ጠመዝማዛ ሁኔታዎችን ካለፈ በኋላ ነው አንደ ህብረተሰብ የሚመሰረተው!!
የአገር ግንባታ ወይም የህብረተሰብ ምስረታ ውስብስብነት!!
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)
ሚያዚያ 29፣ 2018( May 7, 2026)
አሉላ ሰለሞን የወያኔ አክቲቪስቱና ጠባብ ብሄረተኛው በጣም ነው የሚቃዠው። በተለይም ቴዲ አፍሮ ያወጣውንና ያሰራጨውን አዲሱን ዘፈኑን አስመልክቶ ዘፈኑ ጸብን እንደሚጭር አድርጎ ነው ለመተርጎም የሞከረው። እንደ ለማ መገርሳ የመሰለውም የኦሮሞ ኤሊት ነኝ ባይ ቴዲ አፍሮ በዚህ አዲሱ ዘፈኑ የድሮውኑ አገዛዝ እንደሚናፍቅ አድርጎ ነው ለመተርጎምና የጥላቻ ቅስቀሳ ለማድረግ የሞከረው። ሁለቱምና ሌሎችም የቴዲ አፍሮን አዲሱን ዘፈን በተሳሳተ መልክ የተረጎሙትና የጥላቻ ቅስቀሳ የሚያካሄዱት ያልገባቸውና ሊገባቸውም የማይፈልጉት የአንድን ህብረተሰብ አመሰራረት ጉዳይ አለ። አሉላ ሰለሞንና ለማ ጉተማ፣ እንዲሁም ሌሎች የብሄረሰብ አቀንቃኝ ኤሊት ነን ባዮች ከሳይንሳዊ ዕውቀት በብዙ ሺህ ማይሎች ርቀው ስለሚገኙና አስተሳሰባቸውም በጠባብ ትረካ ስለተያዘ ስለ አንድ ህብረተሰብ አመሰራረት ሊገባቸው የማይችሉ መዓት ነገሮች አሉ። የአንድ ህብረተሰብ ምስረታ ጠምዝማዛ ሂደቶችን በማለፍ፣ በመጋጨት፣ አዳዲስ ነገሮችን በመፍጠርና፣ ከዚያ ሲማርና፣ እንደዚህም ነገር አለ ወይ ብሎ ማሰብ ሲጀምርና አዲስ ዐይነት አገዛዝም ሲመሰረት እዲስ ዐይነት ሁኔታን ይፈጥራል። ተበታትኖ የሚኖር ሰውም ሲበሳሰብ የማሰብና የመፍጠር ኃይሉ ይሻሻላል። ከግሪክ ስልጣኔና የኋላ ኋላም ከ16ኛው ክፍለ-ዘመን አንስቶ በአውሮፓ ምድር ውስጥ የተፈጠረውን ሁኔታ ስንመለከት አንድ ማህበረሰብ ወይም ህብረተሰብ ሊሻሻልና ሊዳብር የሚችለው ከሌላው በተሻለ መልክ ሊያስቡ የሚችሉ አዳዲስ ምሁራን ብቅ ሲሉና የገዢ መደቦችን ጭንቅላት መግራት ሲጀምሩ ብቻ ነው። ከዚህ ጋር ተዳምሮም አዲስ ዐይነት የስራ ክፍፍል ሲዳብር፣ የንግድ እንቅስቃሴ ሲስፋፋና አዳዲስ ተቋማትም ሲገነቡ በአጠቃይላ ሲታይ አዲስና የተሻለ ዕድልን የሚፈልግ አዲስ ዐይነት የህብረተስብ ኃይል ይፈጠራል። ይህ ዐይነቱ የህብረተሰብ ኃይልም በገዢው መደብ ላይ ጫና በማድረግ የጥገና ለውጥ እንዲደረግ ግፊት ያደርጋል። በዚህም አማካይነት ነው እነደ ህግ-የበላይነት የሚባሉት ነገሮች በመፈጠርና ተቀባይነት በማግኘት ማንኛውም ኃይል ሊፈነጭ የማይችልበት ሁኔታ ሊፈጠር የቻለው። ከዚያም በኋላ በእነ ዴካ፣ ላይብኒዝና ኒውተን፣ እንዲሁም በሌሎች ሳይንቲስቶች አማካይነት ለቴክኖሎጂ መፈጠር ሳይንሳዊ ግኝትና ፈጠር ሲዳብሩ ልዩ ዐይነት ህብረተሰብ ሊፈጠር ቻለ፤ የውስጥ ኃይልም ለማግኘት ቻለ። ባጭሩ በዚህ መልክ ብቻና በከፍተኛ ዕውቀት በመታገዝ ነው አንድ ህብረተሰብ ከአንድ ዝቅተኛ ወደ ተሻለ ሁኔታ ሊሸጋገር የሚችለው።
እንደሚታወቀውና ግንዛቤም ውስጥ መግባት ያለበት ነገር ማንኛውም አገር በተወሳሰበ ሂደት ውስጥ ነው ያለፈው። አንድ አገር ወይም ህብረተሰብ እንደ ዳቦ የሚጠፈጠፍና ተጋግሮ እንደሚበላ አይደለም። ብዙ ውጣ ውረዶችን ካሳለፈ በኋላ ነው ቀስ በቀስ እንደ ህብረተሰብ ወይም ማህብረሰብ ሊፈጠርና ሊገነባ የሚችለው። እንደሚታወቀው የግል ሀብት(Private Proporty) የሚባለው ነገር ሲፈጠርና በአንድ አካባቢም ሰዎች ተሰባስበው ሲኖሩና የስራ-ክፍፍልም ሲያዳብሩ፣ በተለይም በእርሻ ስራ ላይ ሲሰማሩ አንድ ዐይነት ስርዓትና ይህንንም ስርዓት የሚቆጣጠር የገዢ መደብ ይፈጠራል። በእንደዚህ ዐይነት ሁኔታ ውስጥ ንቃተ-ህሊናና ዕውቀት ያልዳበሩ ስለነበር አብዛኛውን ጊዜ ኃይል ወሳኝ በመሆን ህብረተሰቡን ይቆጣጣራል። ሌላ ተፎካካሪ ኃይልም ሲነሳ ጦርነት የሚባለው በመቀስቀስ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች ሳይወዱ በግድ የጦርነቱ ሰለባ ይሆናሉ። ይህ ዐይነቱ በተለያዩ ገዢዎች መሀከል የሚካሄድ ጦርነት በተለይም ከክርስቶስ ልደት በፊት በስምንተኛው ክፍለ-ዘመንና ከዚያም በኋላ በተለያዩ በግሪክ ደሴት በሚኖሩ ጎሳዎች መሀከል ጦርነት በመቀስቀስ ብዙ ህዝብን ጨርሷል። ወደ አውሮፓ ስንመጣም ተመሳሳይ ሁኔታን እንመለከታለን። በተለይም የአውሮፓውን የህብረ-ብሔር ወይም የአገር ግንባታ ስንመረምር የአውሮፓው ፊዩዳሊዝም በጣም ጨቋኝ ነበር። ገበሬውም በከፍተኛ ደረጃ የሚበዘበዝና ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የመዘዋወር መብትም ስላልነበረውና፣ ከባላባቱ ፈቃድ ውጭ ማግባት ስለማይፈቀድለት በየጊዜው ያምጽ ነበር። ስለሆነም በከፍተኛ ደረጃ ብዙ ጦርነቶች የተካሄዱት በአውሮፓ ምድር ውስጥ ነው። በተለይም የአውሮፓው የካቶሊክ ሀይማኖት በጣም ጨቋኝና ከእሱ አስተሳሰብ ውጭ ያሉ ዕውነተኛ አስተሳሰቦችን የማይቀበልና፣ አንዳንዶችንም የሚያስርና የሚገድል ነበር። ለምሳሌ የካቶሊክ ሃይማኖት መሪዎች መሬት የፕላኔቶች ሁሉ ማዕከል የሆነችና የማትንቀሳቀስ ናት ብለው በጭፍን ያምኑ ነበር። በመጀመሪያ ኮፐርኒከስ፣ የኋላ ላይ ደግሞ ጋሊሊዮ ይህንን አሰተሳሰብ ውድቅ በማድረግ ፀሀይ የፕላኔቶች ሁሉ ማዕከል መሆኗን ያረጋግጣሉ። ጋሊሊዮም እንደዚህ በማለቱ እስር ቤት ውስጥ ተወርውሯል። አስተሳሰቡንም እንዲቀይር ተገዷል። ቡርኖ ጋርዲያኖስ የሚባለውም ፈላስፋ ጭፍን የሆነውን የካቶሊክ የሃይማኖት መሪዎችን አስተሳሰብ በመቃወሙና ትክክልም አለመሆናቸውን በማረጋገጡ ከእነ ነፍሱ ተቃጥሏል።
ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ለስምንት መቶ ዐመት ያህል የፊውዳሉ ስርዓትና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በሰሜኑ ክፍል ብቻ የተወሰኑ ነበሩ። ጭቆናና ብዝበዛ ተደርጓልና ተፈጽሟል ሲባልም ለስምንት መቶ ዓመት ያህል በአማራው ላይ ብቻ ነው። ይሁንና በሰሜኑ ክፍል ጭንቅላትን የሚያድስ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ባለመኖሩና፣ በተለይም ደግሞ በግራኝ መሀመድ ጦርነት የተነሳ በዚያ የነበሩ ቤተክርስቲያናት ሊወድሙና የፊዩዳሉ አገዛዝም ሊዳከም ችሏል። ምናልባት ይህ ዐይነት ወደ 19 ዓመት ገደማ የፈጀ ወረራና አንድ አካባቢን የማውደሞ ጦርነት ባይካሄድ ኖሮ አንድ ዐይነት ምሁራዊ እንቅስቃሴ ሊነሳ ይችል ነበር። ለማንኛውም በዚህ ምክንያት የተነሳና ከውጭ የሚመጣ የተሻለ ምሁራዊ ዕውቀት ባለመኖሩ ብዙ ነገሮች በዘልማድ ነበር ይሰሩ የነበረው። ስለሆነም ለአንድ ህብረተሰብ መሻሻልና መዳእብር አስፈላጊ የሆኑ በተለይም እንደ ዕደ-ጥበብና ንግድ የመሳሰሉት ሊዳብሩና ሊስፋፉ አልቻሉም። በሌላ አነአግገር የአብዛኛው ህዝብ መተዳደሪያ የእርሽ ሙያ ብቻ ነበር።
ወደ ትግራይ ስንሄድ ደግሞ ዘመናዊት ኢትዮጵያ ከተመሰረተች በፊትም ሆነ በኋላ የትግራይን ግዛት ያስተዳድሩ የነበሩት የትግራይ መሪዎች ወይም ባላባቶች ነበሩ። ይህም ማለት አማራ የሚባል ባላባት ክልሉን አስተዳድሮ በፍጹም አያውቅም ነበር። ስለሆነም ጭቆና አለ የሚባል ከሆነ በትግራይ የግዢ መደቦች በራሱ በትግራይ ብሄረሰብ ላይ የሚካሄድ ነበር። ስለ ኋላ-ቀርነትም ሲወራ ተጠያቂ የሚሆኑት ክልሉን የሚያስተዳድሩት ነገስታት ወይም ባላባቶች ናቸው። ስለሆነም የአማራው ብሄረሰብና የገዢ መደቦች ስለ ትግራይ ኋላ-ቀርነት በፍጹም ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም። ወደ ደቡብና ምስራቁ ክፍለኢትዮጵያ ስንመጣም የፋዩዳሉ ስርዓት አልነበረም። በእርግጥ ለክርስቲያኑ ግዛት የሚገብሩ የተለያዩ ነገስታት