መስከረም 06/2018 ዓ.ም
አንብቡት የዛሬ ውሎው ቢያንስ አንብባቹህ
#ሼር አድርጉ ወገን!!
የወንድማችን የተከበሩ አቶ ክርስቲያን ታደለ ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል።
ማረሚያ ቤቱ ከሚፈቅደው ምግብ ውጪ እንዳይገባ ከልክለዋል።ለምሳሌ ማር፣አጥሚትና ሌሎች ፈሳሽ ነገሮች?
የሚፈለገውና የሚያስፈልገው መድኃኒት እየገባለት አይደለም? ባለጊዜዎች አልፈቀዱም!!
የተደረገለት ቀዶ ሕክምና በየጊዜው ስለሚተካ ወደ ሌላ ህመም(ካንሰር) ሳይተካ በጨረር ህክምና መጥፋት አለበት።ለዚህ ደግሞ የቅርብ ሐኪሞቹ ውጪ አገር ሄዶ መታከም እንዳለበት እያለቀሱ ሳይቀር ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ነግረዋቸዋል ግን ሲሚ የአካል የለም!

ያለበት ቦታ መጸዳጃ ቤትም ሆነ ሌላው ነገር ፈጽሞ ምቹ ካለመሆኑ የተነሣ ህመሙ ከመሻል ይልቅ እንዲብስበት እያደረገው ይገኛል!
ሰኞ፣ረቡዕ እና አርብ በቤተሰብ ይጠየቅ የነበረው ጭራሽ እንዲቆም ሆኗል!!
ብዙ ብዙ ስቃይና መከራ እያስተናገደ ለሚገኘው ወንድማችን የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች፣ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እና ሚዲያዎች አገዛዙ ላይ ጫና ፈጥረው ህክምና የሚያገኝበት መፍትሄ ካልተፈጠረ አደጋው ከዚህም የከፋ ስለሚሆን ርብርብ ታደርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን!