April 23, 2018
21 mins read

የአማራን መደራጀት የሚያማቸው የኢትዮጵያን ትንሣኤ የማይሹ ፀረ – ኢትዮጵያ ሃይሎች ናቸው! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

ሓያረ ጠንለሱ

አማራና ተደራጅቶ እራሱን ከገዳዮቹ ይመክታል። አባቶቹ በደም በአጥንታቸው ያቆዩአትን ኢትዮጰያንና ኢትዮጵያዊነት ነብስ ይዘራበታል።

የኢትዮጵያን አንድነት ለማፍረስ በትህነግ-ወያኔ የተቀየሰውና በበታችነት ስሜትና በፈጠራ ትርክት ናላቸው የዞረ የጎሣ ፖለቲከኞች ድጋፍ የተቸረው “የጎሣ ፌደራሊዝም” በደደቢት በረሃ የተጠነሰሰው አማራን ቀንደኛ ጠላቱ በማድረግ ነው።

በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ዜግነት፤ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ክብር አለ:: በአማራ ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያዊነት እየተጠቀምን በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያለውን አማራነት እያዳፈንን ኢትዮጵያዊነትን ማለም አንችልም:: አማራነትን ለፖለቲካ ፍጆታ/Political consumption/ እና ፖለቲካዊ ትክክለኛነት/Political correctness/ አገልግሎት እየተጠቀምንና በተንሸዋረረ ዓይን እያየን ስለኢትዮዽያዊነት ማሠቡና መነዛነዙ ቀልድም ነው::

አማራ የሚለውም ኢትዮጵያዊ ስሙ ተነጥቆና ተንኳሶ አማራ ነው ስምህ ተብሎ ዛሬ በኮሪደር ተገድቦ የሚንገላታውን የህዝብ ስብስብ ነው:: ለነፃነቱ በከፈለው ዋጋና ሃገሩ ኢትዮጵያን በማቆሙና ክብሩን ያለመደራደሩ ወንጀል ሆኖ ዛሬ በባንዳዎችና ከሃዲ ውላጆች እንዲሁም በጎሣ ፖለቲከኞች የሚቀጣ ህዝብ ነው:: ከኢትዮጵያዊነቱ ውስጥ አማራነቱ፤ ከአማራነቱም ውስጥ ኢትዮጵያዊነቱ ተዘርፎ ወራሪን ባርበደበትና ድል በነሣበት በሃገሩ የኢትዮጵያ መሬት ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ በባንዳዎችና በሹምባሾች አዎን ዛሬ ይሸማቀቃል:: ይሰደዳል። ይገደላል። አዎን ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ሁሉ አማራ ተብሎ ከተፈረጀ ከ27 ዓመት በላይ ሆነ:: በተለይ አማርኛ ብቻ ተናጋሪ አማራ ተለይቶ አማርኛን በደባልነት በመናገራቸው አማራ ሆነውና አማራ-ኢትዮጵያዊ መስለውና የአማራ ለምድ ተላብሰው ወያኔ ሠራሹን አሻንጉሊት “የአማራ ድርጅት-ብአዴን” የተሠኘ ስም ጭነው ከከሃዲው ወያኔ ጋር በመሆን ጀግናውን የኢትዮጵያ ልጅ በአማራ ስም ሲገፉት፣ ሲያስሩት፣ ሲገድሉት፣ ሲያስገድሉትና ከቀዔው ሲያፈናቅሉት ይስተዋላል:: እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች አማራውን በመግደል ኢትዮጵያዊነትን የሚሽሩና ኢትዮጵያን የሚንዱ እየመሰላቸው ጥፋታቸውን ተያይዘውታል::

ኢትዮጵያዊነትን ያለ አማራ ማሠብ ውሃን ያለ ሃይድሮጅን ውሁድነት በኦክሲጅን ብቻ ለማምጣት መመኘት ነው:: አማራን ማጥፋት ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ ማጥፋት ነው:: ይህ ህልም ብቻ ሣይሆን የቀን ቅዠት/daydreaming/ ነው:: ኢትዮጵያዊነት አማራነት፤ አማራነትም ኢትዮጵያዊነት ነው:: ምክንያቱም ሁሉም ኢትዮጵያዊ አማራ፤ ሁሉም አማራ ኢትዮጵያዊ ነው:: ኢትዮጵያዊነት አንድነት በፍቅር ተሳስቦና ተፋቅሮ መኖር ነው::
ኢትዮጵያ የህዝቧ እንጂ የገዢዎቿ ንብረት አይደለችም:: ግፈኛ ገዢዎቿ በጊዜ ይወገዳሉ:: ኢትዮጵያ ግን ትቀጥላለች:: ቀጥላለችም:: ኢትዮጵያ ያለ ግፈኛ መሪዎቿ ኖራለች:: ትኖራለችም:: ነገር ግን ግፈኛ መሪዎቿም ሆኑ የግፍ ሠለባ የሆኑ ልጆቿ ያለ ኢትዮጵያ የሉም:: ለዚህ ነው ፖለቲካዊ ስርዐትና ሃገር አይደበላለቁ የምንለው:: ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከአማራ፤ አማራም ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ከደምና አጥንት ተሰርቷል:: ጥንት በጣሊያንና ሌሎች ወራሪዎች ይሁን ዛሬም በወያኔ ከሃዲና ባንዳዎች ስሌትም ኢትዮጵያዊነትን መዘከር አማራነት ነው በሚል እሣቤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አማራን ማጥፋት ከወራሪ ጣሊያን የቀሰሙት የስትራቴጃቸው ዋነኛ ቀመር ነው:: አማራን ማጥፋትም ኢትዮጵያን ማክሠም/cease to exist/ነው:: ኢትዮጵያዊነት እነርሱ አማራ ብለው የፈረጁት ህዝብ ብቻ አይደለም:: የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ንብረት እንጂ:: ዛሬም የህወሃት ወራሪዎች ከሃዲና ባንዳዎች ልክ እንደ ጥንቱ ጣሊያንና ሌሎች ወራሪዎች ኢትዮጵያን በመዳፋቸው አድርገው የልጆቿብ ደም በዋግምት ለመመጥመጥ በግንባር ቀደም ጠላትነት ፈርጀው የመጡት አማራ ኢትዮጵያዊውን ነው:: አማራም ብለው የሣሉት ኢትዮጵያዊነትን የሚያወድሠውንና ለአንድነቷና ክብሯ በባለቤትነት የቆመውን ኢትዮጵያዊን ነው:: ህወሃቶች እንድ አንበጣ መንጋ የወረሩት መላው ኢትዮጵያን ረግጠው የሚገዙትም ሁሉን ኢትዮጵያዊ ነው:: ለዚህ ነው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚመክቱትን ኢትዮጵያውያን ሁሉ በአማራነት የሚፈረጁት:: ጣሊያንም ቀመሩ ይህ ነበር። ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊነት አማራነት፤ አማራነትም ኢትዮጵያዊነት ነው የምንለው:: አማራነት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ፤ ኢትዮጵያዊነትም የአማራ ክብር ነው:: ኢትዮጵያውያንም ለሃገራቸው ኢትዮጵያ ማገርና ምሰሶም ናቸው:: የጨቋኝ ስርዐት ግፍና በደል ሠለባነት እንጂ የኢትዮጵያ ዜግነት አድልዎና ችግር የለባቸውም:: ትግላችንም ኢትዮጵያን የአማራ ወይም ያንዱ ጎሣ ለማድረግ ሣይሆን ኢትዮጵያን የኢትዮጵያውያን ሁሉ ለማድረግ ብቻ ነው:: ኢትዮጵያም የአማራ ሣይሆን የገዢዎቿ ንብረት ነበረች። አሁንም ናት። ለዚህ ማረጋገጫው ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩበት፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚኖርበት፣ የእምነት ነፃነት የሰፈነበት፣ የግለሰቦች ያልተገደበ መብትና ነፃነት የሚፀናበት፣ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት የነገሠበትና ሠዎች ለሕግ እንጂ ሕግ ለሠዎች የማይገዙበት ዲሞክራሲያዊ ስርዐት ምስረታ ብቻ ነው::

አማሮች ለምንና በማን ይገደላሉ?