ነበሩ። እነዚህ ወደ አምስት የሚጠጉ ነገስታት አነሰም በዛም የተሻለ አደረጃጀት የነበራቸውና በእርሻ ስራ ላይም የተሰማሩ ነበሩ። የራሳቸው ነፃነትም ነበራቸው። የሰሜኑ ገዢዎች በእነሱ ላይ ጫና ያደረጉበት ጊዜ አልነበረም። በሌላ አነጋገር አፄ ምኒልክ አዲሲቱን ኢትዮጵያ ከመመስረታቸው በፊት የደቡቡን ክፍል ያስተዳድሩ የነበሩት የተለያዩ የየብሄረሰቡ መሪዎች ነበሩ። ይሁንና እነዚህ የተለያዩ መሪዎችና ብሄረሰቦች በ16ኛው ክፍለ-ዘመን ኦሮሞዎች በአብዛኛው የኢትዮፕያ ክፍል ሲስፋፉ አገዛዞችን ያውድሟቸዋል፤ ማህበረሰቡንም ይበታትናሉ። የተለያዩ ብሄረሰቦችንም ይውጧቸዋል። ትርሚንግሃም የሚባለው የእንግሊዙ ደራሲ የእስልምና ሃይማኖት በኢትዮጵያ(Islam in Ethiopia) በሚለው ግሩም መጽሀፋ ኦሮሞዎች በተለይም በደቡቡ ክፍል የኢትዮጵያ ግዛት ያደረሱትን ጥፋት ነው የሚያረጋግጠው። ኦሮሞዎች ሲስፋፉም አዲስ በዕደ-ጥበብና በቤት አሰራር፣ እንዲሁም በልዩ ልዩ መልኮች የሚገለጹ ባህሎችንና ቅርሳቅርሶችን ይዘው ያልመጡና ያልነበራቸውም ስለነበሩ ለአካባቢው ዕድገት ምንም ያበረከቱት አስተዋፅዖ አልነበረም። ስለሆነም እስከ 19ኛው ክፍለ-ዘመን ድረስ በደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል ጭቆና ነበረ የሚባል ከሆነ የሰሜኑ የፊዩዳል ስርዓትና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በፍጹም ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም። በሌላ ወገን ደግሞ የኦርቶዶክስ ሀይማኖትና የፊዩዳሉ ስርዓት እዚያው በእዚያው የስልጣኔ መሠረቶችም ነበሩ። ዛሬ የምንጠቀምባቸው አብዛኛዎቹ ነገሮች በሙሉ ከአራተኛው ክፍለ-ዘመን ጀምሮ እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረሰ እየዳበሩ የመጡ ናቸው። የግዕዝ ፊደልና ቋንቋ፣ የሙዚቃ ቃና መዳበርና ፅላንፅል፣ በገና፣ ማሲንቆና ክራር፣ እንዲሁም ከበሮ በዚያው ዘመን ነው የተፈጠሩትና የዳበሩት። ሰዋስውም በእዚያ ዘመን ነው የተቀነባበረው። ይህም ራሱን የቻለ ሳይንሳዊ ስራ ነው። የእርሻ ባህልም የዳበረው በዚያው ዘመን ነው። ጤፍ፣ ገብስ፣ ሰንዴ፣ ማሽላ ዘንጋዳና ሌሎችም ለዘይት ጭማቂ የሚያገለግሉ እንደ ተልባ፣ ኑግና ሰሊጥ፣ እንዲሁም ሌሎች የጥራ-ጥሬ እህሎች፣ ሽምብራ፣ ባቄላ፣ አተርና ሌሎችም በገበሬው የማሰብ ኃይል የዳበሩና የተስፋፉ ናቸው። ይህም ራሱን የቻለ የስልጣኔ መሰረት