አበበ ቶላን ተው በሉት!!! (ከተማ ዋቅጅራ)

እሩአንዳ ለይ የአንድ አገር ዜጎች እንዲተላለቁ ትልቁን ድርሻ የያዙት ለፖለቲካ ትርፍና ለጥቅም የተገዙ ጥቂት ግለሰቦች  በሚያደርጉት ያልተገባ ንግግርና ቅስቀሳ ነው።
በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበሩ እድሜአቸው ከ7 እስከ 8 አመት የሚገመቱ ነበሩ። ዛሬ አንዱ ቤት ሄደው እየተጫወቱ ምሳቸውንም እራታቸውንም በልተው ሲመሽ ወደየቤታቸው ይሄዳሉ። በዚህ ሁኔታ ቤተሰብም ደስተኞች ነበሩ። ነገር ግን ከልጆቹ ወላጆች አንድኛው ክፉና ተንኮለኛ ነበረ። ልጆቹ እሱ ቤት መተው በሚውሉበት ግዜ ይሄንን ስራ ስሩና ምግብ እሰጣችኋለው ይላቸዋል እያለ ከባድ ስራ ያሰራቸው ነበረ። ስራውን ጨርሰው ጨርሰናል  ሲሉት ቆይ ምግቡ አልደረሰም ጠብቁ ይላቸዋል። ሲጠብቁም ይመሻል ማምሻው ለይ ግን ምግብ ያቀርብና እናንተ  ልጆች ናችሁ ዝም ብላቹ ቁጭ በሉና እኔ ለሁላችሁም አጎርሳችኋለው ይልና ለራሱና ለልጁ እያጎረሰ ለሌሎቹ  ልጆች እጃቸውንና አፋቸውን ወጥ ይቀባቸውና በቃ አሁን ወደቤት ሂዱ ይላቸዋል። ልጆቹም እቤት ሲሄዱ እራበን ብለው ይጠይቃሉ እንዴ ጓደኛችሁ ቤት በልታቹ የለ ተብለው ይወቀሱና የወላጅ አንጀት ነውና ልጅ ጠይቆ እንቢ ስለማይል ምግብ ይቀርብላቸውና ይበላሉ ሲበሉ ግን እንደበላ ሰው ሳይሆን እንደተራበ ነበረና ቤተሰብ በትዝብት ይከታተሉ ነበር። እንዲህ እያለ ብዙ ግዜዎች አለፈ። ከብዙ ግዜ በኋላ አንንድ ቀን ከመሃላቸው የአንዱ ቤተሰብ ልጅ ለአባቷ ትነግራቸዋለች ክፉው ወላጅ ቤት አምሽተው ሲመጡ እንደተለመደው አፋቸውና እጃቸው በወጥ ተነካክቷል እናም እራበን እራት ሲሉ ሁለት ቦታ ነው እራት የምትበሉት እንዴ እራት ደሞ ተጠግቦ አይበላም ብለው ወላጆች ሲቆጡ ህጻኗ ከአይኗ ለይ እንባዋ ዱብ ዱብ ይላል አባትም ምን ሆነሻል ንሪኝ ይሏታል ።ልጄ የሆነ ነገር ሳትሆን ህንዲህ እንባዋ አይፈስም ይላሉ። ልጅም መናገት ትጀምራለች። አባዬ ሁል ግዜ አቶ እከሌ ቤት ስንሄድ ስራ ያሰሩናል እንጂ ምግብ አይሰጡንም ብላ ታለቅሳለች። አባትም ታዲያ አፍሽ ለይ ያለው ወጥ እጅሽ ላይ ያለው ወጥ ከየት መጣ ይሏታል በእጃቸው እየነካኳት። አይ …. አይ …. አለች እንደማፈርም እንደመፍራትም እያለች። አባትም ንገሪኝ ልጄ አይዞሽ አሏት። ልጅም ጋሽ እከሌ እናንተ ልጅ ናችሁ እኔ ነው የማጎርሳችሁ ይሉና የቀረበውን ምግብ ሁሉንም እሱና ልጁ ይበላሉ ለኛ ግን አፋችንንና እጃችንን ወጥ ቀብቶ በቃችሁ ይለናል ብል በውስጣ የያዘችውን ነገረቻቸው ቤተሰቧም በጣም ይናደዱና በቁጣ ከዛሬ ጀምሮ እነሱ ቤት ድርሽ እንዳትዪ የሱንም ልጅ ቤቴ ይዘሽብኝ እንዳትመጪ ብለው ተናገሩ። ከዛም ለሁሉም ልጆች ወላጆች ይሄ ነገር ይነገራቸዋል ሁሉም ልጆች ክፉው ሰውዬ ቤተሰብ ጋር መሄድ አቆሙ። በኋላም ልጆቹ በሙሉ ከቤቱ መቅረቱን ሲያውቁ ለምን ከቤቴ ቀራችሁ ብሎ ለማናገርሁሉም ቤተሰብ ጋር ሲሄድ አንድ አይነት መልስ ይሰጠዋል። እኛ ልጅችንን ወደአንተ ቤት የምንልከው እኛ ቤት ሲመጡ እንደሚያረጉት ተጫውተውና ተደስተው እንዲመጡ ነው እንጂ እንደባርያ ልታሰራቸውና ወጥ ቀብተኋቸው እንድትልካቸው አይደለም ከአሁን በኋላ የኛም ልጆች እናንተ ቤት አይመጡም ያንተም ልጅ እኛ ቤት እንዳትመጣ ብለው ይነግሩታል።
እናም አበበ ቶላ ይሄ ነገር ቢደርሰው  የሚፈርደው ፍርድ እንደዚህ ነው።
እንዴ ምን ይላሉ እነዚህ የግድ ጸቡን ቤተሰብ ለቤተሰብ ለማጋጨት ባንጠቀምበት ጥሩ ነው ጸቡ የልጆች ስለሆነ እዛው ልጆቹጋር ማለቅ ሲገባው ወደ ቤተሰብ አምጥቶ ቤተሰብንና ቤተሰብን ማጋጨት እንደአገር አሳፋሪ ነው ኧረ ጎበዝ ይቺ አገር ወዴት እየሄደች ነው የልጆችን ጸብ ወደቤተሰብ ከወሰድነው እደአገር አሳሳቢ ነው። እንደው ሰው ለፍርድ እንዲያመቸው የጸቡን መነሻ የሆነውን በልተዋል አልበሉም የሚለውን እንዲረዳው። “ፎቶውን ለጥፎ”  አሁን እነዚህ ህጻናት አፋቸው ለይ ያለው ምግብ ከየት መጣ እጃቸው ላይ ያለውስ ወጥ ከየት መጣ ተሰብስበው ስልቅጥ አድርገው ከጨረሱ በኋላ አልበላሁም ማለት አይቻልም። እነዚህ ህጻናትን በደንብ እንዲቀጡ ምግብ የሌለበት ክፍል ውስጥ ከርችማ ማሰር ነበር። የሚል ፍርድ ይፈርድ ነበር።
ከዛም የሚሰጠውን አስተያየት ማንበብ ነው። እውነትን በማዛባት የሚደረጉ ነገሮች ችግርን ወደበለጠ አደገኛነት ያሸጋግረዋል እንጂ አያረግበውም።
ሲጀመር ጋዜጠኛ ነኝ የህዝብን ብሶትና እውነተኛ ነገሮችን በትክክል ያለ አድሎ እዘግባለው የምትል ይመስለኝ ነበረ። ምክንያቱም የጋዜጠኛ ተግባር ይሄ ስለሆነ። በፌስ ቡክ ላይ ብዙ ህውአት ያዘመታቸው ዘርንና ዘርን የሚያዛጩ ቢኖርም ላንተ መመለስ ያስፈለገኝ ከነበረህ የሙያ ስነምግባር ዘንድ ይወረድክ ስለሆነ ለማስታወስ ነው። ህውአትን በስልጣን ለማቆየት በሚያደርጉት ህዝብን የመዝለፍ ስራ አብሮ የመኖርን ግንኙነት እስከመጨረሻው የሚለያይ ነውና ቆም ተብሎ ማሰበ መልካም ነው እላለው።  