በያዝነውም ዘመን ልክ እንደ ጣሊያን ወራሪዎች ኢትዮጵያዊነት እንዲያከትም ኢትዮጵያም እንድትበተን ዋነኛው የኢትዮጵያ ጋሻ አማራ ነውና ይህን አማራ ማጥፋት የሚል መርሃ ግብር ተግብሮ የሚንቀሣቀሰው በዋናነት ወያኔ ነው:: ወያኔም ለዓላማው መሣካት ከሻዕቢያ ጥንት የወረሠውንና በጊዜ የማይለወጠውን ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ትርክት አንግቦ ይህንንም የፈጠራ ትርክት ለአክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች አሸክሞና አከፋፍሎ፤ እነርሱንም እየነዳ በአማራ ላይ ታሪክ የመዘገበው ጅምላ ጭፍጨፋ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተግብሯል:: እየተገበረም ነው:: የጣሊያኖችና ወያኔዎች ትርክት ሰለባዎችን አደራጅቶ በበደኖ፣ በአርባጉጉ፣ በጉራፈርዳ በቅርቡም በኢሊባቡርና በቤኒሻንጉል ንፁሃን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ አሣርዷል:: ግድያውን የሚተገብረው በአካባቢው ጎሣዎች ሣይሆን ከጎሣው ውስጥ በመለመላቸው ቅጥረኞችና ፀረ-ኢትዮጵያ ግለሰቦችን በመጠቀም ነው:: ይህም ግድያ ጎሣዎችን እርስ በርስ ለማጋጨትና ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከም ሆን ተብሎ በተጠና መንገድ የሚከናወን የዘር ፍጅት/genocide/ ጥንስስም ነው:: አማራ ለሃገሩ ኢትዮጵያ እንጂ ለራሱ ኖሮም ሞቶም አያውቅም:: ዛሬም የሚገደለው እጥብቆ ለያዘው ኢትዮጵያዊነት ማህተሙና ማተቡ ብቻ ነው:: ዛሬም እንደትላንቱ የሚገፉትና የሚገድሉት ባንዳዎችና ሹምባሾቻቸው ናቸው:: ዛሬም የሚገደለውና የሚሠደደው “በጎሣ ፌደራሊዝም” ስም ነው:: ዛሬም የሚሞተው ለኢትዮጵያዊነቱ ነው:: ፈጣሪ ታማኝነቱንና ትዕዛዙን መፈፀሙን ለማረጋገጥ አብርሃምን ልጁን ይስሃቅን ለመስዋትነት እንዲያቀርብ አዘዘው:: አብርሃምም የፈጣረውን ትዕዛዝ በማክበር ልጁ ይስሃቅን ለመስዋትነት አቀረበው:: የትዕዛዙን መከበር ያረጋገጠው ፈጣሪም የይስሃቅን መስዋዕት በበግ ተክቶት የይስሃቅን ህይወት ታደገው:: በአንፃሩም ፋሺስቱ ወያኔም ለይስሙላ የጎሣ ፌዴሬሽኑ ጠላት አድርጎ የፈረጀውን አማራ በየአቅጣጫው ለጭዳነት አቀረበው:: ልቡ የተደፈነ አረመኔም ነውና መስዋዕቱን በበግ መተካት ይቅርና እራሱን አማራን አረደው:: ዛሬም እያረደውና በትዕዛዙ እያሣረደው ነው:: ፈጣሪ ወያኔ አይደለም:: አማራም ከእንግዲህ ልጆቹን ለመስዋዕትነት እንደ አብርሀም አያቀርብም:: የመስዋዕት በግም አይደለም:: በልጆቹ ደም ህልውናው ያብባል።

ምን መደረግ አለበት?

ዝንጀሮ ‘መጀመሪያ የመቀመጫዬን ንቀሉልኝ’ ብላለች። ሌላው ዕዳው ገብስ ነው።

የህወሃት ወያኔ ሽፍታዎች ለማጥፋት የተነሱት ኢትዮጵያዊነትን የሚያወድሠውንና ለአንድነቷና ክብሯ የቆመውን ኢትዮጵያዊን ነው:: ይህን ስብስብ አማራ ወይም ነፍጠኛ በሚል ስያሜ ስር አነጣጥረውበታል:: እየተኮሱበትም ነው:: ከእንግዲህ ሞትን ወደ ገዳዮች መንደር መውሰድ እንጂ ቆሞ አይጠብቀውም:: ከእንግዲህ ሞትን ሞቶ አይጠብቅም:: የሚነደውንና የሚመጣውን እሳት ለማጥፋት ያልተቀጣጠለውን መለኮስ እሳትን በእሳት ማጥፋት የሚያስችል ብልህነትና ጥበብና የተላበሰ ብቸኛ ምርጫም ነው:: ለዚህም የአማራ-ኢትዮጵያዊ መደራጀት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው:: ኢትዮጵያ ሃገራችን በደም ከመዋዠቅ የሚያድናት መፍትሄም ነው:: አማራነት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያቀፈ የመከላከል ሃይል ነው:: የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትንሣኤ ጎህ ቀዳጅ ነው::

የአማራው መደራጀት የወያኔን ‘ዳሞክራሲያዊ ብሄረተኝነትን’ በታኝ ሃሳባዊ ቅዠት የሚጋራ ሣይሆን ይልቁንም የሚያመክንና/debunking/ለኢትዮጵያ ምፅዓትና ልዕልና መኖር ዋስትና ነው:: ህብረ-ብሄራዊነትን ለማጠናከር ምድር ላይ ያለውን አደረጃጀት ‘የወያኔን ሠርዶ ባገሩ በሬ’ ለማክሰም እንደ አንድ ግብዓት የሚታይ እንዲሁም ህብረ-ብሄራዊት ኢትዮጵያን ለማዳን ሲባል ‘ጎባጣን ለመምሰል ጎብጦ መሄድ ወይም ሮም ስትኖር ሮማውያንን ምሰል’ ዓይነት በሣልና ወቅታዊውን እውነታ ጋር የተጋባ አማራጭ የሊለውም ፖለቲካዊ ስልት ነው:: አማራው በኢትዮጵይዊነቱ ውስጥ ያለውን አማራነት ይምዘዝና ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ሳንጃውን ይወድር ማለት ነው:: አማራው ተደራጅቶና ሌሎች ኢትዮጵያውይንን አደራጅቶና አካቶ ልክ የጣሊያን ወራሪን ድል እንደነሣ ባንዳ ወያኔዎችን ወደ ትቢያ ያሽቀንጥር ማለት ነው::

አማራው በኢትዮጵያዊነቱ ውስጥ ያለውን አማራነት መዞ ለኢትዮጵያ አንድነት እስካዋለው ድረስ በአማራነቱ ተደራጅቶ እንደ ጭዳ በግ በየሜዳው ከሚያርዱት ገዳዮቹ እራሱን መጠበቁና መታደጉና ኢትዮጵያን ከእፍራሾቿና ተላላኪ የውስጥ አርበኞች/fifth column/ መመከቱና መከላከሉ ችግሩ ምንድነው? ይህን አደረጃጀት መቃወምና ማብጠልጠል ‘አያድን ጋሻ ቂጥ አስወጊነትም’ ነው:: አማራ በአማራነቱ መደራጀቱ ኢትዮጵያን ለምንል ኢትዮጵያውያን መጨረሻው ከዘር አባዜ የፀዳ ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩበት: ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚኖርበት፣ የእምነት ነፃነት የሰፈነበት፣ የግለሰቦች ያልተገደበ መብትና ነፃነት የሚፀናበት፣ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት የነገሠበትና ሠዎች ለሕግ እንጂ ሕግ ለሠዎች የማይገዙበት ዲሞክራሲያዊ ስርዐት ምስረታ ዋስትና ነው::

አማራ በአማራነት ከተደራጀ የኢትዮጵያን አንድነት አደጋ ላይ ይጥላል የሚለው ምድር ላይ ካለው እውነታ በብዙ ሺ ኪሎሜትሮች ያፈነገጠ ግዙፍ ስህተት ነው:: ይህ ‘ለቀባሪው አረዱት’ ነው። የገዳዮቹን የሞት ድግስ እንዲቀበልና የሞት ፅዋ በቁሙ እንዲቀበል መምከር ነው:: ፖለቲካዊ እጥፍ ዘርጋ ዥዋዥዌ /Political seesawing/ አጭር ግቦችን ለማሳካት በጊዜያዊነት ቢያገለግልም በዘላቂነት ከያዙትና ከተጣበቁበት ያጭር ጊዜ ስልት መሆኑ ይቀርና የመጨረሻውን ግብ ለድርድርና ለክለሣ የሚያቀርብ አድርባይነት/opportunism/ ይሆናል:: ይህ ትርክትና የፖለቲካ ትክክለኛነት ስሌት ከትርፉ ይልቅ ኪሣራው ያመዘነ፤ ያልተገመተ ወይም ያልተጠበቀ መዘዝን/unintended consequences/ ያላገናዘበ ፖለቲካዊ ብዥታም ነው:: ህዝባዊና ሃገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለ ህዝባዊ ይሁንታና ተወካይነትና ያለዲሞክራሲያዊ አግባብም በድርጅቶች መሃል የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ፖለቲካዊ ስምምነትና ፈቃድ/concession/ፖለቲካዊ ጥበብ ሣይሆን ፖለቲካዊ አሻጥር/Political intrigue/ ነው:: በተፈጥሮውም ፀረ- ዲሞክራሲያዊ አካሄድም ነው:: ለምሳሌ በህብረብሄራዊነት የተደራጁ ቡድኖች የጎሣ ድርጅት ስብስቦች መሆናቸውን ልብ እንበል።

ባጭሩ አማራዊ እና ህብረ-ብሄራዊ አደረጃጀት የሚጣረሡ ሳይሆን የሚደጋገፉና የሚመጋገቡ/symbiotic & obligatory/ ግባቸው አንድና ኢትዮጵያም ነው:: ልብ እንበል:: ጠላት እያሣደደ የሚያጠቃው አማራነት በራሱ ኢትዮጵያዊነት ነው:: አማራነት ልክ እንደ አይሁድነት የአንድነት ምልክት ነው:: እራሱን ከአጥፊዎቹም ለመከላከል ሲደራጅ ከማንም ፈቃድ መጠየቅም የለበትም። ከአማራው ይልቅ ኢትዮጵያዊነትን አማራው ለማዳን በሚያደርገው ተጋድሎ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ደስታቸው ነው። ከጎኑም መቆም ታሪካዊ ሃላፊነታቸው ነው። ጥንትም የሆነው ይህ ነው።

አማራዊ አደረጃጀት የአማራን መጋዝና ሞትን ይታደጋል:: የአማራ መደራጀት የኢትዮጵያን መኖር ያረጋግጣል::
አማራ ከእንግዲህ የአብርሃም በግ አይሆንም እራሱን ያደራጃል:: አማራነት እራሱንና ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን ይታደጋል::
አማራነት ኢትዮጵያዊነት ነው:: ኢትዮጵያዊ- አማራነት በድርጅታዊ ክህሎቱ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ዛሬም እንደ ትላንቱ ያበስራል::

አዎን! እሾክን በእሾክ ነውና አዎ አማራ ይደራጃል::

4 Comments

  1. Oromoo nationalism or Oromuuma is the core  values and ingredients of the Oromo struggles for social, economic, cultural and  democratic rights, freedom and prosperity. The Oromo nationalism is against the inhuman systems  of Minilik, Haile Selassie, Mengistu Hailemariam and that of Meles Zenawi and those who have been trying to defend those dark eras. But it is not against no nations and no peoples of Ethiopia. Oromo nationalism promotes mutual understanding among nations and nationalities of Ethiopia, especially between the Oromo and Amhara nations. Abiy Ahmed is a product of the Oromo struggles. The main source of his  political power is the Oromo people in general and the Qeerroo  in particular, but not his personal merits. Dr. Abiy knows all these more than any body might do it.

    The current spearhead of the Oromo struggles is the Qubee generations or QEERROO, but not Abiy Ahmed and Lemma Megerssa. These two heroes of the nation are tasked  to implement the roadmaps of the freedom which are worked out by the Qubee generations. The main sources of the political powers of Abiy Ahmed and Lemma Megerssa are the struggles of the Oromo nation in general and that of the QERROOS in particular. Dr. Abiy Ahmed is the Primeminster of all Ethiopians. But don’t forget he is the son of the Oromo nation.

    No one has disowned the ethnic background of Mengesitu, Haile Selassie, Gobana Datche, the Hitler of Africa and other Anti-Oromo and Oromummaa elements. If you can claim that Meles Zenawi himself is an Oromo, it is okay. In general, we have no problem with the ethnic background of an individual or a group of individuals. What matters most is their psychological makeup and stands on the basic human rights and the systems which they have served. That means, it doesn’t matter from which ethnic background they were or are.

    The struggle of the Oromo nation is not against the Amahara and the Tigre peoples. It is only against subjugation and exploitation, discrimination and forcibly imposed assimilation.

    We believe the Oromo nation is the pillar of peace, stability, security and prosperity of the Horn of Africa. You should have to accept these facts and work with us so that we can promote together mutual understanding and respect. It is up to you if you think rationally and adjust yourself with the realities  of this time instead of dreaming the golden time of the eradicated old past eras. By negotiating we can build a multinational federal states of Ethiopia at the best interests of all nations in Ethiopia.

    Narrow nationalists are those who are against the democratic rights of the differet nations in Ethiopia. They have been using always derogatory terminologies in order to undermine the demands of the Oromo nation. Those individuals are desperate and hopeless. No more business as a usual.

  2. To ሓያረ ጠንለሱ

    You are comparing apples and oranges man. You have to select only one of them. You can’t have it both ways. Either you are Ethiopian or not. All nations equally contributed to Ethiopian nationalism and defended this country for thousands of years. There is no reason Amharas should take the burden of keeping ths country together or have special place in Ethiopia. የዞረብህ ትመስላለህ:: ሆድ አደር አማራ የወያኔ አሽከር:: ወያኔ ወያኔ ትሸታለህ። ከኣህያ የዋለ ምን ተምሮ ይመጣል ዕንደሚባለው ነው።

  3. @ሓያረ ጠንለሱ

    You are comparing apples and oranges man. You have to select only one of them. You can’t have it both ways. Either you are Ethiopian or not. All nations equally contributed to Ethiopian nationalism and defended this country for thousands of years. There is no reason Amharas should take the burden of keeping ths country together or have special place in Ethiopia. የዞረብህ ትመስላለህ:: ሆድ አደር አማራ የወያኔ አሽከር:: ወያኔ ወያኔ ትሸታለህ። ከኣህያ የዋለ ምን ተምሮ ይመጣል ዕንደሚባለው ነው።

  4. Amaras have endured the most gruesome atrocities for at least four decades under the guise of socialism and now the naked Tigreean fascism that has declared their annihilation as its primary national project.

    Amaras do not need anybody’ s approval to stand up together and speak in unison. Amaras are can speak every language its adversaries choose to speak. The belated emergence of Amara awakening had to do with the inexhaustible Amara patience. Amaras tolerated their own brutalization at the hands of lowly and inferior breed of men who more than anything else are angry that they lack the noble Amara traits, justice, fairness, patriotism and love for everything Ethiopian. It is seemingly impossible to live decently among beasts without duly equipping oneself with the right defensive gears. The Amara movement is here to stay. It is founded on a solid foundation to withstand any force from within and out.

Comments are closed.

Previous Story

በዘረኝነት=ብሔረተኝነት ልክፍት ስለተያዝን እንደወረድን አይገባንም! – ሰርፀ ደስታ

Next Story

ከታሪክ ማህደር – አገሬ አዲስ

Latest from Blog

blank

አርበኛ አስረስ ማረ እና ምርኮኞቹ | ስለ ፋኖ የብሔራዊ ባንክ ገዥው ያልተጠበቀ ንግግር |

#ሰበር_ዜና #AmharaFano ➢መሰከረም 29/01/2017 ዓ.ምብዙ ድሎችን አግኝተናል፣➢1️⃣115 ምርኮኛ ➢2️⃣70 እስረኞችን አስለቅቀናል➢3️⃣ 7 ብሬን➢4️⃣2 ድሽቃ➢5️⃣ 4 ስናይፐሮችን➢ለትግል የሚጠቅሙ የነፍስ ወከፍ ክላሾችንተተኳሾችን መኪኖችም ገቢ… pic.twitter.com/GbYaOAtFtr — ትዝብቱ🔔 (@Geteriew1) October 12, 2024 በፋኖ የተማረኩት ኮሎኔል
blank

ትግሉ ይጥራ – ከጥሩነህ ግርማ

የህልውና ትግሉን ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለማሸጋገር የኦይዶሎጂ ብዥታን ማጥራትና በመሬት ላይ ያለውን ተንኮል መጋፈጥና ማፅዳት ያስፈልጋል የህልውና ትግሉ በአማራ ብሄርተኝነት ላይ ያጠነጠነ እንደመሆኑ የመኖር አለዚያም እንደ ህዝብ  የመጥፋት ትግል ነው: ሌላው ኢትዮዽያዊ ወገን
blank

የፋሽስቱ አብይ አህመድ አሊ ኢትዮጵያ ውስጥ በአማራ ላይ እየተካሄደ ስለሚገኘው ጦርነት ከመስከረም 13 እስከ 27/2017 ዓ.ም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የደረሰ የጉዳት !!!መረጃ:

ሸዋ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት መርሀቤቴ አውራጃ በደራ ወረዳ ልዩ ስሙ ኮሉ በተባለ አካባቢ ላይ በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ አሸባሪው የሸኔ ቡድን ከኦሆዴዱ ጥምር ጦር ጋር ቅንጅት በመፈጠር መስከረም 22 ቀን 2017ዒ.ም ከለሊቱ
Go toTop