ጋር ለመስራት ግዜ አችውን የምታጠፉት ለምንድን ነው? ግንቦት ሰባት ንቅናቄ እንጂ የተባበሩት መንግስታት ነው ወይ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የለችም የሚሉትን ወገኖች ለማስታረቅ ላይ ታች የሚሉት የሚል ነበር ጥያቄዪ አልኩት:: ያም ሰው ጥያቄው ትገቢ ይሁ ወይንም አይሁ በሚገልጽ ምልክት ይመስለኛል አንገቱን ከፍ ዝቅ በማድረግ መለሰልኝ::

እንደ እውነት ከሆነ ግንቦት ሰባት ሲመሰረት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ድርጅቱን በአባልነት ደረጃ ባይሆንም አቅሜ በሚፈቅደው ሁሉ ደግፌላሁ በመደገፌም የምጸጸትበት ምንም ነገር የለኝም ምክንያቱም ማንኛውም ድርጅት ለአገርና ለህዝብ የሚጠቅም ራይ ሲኖረው መደገፍ ከዛ አይነቱ ራይ ሲያፈነግጥ አለመደገፍ የሁላችንም ምርጫ ይመስለኛል በዚህ መልኩ የግንቦት ሰባትን አካሄድ  ከግዜ ወደ ግዜ ስመለከት ቡዙም አብሬ ለመጎዝ ፍላጎቴ እየጠፋ መጣ ምክንያቱም እንደኔ ተከታይ የሆኑትም ሆኑ በአባልነት የተመዘገቡት አብዝኞች በአካባቢዪ ያሉት ግለሰቦች ድርጅቱንም ሆነ መሪዎቹን ወደ ማምለክ ተለወጡ ይህም ለኔ የሚዋጥልኝ ሆኖ አላገኘሁትም ነበር በዚህ መሃል በ2013 በወረሃ ጥቅምት የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሀኑ (በወቅቱ ዶ/ር ነብሩ) ከአቶ አበበ ገላው ጋር የኢሳትን አመታዊ በዓል ለማክበር በምኖርብርት ከተማ ተገኝተው ነበር በአሉ ላይ  ፕ/ር ብርሀኑ ዛሬ እዚህ የምገኘው ለኢሳት ስለሆነ ስለ ግንቦት ሰባት ጥያቄም ሆነ አስተያየት አልቀበልም ነገር ግን በግንቦት ሰባት ላይ ጥያቄና አስተያየት ያላችሁ በነገው እለት ዳንፎርዝ በሚገኘው ምግብ ቤት ወስጥ ተግኝታችሁ መነጋገር እንችላለኝ አሉ::

እኔም በእለቱ ስብሰባው ላይ ታደምኩ የተለያዩ ጥያቄውችና መልሶች ከተደመጡ ቦሃላ እኔም ተራ ደረሰኝና ተነሳው ጥያቄም ከመጠየቄ በፊት ፕ/ር ብርሀኑ ስብሰባውን ሲከፍቱ እንዲህ በለው ነበር “አሁን እዚህ ያላችሁ ሰዎች ጥያቄ ብቻ አይደለም  ስድብም ካላችሁ መሳደብ ትችላላችሁ” ብለው ስለነበር እኔም ይህንን አልኮቸው “በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ  በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ንጉስ የነበሩ ሰው ሸንጎ ሰብስበው እሲቲ ስደቡኝ ይሉ ነበር ካዛም አንዱ ተነስቶ “ትገርፈኝም እንደሆነ ትገልኝም እንድሆን ከፊትህ ቆሚያላው ያ ለምጣም ሚኒሊክ ቢዪ ሰድቢያለው” ብሎ ተቀመጠ እርሶ ዶ/ር ብርሀኑ ዛሬ ያንን አባባል ነው ያስታወሱኝ ካልኩኝ ቦሃላ ጥያቄዪን እንዲህ በማለት በአስታተያየት ጀመርኩ::

ተጨማሪ ያንብቡ:  የይቅርታ ፖሊቲካና የፍትሕ ነጻነት ወቅታዊ ችግራችን - ቁጥር 2 - ባይሳ ዋቅ-ወያ

ዶ/ር ብርሃኑ የደርጅቶት አባልና ደጋፊ የሆኑ ሰዎች ድርጅቱንና እርሶን ከመደገፍና ከማገዝ ባለፈ መልኩ እርሶን; ድርጅቶትን ግንቦት ሰባትና እንዲሁም ሚዲያን (ኢሳትን) ማምለክ ጀምረዋል ብዪ ወደ ግንቦት ሰባትና የሻቢያን ግንኙነት   በተመለከተ ገና ከመጀመሬ በዶ/ር ብርሃኑ በግራ በኩል ተቀምጣ የነበረች እህት  ስሜን በመጥራት ተቀመጥ ተቀመጥ አለች አሶን ተከትሎ ሌላው ወንድም  ከወደ በሩ ሆኖ ተቀመጥ ተቀመጥ አለ እኔም የእነዚህ ሁለት ሰዎች ጫጫታቸውን ከስጨረሱኩ ቦሃላ “ዶ/ር ብርሃኑ እርሶ ጥያቄ አይደለም ስድብም ካላችሁ ተሳደቡ ለማስተናገድ ዝግጁ ነኝ ብለው እድሉን ቢሰጡኝ እነዚህ ሁለት ሰዎች የሚሉትን ይሰማሉ?  እነዚህ ሰዎች የእርሶና የደርጅቶት ደጋፊዎች ሳይሆኑ የርሶና የድርጅቶት አሚላኪዋች ነቸው ይህንን በግዜ ካላስወገዱ የኾላ ኾላ ለርሶም ሆነ ለድርጅቶት ዋጋ የለውም ምክንያቱን  “አምልኮ ለፈጣሪ” እንጂ ለግለሰብ; ለድርጅትና ለሚዲያ አይደለም አልኮቸው :: ዶ/ር ብርሃኑም ሲመልሱ አንተ እንዳሰብከው አምላኪዎች ሳይሆኑ ካለው ግዜ አንጻር ነው ብለው መለሱ እኔም የተሰማኝን ተናገርኩ እርሳቸውም መልሳቸውን ተናገሩ::

በነገራችን ላይ ያን ግዜ ያዙኝ ልቀቁኝ ከሚሉት አምላኪዎች ግማሾቹ ለግንቦት ሰባት ስብሰባ ኤርትራ ደርሰው ከመጡ ቦሃላ በኤርትራ በኩል የሚደረገው ትግልም ሆነ  ጋዜጠኛ መሳይ መኮንንና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም  ኤርትራ ድረስ ተጉዘው ያቀናበሩት ቅንብር ከጋዜጠኛ ስነ ምግባር የወጣና የልማታዊ ጋዜጠኛ ያዘጋጀው  መሆኑን በዓይናቸው አይተው ስለተረዱት አባቶቻቻን የሚሉትን አባባል “ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል” የሚለውን በማስታወስ ግንቦት ሰባትን አይንህን ለአፈር ብለው ቤታቸው መቀመጥን ከመረጡ ሰንበት በት ብለዋል::

ወደ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም የጋሼ ሌንጮ ነገር ወደሚለው መጣጥፉ ስመለስ  ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ሊነግረን እንደሚያስበው ሳይሆን ግንቦት ሰባት የተጎዘው ጉዞ ከፈረሱ ጋሪው ቀደሞ በሚዲያ አጃቢነት እንጂ በትግሉ ውስጥ እንደ መቆየቱ ምንም የስመዘገበው እሚንት የሆነ ነገር አይታይም:: ይህንን ከተመለከትኩ ቦሃላ በምኖርበት ከተማ ላሉ የግንቦት ሰባት አባል ለሆነና ለግንቦት ሰባት ጥሩ አመለካከት አላቸው ከምላቸው ወንድሞች የተለያየ ውይይት ሳደርግ የሚሰማኝን ከመናገር አልቆጠብም ነበር:: ለምሳሌ ሁላችንም እንደምናውቀው የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራሮች በአንድ ወቅት ትግሉን ለመምራት ብለው ጠቅልለው ኤርትራ ገብተው ነበር አብረው እንደገቡ ሁሉ እብረው ወጥተው እንደነበር አይዘነጋም ይህንን በተመለከተ ከአንድ ወንድም ጋር ስወያይ “ኤርትራ የገቡት የግንቦት ሰባት አመራሮች ይህው ሁሉንም ነገር አይተው ተመልሰዋል ሁሉም እንደሚገነዘበው በኤርትራ በኩል የተሄደው ጉዞ ጥቅሙ ስላልታየ ለምን አሁን የግንቦት ሰባት አመራሮች ለግዜው የትጥቅ ትግሉን  ሙሉ በሙሉ ትተን (Suspended ) እድርገን ያለ የሌለ ሀይላችንን ሰላማዊ ትግሉ ላይ እንድናውል ግዜው የግድ ስለሚል ብለው ለአባላቶቻቸው ለውይይት አያቀርቡም ብለው ይህ ወንድሜ የሰጠኝ መልስ አንተ ሞኝ ነህ እንዴ” ግንቦት ሰባት ይህን የሚያደርገው ኢህአፓ ወይንስ ሸንጎ ደስ እንዲለው ነው የሚል መልስ ነበር የሰጠኝ” እኔም ስመልስለት ላካ ትግሉ ማን ደስ ይለዋል ማን ይከፋዋል ነው እንጂ የአገርና የህዝብ ጉዳት አይደለም የሚያሳስባችሁ በማለት ነበር የመለስኩለት::

ተጨማሪ ያንብቡ:  አማራ ሆይ! ቆሻሻ ሌባ ጣት እየተቀሰረብህ እስከ መቼ ትኖራልህ? - በላይነህ አባተ 

የኦዴግ አመራሮች አገር ቤት እንደሚገቡ ስሰማ ይኽው ወዳጄ ጋ ስልክ ደውዪ ሳወራው ይህንን ጨዋታችንን አስታወስኩት እርሱም ስመልስ “አዎ ብለኽኝ ነበር ነገር ግን ዶ/ር አብይ ለስልጣን ይበቃል ብሎ ከሶስት ወር በፊት ያሰበ ማን አለ አለኝ” እኔም ስመልስለት የድርጅት መሪ የሚመጣውን ሶስት ወር ሳይሆን ፎር ካስት ማደረግ ያለበት ከዓመትና ከሁለት ዓመት ቦሃላ ምን ይመጣል ብሎ ካላሰበ ከኔ ከተራው ግለሰብ በምን ተሻለ ስለው መልስ አልነበረውም::

በአጠቃላይ በአሁኑ ዘመን የሚደረገውን ሁሉ በቀላሉ ለሚከታለልና ለሚያውቅ ሰው ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ግንቦት ሰባትን ትክክለኛ መንግድ የተጎዘና “እንደ ኦዴግ አይነቶችን እምነት የማይጣልባቸውን ድርጅቶች እንኳ ለአገር አንድነት ሲባል አቅፎ ለመጓዝ የማይቸግረው ድርጅት ነው ሊለን ሞሞከሩ የተሳሳት ሙገሳ ለግንቦት ሰባት ለመለገስ ማሰቡን ነው የሚያሳየው ይህም በኔ እይታ ስህተት ከመሆኑ ባሻገር ድርጅቱ ከድጡ ወደ ማጡ እንደመክተትና ከስህተቱንም እንዳያርም ማድረግ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝም::

በመጨረሻም ለግንቦት ሰባት አመራሮችና አባላቶች እንዲሁም ለድርጅቱ ቅናዊነት ላላቸው ሰዎች ያለኝ መልእክት ፖለቲካ እንደ ሀይማኖት ”ዶግማ “ አይደለም ስለሆነም እንደ ግዜውና እንደ አካባቢው ሁኔታ የሚለወጥና የሚሻሻል ስለሆነ በዓሁኑ ሰዓት በዓለም ያሉ መሪዎች በተለይ ምዕራብያውያን  የአንድ ሀገር ህዝቦች እርስ ብረሳቸው ተዋግተው የመንግስት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ እይደሉም ምክንያቱም በኔ እይታ ጦሱም ለነሱ እንደሚደርስ ያውቃሉና:: ስለሆነም ግንቦት ሰባት አመራሮች በመሳሪያ ትግል መንግስት መለወጥ የሚሉትን ሃሳብ ቀይረው ሙሉ በሙሉ በሰላማዊ ትግል ለመታገል ለአባላቶቻቸውም ሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋዊ የሆነ መግለጫ የማውጫ ሰዓታቸው አሁን ይመስለኛል::

እርግጥ ነው የድርጅት አባላቶችም ሆኑ ደጋፊዎች በሁኔታው ላይደሰቱ ይችላሉ አማራሮቹንም በጥያቄ ሊያጣድፉ ይችላሉ በኔ እምነት መሪ ማለት ተከታዩን ማሳመን የሚችል ሰው ነው::  ይህንን ማድረግ የማይችል መሪ በፊትም የመሪነት ችሎታው አጠያያቂ ነበር ማለት ነው እያልኩ የዛሬን ጹሁፌን ልቆጭ::

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈቱ!

አምላክ አገራችንን ኢትዮጵያን በምህረቱ ይጎብኝልን!!

 

 

9 Comments

  1. በራሰህ ወያኔ እንደሆንክ ጹሑፍህን ያነበበ ሰው ያውቃል ተነቅቶብሃል

  2. @ ታምራት ይገዙ

    የደርግ አብዮት ጥበቃ ልጅ ና የመዒሶን ገራፊ ርዝራዥ ሁሉ ፃፊ ና ዜና አንባቢ ሆነ። ወዛደራዊነት ናፈቃችሁ አይደል። ድሮም ከናንተ ምን ይበቃል። ሁለትህም የታሪክ ዐተላ ነህ።እናንተ ብሎ ለሃገር ተቆቝሪ። የደርግ አብዮት ጠባቂ የእውቀት ድኩማን ሁሉ።ዝም ብሎ በባዶ G 7 ን ከመንቀፍ ኣንተ ወይ በሱዳን ፤ በጅቡቲ ፤ ወይ በሱማሌ የተሻለ ስራ መስራት ሚቻል ከሆነ ሰርቶ ማሳየት ነው። ሁሉም የ G 7 ሰዎች ዕንደኣንዳርጋቸው የሞቀ ቤታቸውን ጥለው ነው ኤርትራ በረሃ የገቡት።ግንቦት 7 ማለት ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ በ1997 EC ወያኔዎችን በድምፁ አንፈልጋችሁም ያለበት ታሪካዊ ቀን ነው። የነ ኤሊያስ ክፍሌ Ethiopian Review ወሬ ና ያንተ ኣይነቱ የውሸት ችርቻሮ ይህንን እውነታ አይለውጠውም።

  3. ታምራት ይገዙ ጽሁፍን አነበብኩት።
    ፋሲል የኔአለምን ሰው ብለህ የእርሱን ፎቶ መለጠፈህ አሳዘነኝ። ስለ G-7 የአሥመራን ምልልስ በተመለከ፤ ዘ ሃበሻ
    Shukshukta (ሹክሹክታ) – ሌንጮ ለታ ለምን አርበኞች ግንቦት 7ን ከዱ? | Lencho Leta Vs Dr Berhanu Nega የሚለዉን ድንቅ ትንታኔ አቅርባለን ነበር ….እባክህን እንደገና ይሄንን ከላይ ያስቀመጥኩትን “ሹክሹክታ” ጥሩ ቡናህን ይዘህ፤ ለስላሳ የ SUMMER ፀሀይን እየሞክ በጥሞና እንድታዳምጠው ጋብዥሃለሁ። እዉነታዉን ቁልጭ አደረጋ ሹክሹክታ አስቀምጣዋለችና ነው። ይሁነና ኢሣት ማለት የዲያስፖራው ETV ሲሆን ፡ ኤርሚያስ ለገሠ ደግሞ በቅርቡ “ፖለቲካችን” የሚል ፕሮግራም በ ኢሣት ሥር ሌላ ENN ከድሮው የደቦስኮ የEPRDF ምልምሉ ሃብታሙ አያሌው ጋር ይዞ በመቅረብ ETVን በዲያስፓራ እያስኮመኮሙን ነው ጆሮ አልሰማ አይል!። በተረፈ አቶ ዮሐንስ ለታ የአዎሮፓ ብርድ ሰለቼኝ ብሎ ወደ “እሚወዷት ሀገሩ ኢትዮጵያ” እየሄደ ፀሃይ እንደሚኮመኩመው ሁሉ የግንቦቴ አለቆች ደግሞ የ አሜሪካ tornadoes ወይም STORM ሲያዳፋቸው ወደ ኤርትራ እየሄዱ ከጥላሁን ገሠሠ መዚቃ ጋር የኤርትራን የሳህል በረሃ ፀሃይ ከዋና ጋር እንደሚጠጡት ማለት ነው። በተረፈ ፋሲል የእኔአለም ማለት ሌላው የኢሣት ተመሠገን በየን ማለት ነው። አበበ ገላው ዋናው ዳሬክተር ደግሞ የኢሣቱ ዘርዓይ አስገዶም ማለት ነው – አይፈረድባቸዉም። ሁሉም የኢሣት ጋዜጠኞች ማለት ይቻላል በETV ሠልጥነው፣ የETV የልማት ጋዜጠኞች የነበሩ፣ ነገር ግን በጥቃቃን ጥቅማ ጥቅም ከETV አለቆቻቸው ጋር ተኳርፈው ሲመጡ፤ ኢሣት እጁን ዘርገቶ የተቀበላቸው ናቸው። የ ETV ዋና አዛዡ የትግሬው ወያኔ ሲሆን፣ የ ኢሣት መሥራችና የንስሃ አባት ደግሞ ኢሣያስ አፈወርቂ ነው። እሳት ካዬው ምን ለዬው ይሉሃል እንዲህ ነው ታምራት ይገዙ