ጠላትንቱን በግድ ማህበረሰብ ውስጥ ካስገባነው መመለሻው እንዳያጥረን እንደነ አበበ ያላቹ የሚዲያ ሰዋች ሰከን ብትሉ ጥሩ ነው በኋላ ለሚፈጠረው አደጋ ተጠያቂነትን ሊኖር ስለሚችል። ስጋ ስትበላው መጣፈጥ ብቻ ሳይሆን አንቆም እስከመጨረሻው እንደሚያሰናብት ማወቁ መልካም ነው። የኪሳችንን ነገር እንዳይጎልብን ብለን  ህብረሰብን ማጋጨት ይቁም።
እበበ ባነሳሃቸው ሃሳቦች ላይ ከስር ህዝቡ የሚሰጥህን መልስ ትመለከተዋለህን? በዚህ ንትርክ መሃል ለይ በ1000 የሚቆጠረው ህዝብ ከዛም በአስር ሺ የሚቆጠረው ህዝብ እያለ አጠቃላዩ ወደራሱ ዘር በመግባት ከዘሩ ውጪ እንድያይ በመሆን ለትግል እደሚነሳና የከፋ አደጋ እንደሚመጣ ስለምን መረዳት ተሳነን። ህውአት በዘራቸው ሲደራጁ ሰባት ነበሩ ዛሬ የት እንደደረሱ መቼም አይነገርህም ታድያ ዛሬስ ሌላው የማይደራጅበትና ጠላት ያለውን ማህበረሰብ ማጥፋት የማይችልበት ነገር ያለ ይመስልሃልን?  ሃረጉን ስትመዘው አጥሩ ይነቃነቃል ነውና የዘረኝነት ርእስ እየፈጠራችሁ ህዝ ወደከፋ ነገር ባታስገቡት መልካም ነው እላለው።
የጋዜጠኛነት ሙያ በዳይንና ተበዳይን ቀርበህ በማናገር የሁለቱንም ሃሳብ በማቅረብ ህዝብ እንዲያውቀው ያደርጋል እንጂ የአንዱን ሃሳብ በማጉላት የሌላውን ማንኳሰስ ህዝብን ወደቁጣ ያመረዋል እንጂ የሚፈይደው ነገር የለምና በዚህ ስራ ለይ የተሰማራችሁ የፌስቡክ ቤንዝን እና ክብሪቶች በዛች አገር ላይ በሚፈጠረው አደጋ ስልጣን ላይ ካለው አካል ጋር ተጠያቂ እንደምትሆኑ በማወቅ ከድርጊታችሁ ብትቆጠቡ መልካም ነው። ደራሲው ብቻ ሳይሆን ተዋናዮችም ተከፋይ ናቸውና።
የተጀመረውን የአንድነትና የፍቅር ጉዞ የሚያዳክም ነውና በፍጥነት በዚህ ስራ ለይ የተሰማራችሁ ወንድም አበበ እንዲሁም ሌሎች ግለሰቦች አደብ ብትገዙ መልካም ነው። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ አለበለዛ ድንጋይ ነህ ተብለህ ትጣላለህ ነውና ነገሩ።
ከተማ ዋቅጅራ
 09.05.2018
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከአማራ ቆዳ በተሠራ ከበሮ: ጭፋሮ !! (አሥራደው ከፈረንሳይ)

1 Comment

  1. እውነት ብለሃል ወንድሜ፣ አበበ ቶላ “አወቅሽ_አወቅሽ ቢሏት የባሏን መጽሃፍ አጠበች” እንደተባለው
    ብሂል ያቤ ነገር ጥሩ አይደለም!

Comments are closed.

Share