ማህደረ ወልቃይትን በወፍ በረር  (መስቀሉ አየለ)

ወልቃይት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በወገራ አውራጃ ውስጥ የነበረ ወረዳ ሲሆን ከተማውም አዲረመጥ ይሰኛል። በወልቃይት እና በትግራይ መካከል ያለው የተፈጥሮ ድንበር የተከዜ ወንዝን የተከተለ ሲሆን በውስጡ ከአማራዎች በተጨመማሪ ደግሞ እስከ አስራዘጠኝ አርባ አከባቢ ድረስ በጣም ውስን የሆኑ ቤተእስራኤልውያን፣ አገዎችና ሴሜቲክ ያልሆኑ የጉምዝ ተወላጆች ይኖሩበት እንደነበር ፍንጭ መስጠቱ እንድሁም በዚሁ በወልቃይት ውስጥ የተገኙት ዘመን ጠገብ የፈራርሱ የጥንት የእስላም የቀብር ስፍራዎች የሚያሳዩት በአንድ ወቅት በዚህ ቦታ ይኖሩ የነበሩት ጉምዝን የመሳሰሉት አናሳ ብሄሮች በእስልምና ተጽእኖ ስር ወድቀው የነበረ ሲሆን እንደ ጤዛ ብቅ ብሎ በሂደት መዳከም የጀመረው የማዛጋ የእስላም አስተዳደርን መዳከም ተከትሎ የእስልምናውም ተጽእኖ አብሮ እንደከሰመ ማየት ይቻላል (Ibid 115 )። ክርስትና ዳግም በወልቃይት በብዛት እንዲሰርጽ የተደረገው የአውስታቲዎስ ደቀመዘሙር በነበሩት ታዋቂውና አይናማው አቡነ ገብረ ናዝራዊ እንደሆን ይነገራል።መሃሉ በተናጋና በጠነከረ ቁጥር ሲጠብቅና ሲላላ በኖረው ወደዚህ የወልቃይት ጠረፋማ አካባቢ የነገስታቱ አሻራ እንደገና የገባው አጼ በእደማርያም ጠለምትንና ደምቢያን ከያዘ ቦሃላ ነበር ማለት ይቻላል።

ወልቃይት በአስራ ሰባተኛው ክፍለዘመን መጀመሪያ ላይ ከበጌምድር ተገንጥሎና እራሱን ችሎ የራስ ዳግና ወራሽ በሆኑት ደጃዝማች አያና እግዚ ስር ሲተዳድር ቆኦይቷል።አጼ ዮቶስ በደጃዝማች አያና እግዚ በተደረገላቸው መልካም ፈቃድ ወልቃይት ውስጥ ለተወሰነ አመታት ተጠልለው የቆዩ ሲሆን ነገር ግን በንጉስ ዳዊት ሶስተኛ እንደገና ወደ ጎንደር ተግዘው ሄደው በዲንጋይ ተወግረው ሞተዋል(DombrChr 264f. and no. 793; cp. BudHist 440f.;BruNile II, 568f., 579f.)። ( ድንቁርና ደፋር ያደረጋቸው “የደደቢት ደደቦች” ደጃዝማቹን ትግሬ ናቸው እያሉ እንደሚቀጥፉ ይሰማል። ደጃዝማቹ ትግሬ ሳይሆኑ ከቀደምት የአክሱም አማራ ነገስታት መጠሪያዎች አንዱ የዘር ግንድ ከሆነው ድግናንጃን ፣ ወይንም ድጋዛን ዘራቸውን የሚጠቅሱ ሲሆን በዋንናነት ቃሉ ቃሉ በዲ ይጀምራል ይህ ገናና ንጉስ የነበረው በአክሱማዊት ኢምፓየር መውደቂያና በሶሎሞኒክ ዳይነስቲ እንደገና ሸዋ ውስጥ ተመልሶ መጠናከር (1270s ) መካከል ሲሆን የአንበሳ ውድ እና የ አጼ ድልነ አድ አባት እንደሆነ ይነገራል። ደጃዝማቹም እራሳቸውን ከዚሁ ወገን መጥቀሳቸው ነው። መቸም የአክሱምን ስረመሰረት ከነገስታቱ አውጥተን ለባሮቻቸው እንስጣቸው ካልተባለ።) የጎንደሬያን የስነ ህንጻ አሻራው በወልቃይት በተለይም በማይጋባ አጋባቢ በሰፊው መኖሩ ታሪካዊ ግንኙነቱን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን በተለይም ንጉስ በካፋ ሳይቀር ከደጃዝማች አያና እግዚ ጋር በነበረው መንልካም ግንኙነት በ አስራ ሰባት ሰላሳ ሁለት አካባቢ ወልቃይትን ድንበር አቁዋርጠው ኢትዮጵያን ሊወሩ የመጡትን የውጭ ወራሪዎች እየተሻገር ለመውጋት እንደ አንድ መንደርደሪያ ይጠቀምበት እንደነበር መዛግብቱ ያስረዳሉ። ነገር ግን በውስጥ በተነሳ የስልጣን ሽኩቻ የተነሳ የሳዛጌው ማሞ በባምቤሎ ምላስ ላይ በተሾመ ግዜ ደጃዝማች እያና እግዚ ጋር በገጠመው ጦርነት ደጃምዝማቹን ድል ስለነሳቸው ግንኙነቱ ለግዜው ደብዘዝ ብሎ የቆየ ሲሆን ደጃዝማቹም በአስራ ዘጠኝ ሰላሳ ስምንት ገደማ ህይወታቸው አልፏል(GuiIyas 47 [text]። በአስራ ዘጠኝ አምሳ ስድስት አም ሌላው አማጺ ካሳድ በተደመሰሰ ማግስት ሰርቅን ነኮ የወልቃይት ጸገዴ ገዥሆኖ የተሾመ ሲሆን በ1762 ሱራሄ ክርስቶስ ሲያስተዳድረው በ1788 ደጃዝማች ገድሉ አስገድደው እንዲገብር ያደረጉት አጼ ተክለጊዎርጊስ ነበሩ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ማለቂያ የሌለው ጉዳችን - አንዱዓለም ተፈራ

በአስራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ገደማ ደግሞ ወልቃይት ባላት ለም መሬትና እርጥበት ብቻ ሳይሆን በዘረጋችው የንግድ ማእከል የተነሳ ሱዳኖችም አይናቸውን ከመጣልም አልፈው ወጣ ገባ ማለት ሲጀመሩባት በዚህ ወቅት አረቦች ደግሞ በወልቃይት ከፍተኛ የባሪያ ፍንገላ ያካሂዱ የነበር ሲሆን ብረታብረትና የጥጥ ምርት ወደ አገር ውስጥ የሚገባውም ሆነ አገር ውስጥ የሚመረት መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የልብስ አይነት ወደ ውጭ የሚወጣው በዚሁ በወልቃይት በኩል ነበር።

ፓርኪንስ ወልቃይትን ባቁዋረጠበት አመት አካባቢውን ይገዛ የነበረው ከአባቱ ሃይለማርያም ክፍሌ ስልጣኑ የወረሰው ልጅ ሃይሉ ሲሆን በ1858 ንጉሴ ውልደሚካኤል በ1867 ደግሞ አማጺው ጣሶ ጎበዜ በየተራ አስተዳደረውት በመጨረሻም የጣሶ ጎበዜ በዋግሹም ጎበዜ መገደል የተነሳ (RubActa II, 141, no. 102) በመይሳው ተጀምሮ ባጭሩ የተደናቀፈው አገሪቱን መልሶ የመስፋት ትግል ብዙም ሳይቆይ ከአስራ ስምንት ሰማንያ አንድ ቦሃላ ያለ ተጨማሪ ደምመፋሰስ ወልቃይት ዳግም የኢምፓየሯ ሙሉ አካል ሆናለች።

ወደ ኋላ በመቆፈር የቻለውን ያህል መሄድ ለቻለ ሰው ጠብ የሚል የበቀለ የትግሬ ማንነት ቀርቶ በወልቃይት መንደር ሽው ብሎ ያለፈ የትግሬ ጠረን ለምልክት አያገኝም።ይልቁንም እውነት እንነጋግር ከተባለ ወልቃይትን በመርገጥ እረገድ ከትግሬዎቹ ይልቅ ሱዳኖቹ ስንዝር ከድርብ ይቀድማሉ።

1 Comment

Comments are closed.

Share