  4. ESAT = ERETRIAN SPY AGENCY TV

    CEO = GENERAL FITSUM

    OBJECTIVES FOR SHABIA

    -TALK ABOUT TPLF 24/7
    -SHOW ERETRIA AS A SAFE , HAPPY PLACE
    -SHOW SHABIA AS A DEMOCRAT
    -MAKE ETHIOPIANS WEAK BY INCITING VIOLENCE AND HATRED

    OBJECTIVES FOR G7

    MONEY , MONEY , MONEY $$$$$$$$$$$$

  5. የትጋ ነው የግንቦቲዎች ህዝባዊ ሀይል ያለው? ኦሮሞው በኦሮሞነት ፣ ሶማሌው በሱማሌነት ፤ አፋርሙ ፣ ትግሪውም ፤ ደቡቡም እንደዚሁ ። የአማርም አብዛኛው ወጣት በእማራ ነት መደራጀት የሚፈልገው ስለዚህ ግንቦት 7 ማን ነው የሚወክልው? በጨረቃ ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን?

  6. The writer (Mr. Yigezu) sounds a ‘TPLF Lmatawi Cadre’, illiterate though!

  7. ታምራት ምርጥ ትንታኔ አቅርበሃል ፣ 99% ትክክል ነህ ፣ በተጨማሪ ጳውሎስ የተባለው አስተያየት
    ሰጪ እንደጠቀሰው የዘሃበሻው ተወዳጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ ዓለማየሁ ቁልጭ ያለ ማብራሪያ ስለሰጠበት
    ብታዳምጠው መልካም ነው ! ሌላው ግንቦት 7 የተባለው የውሸት ድርጅት የኢትዮጵያ ብሄራዊ
    ባንድራ አስመራ ላይ የሻእቢያ ወታደሮች መሬት ለመሬት እየጎተቱ ሲያቃጥሉት ግንቦቴዎቹ እዚያው
    አስመራ ነበሩ ! ትንፍሽ አላሉም ! ኢሳት የተባለውም የግንቦት 7 ልሳን አንዲት ቃል አልተናገረም !
    ግንቦት 7 ለሻእቢያ ቦቆሎ መግዢያ በየሃገሩ እየዞሩ ከመለመን ውጪ አንዳች ፋይዳ ያለው ተግባር
    ይሰራል ብሎ ማሰብ ቂልነት ወይም የዋህነት ነው ! ፋሲል የኔዓለም ይህንን ቢል ምን ያስገርማል!
    ምክንያቱም “ውሻ በበላበት ይጮሃል” ይባል የለ ! ግንቦቴዎቹ በየደረሱበት ብቻ የትግራይ ነፍሰ
    ገዳዮችን ማውገዝ ነው ! እንደ ነአምን ዘለቀ ያለው በተለይ ሲደነፋና ትከሻውን ሲያሳብጥ ልክ
    ህወሃትን የደመሰሰና የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻ ያወጣ ይመስለዋል ! በዚህም የሻእቢያ ቀንደኛ
    ደጋፊና ጠበቃ ነው ! የግቦት 7 ደጋፊዎችና አሽቃባጮች በማይጨበጥና በማይዳሰስ ነገር ላይ
    ህሊናቸው እያወቀ ለምን ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር አምባ ጔሮ እንደሚያነሱ አላውቅም ! ግንቦት
    7ትን መቃወም የህወሃት ደጋፊ መሆን ነው ! የደጋፊዎቹ መፈክር !
    የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ እንደተባለው ! ግንቦት 7 የሚባል ነገር ከስም በስተቀር የለም @

    • @ አደባይ የዠማው

      ግንቦት ፯ ን ለመቃወም ያጠፋኸውን ጊዜ ምን ኣለ ወያኔ ላይ ብታደርገው። የ ኢትዮጵያ ባንዲራ ኣስመራ ተቃጠለ ተቀደደ ግንቦት ፯ ምንም ማድረግ ኣይችልም። ቢቃጠልም በግለሰብ ኤርትራውያን ዕንጂ ሻቢያ ስዕንደመንግስት ያበረታታው ወይም ያደረገው ኣይመስለኝም። ለምን በዚህ ጉዳይ ብልጣብልጥ ለመሆን ዕንደፈለክ ይታወቃል። ሰው በገዛ ሃገሩ የራሱን ባንዲራ ማቃጠል የሚችልበት ሀገር ዓሜሪካ ዕየኖርን ኣስመራ ላይ ያውም በግለሰቦች ለተሰራ ድርጊት መንጨርጨሩ ግብዝነት ነው። ኣሊያም ቀረርቶ መሆን ኣለበት። የዒትዮጵያ ትንሳዔ ቅርብ ነው። ያኔ የወያኔው ና የናንተ ዕጣ መቋጫ ያገኛል።

  8. ጥርሳቸውን በአማራ ጥላቻ የነቀሉ ፅንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከሁኔታዎች ጋር የሚገለባበጡ ከጥቅማቸው ውጪ ሌላ ነገር የማይታያቸው opportunist politician ናቸው። አብዛኛዎቹ የኦሮሞ ፅንፈኛ ፖለቲከኞች ወይም ልሂቃን በዋናነት የሚያመሳስላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ አለመረጋጋት፣ የፖለቲካ ነውጥ፣ ጦርነት ወይም ብጥብጥ ሲከሰትና መንግስት ሲዳከም ሁኔታውን ለእነሱ ከሚያስገኘው ጥቅም አንጻር መመልከታቸው ነው ።

    ለምሳሌ ከብዙ በጥቂቱ፦ (1). በ16 ኛው ክ.ዘመን የግራኝ አህመድን ወረራን ተከትሎ በጦርነት የማዕከላዊው መንግስት ሃይል ሲዳከም የኦሮሞ ጎሳዎች በየአቅጣጫው ወረራ በማድረግ መስፋፋታቸውና የባህል ተጽእኖ በመፍጠር በሞጋሳና በጉዲፈቻ ነባሩን ባለመሬቱን ህዝብ Oromized ማድረጋቸው።

    (2). በ1983 ዓ.ም ወያኔና ኦነግ የሽግግር መንግስት ሲመሰርቱ ከዛ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ ታሪክ ያልነበረ “ኦሮሚያ” የሚባል አዲስ ተሰምቶ የማይታወቅ ክልል ከዚህም ከዚያም መሬት በመንጠቅ ፈጠሩ። ኦነግ የመንግሥትን ለውጥ እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ በግርግር የማይገባቸውን ጥቅም ማግበስበስ ችሏል።

    (3). ቢያንስ በ1929 ዓ.ም 30 ሺህ በላይ የሚሆን የአማራ ህዝብ በፋሺስት ጣሊያን ደም ያፈሰሰባትን ሸዋ አዲስ አበባ (በረራ) የኛ ናት በሚል ሂሳብ ሲፋቁ ኦነግ የሆኑት የኦህዴድ ካድሬዎች ጨፌ ኦሮሚያ ተሰባስበው በአዲስ አበባ ላይ ኦሮሞ (ኦሮሚያ) ከሌላው ዜጋ በተለየ ሁኔታ “ልዩ ጥቅም” ይገባዋል የሚል ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅተው ለፌዴራል መንግስቱ ፓርላማ ለውይይትና ለውሳኔ ማቅረባቸው ማንነታቸውን ያሳያል።

    (4). የኦነግ መስራች የሆኑት ሌንጮ ለታ፣ ዶ/ር ዲማ ነገዎ እና ዶ/ር በያን አሶባ በአቋም ወይም በመርህ ሳይሆን በአካሄድ ከኦነግ ጋር በተፈጠረ ልዩነት ከኦነግ ወደ ኦዴግ በአንድ ፊደል ልዩነት እራሳቸውን በመለወጥ ዲያስፓራውን ሲያተራምሱት ከቆዩ በኋላ ከኦህዴድ ጋር በደባልነት ሃገር ሊመሩ፣ በ1983 ዓ.ም የጀመሩትን የክፋት መንገድ ሊያጠናቅቁ ወደ አዲስ አበባ አቀኑ።

    ፅንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከሁኔታዎች ጋር የሚገለባበጡ ከሚያገኙት advantage ውጪ ሌላ ነገር የማይታያቸው opportunist politician ናቸው። –//—

    ……………

Comments are closed.

Share