ነው። የአንትሮፖሎጂ ተመራማሪዎች እንደሚያስተምሩን የስልጣኔ ዋናው መሰረትና በአንድ አካባቢ መስፈርና የእርሽ ባህልን ማዳበርና ከብት ማርባት ነው። ጠላ፣ ጠጅና ካቲካላ፣ እንዲሁም እንጀራ መጋገርና የወጥ ስራ፣ ድፎ ዳቦ መጋገርም በፊዩዳሉ ስርዓትና በኦርቶዶክስ ሀይማኖት የበላይነት ዘመን የተፈጠሩ ናቸው። እነዚህ ዐይነት ባህሎችም በመፈጠራቸው ቀስ በቀስ ህብረተሰቡን ሊያያይዙ ችለዋል። የኋላ ኋላ ላይ ሁሉም ብሄረሰቦች ሊጠቅሙባቸው ችለዋል። አፄ ኃይለስላሴ ከስደት ከተመለሱና የመንግስቱንም መኪና ከጨበጡ በኋላ በተለይም ከ1950ዎቹ መጀመሪያ ጀምሮ የዘመናዊነትን ፖሊሲ(Modernaization Policy) ተግባራዊ ሲያደርጉ በተለይም እንደ አዲስ አበባ በመሰለው ቀስ በቀስ እየደመቀ በመጣ ዋና ከተማ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ጎሳዎች በመሰባሰብ አዲስ ዐይነት የስራ ዕድል ማግኘት ችለዋል። ይሁንና የዘመናዊነቱ ፖሊሲ የተሟላና ለተስተካከለ ዕድገት የሚያመች ስላልነበር ለሁሉም የተሻለ የመፍጠርና የመስራት ዕድል ሊከፍት አልቻለም። በሌሎች የአፍሪካና የደቡብ አሜሪካ አገሮች ይታዩ የነበሩና አሁንም የሚታዩ ዝብርቅርቅ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ችለዋል።
ወደ አገራችን ስንመጣ የአዲስቱ ኢትዮጵያ መፈጠርና ህዝቡም እየተሰባሰብ ሲመጣ በተለይም እንደሙዚቃ ወይም ዘፈን የመሳሰሉት ባህሎች ልዩ ዕምርታን በማግኘት ሁሉም የሚያዳምጣቸውና የሚደሰትባቸው ሊሆኑ በቅተዋል። በዚህም አማካይነት ብቻ ነው ማንኛውም የሰው ልጅ የማሰብ ኃይሉ ሊዳብርና አዳዲስ ነገሮችንም ሊፈጥር የሚችለው። እነዚህን የመሳሰሉት በልዩ ልዩ መልክ የሚገለጹ ባህሎችም የመጨቆኛ መሳሪያዎች ተደርገው በፍጹም ሊታዩ አይችሉም። የሚታዩ ከሆነ ደግሞ ተጨቁነናል የሚሉ ብሄረሰቦች ለምሳሌ እንጀራን መብላትና ጠላን መጠጣት ወይም መጥመቅ ማቆም አለባቸው። ባጭሩ በአጠቃላይ ሲታይ የቋንቋ መዳበርና አብዛኛው ህዝብ ሊጠቀምባቸው መቻሉ፣ የሌሎች ባህሎችም መዳበርና መስፋፋት፣ እንዲሁም በማንኛውም ዜጋ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘትና መጠቀሚያ ማድረግ እንደመጨቆኛ መሳሪያዎች መታየት የለባቸውም። እንደዚህ የሚባል ከሆነ ደግሞ እነዚህን ብቻ ሳይሆኑ ከውጭ የመጡና የሚመጡ ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ ጋር የሚያያዙ ምርቶችን፣ የልብስና የጫማ ዐይነቶችን ሁሉ የመጭቆኛ መሳሪያዎች ስለሆኑ አንፈልግም ማለት ያስፈልጋል። ከውጭ የሚመጡ ዕውቀቶችም የመጨቆኛ መሳሪያዎች ስለሆኑ መማር የለበንም ብሎ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ያስፈልጋል። ይህ ከሆነ ደግሞ በጨለማ ዓለም ውስጥ መኖርና የልዩ ልዩ በሽታዎች ሰለባ መሆን ነው። በአጠቃላይ ሲታይ የሰው ልጅ ውስጣዊ ኃይል ስላለውና ማሰብም ስለሚችል በአንድ አካባቢ ብቻ ተወሰኖ ሊኖር በፍጹም አይችልም። ሲንቀሳቀስና ከሌላው ማህበረሰብ ጋር ሲቀላቀል፣ ሲጋባ፣ ሲዋለድና ሲተሳሰር የማሰብ ኃይሉ ይዳብራል። አዲስ ዐይነትም ስራ-ክፍፍል በማዳበር በንግድ አማካይነት ይተሳሰራል። ገንዘብ የሚባለውንም ነገር በመፍጠር በአጠቃላይ ሲታይ ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ልዩ ዕምርታን ይሰጠዋል።፡ በአጠቃላይ ሲታይ የሰውን ልጅ የልጣኔ ታሪክ ስንመለከት ማንኛውም አገርና ህዝብ በራሱ ብቻውን የፈጠራቸው ነገሮች የሉም። ቢኖሩም እንኳ ሊሻሻሉና ሊዳብሩ የሚችሉት ከውጭ ከመጣ አስተሳሰብ ጋር ሲጣመሩና በአዲስ መልክ ሲዋቀሩ ብቻ ነው። የዓለም ህዝብ የስልጣኔ ታሪክ ይህንን ነው የሚያረጋግጠው። ይህንን ስንመለከት ሰውም ሆነ ማንኛውም ነገር የብዙ ነገሮች ውህደቶች ናቸው። የሰውን ልጅ ስንመለከት ከዚህ ጎሳ የመጣሁ ነው ብሎ ቢገልጽ ይህ ዐይነቱ አባባል ሳይንሳዊና ባይሎጂካሊ ሳይሆን የማህበረሰብ አወቃቀር(Social Construction) ውጤት ነው። የጎሳ ጉዳይና የማንነት ጉዳይ በጉልህ መታየት የጀመሩት ከ20ኛው ክፈለ-ዘመን አማካይ ጀሞሮ ካፒታሊዝም በዓለም አቀፍ እየተስፋፋ ሲመጣና በተለይም እንደኛ ባለው አገር ያልተስተካከለ ዕድገት(Unequal Development) ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ ነው። የጎሳንም ጥያቄ ያነሳው ብዙም የህብረተሰብን ጠመዝማዛ ጉዞና ዕድገት ያልገባው የየብሄረሰቡ ኤሊት ነኝ ባይና የተማሪው እንቅስቃሴ ናቸው። እነዚህም በሁሉም አቅጣጫ የጠለቀ ዕውቀት ስላልነበራቸው ኢትዮጵያን የብሄረሰቦች እስር ቤት ናት በማለት አጨልመው ስለዋል። በተለይም የየብሄረሰቡ ኤሊቶች የውጭ ኃይሎች ተገዢ በመሆን በዚህ አማካይነት አገራችንን የማዳከምና ኋላ-ቀር ሆና እንድትቆይ የማይሰሩት የታሪክ ወንጀል የለም።
የህብረተሰብን ጠመዝማዛ ሂደት፣ የመሻሻልና አዳዲስና የተገለጸላቸው ኃይሎች የመፈጠርን ጉዳይ ለመረዳት የማይችሉ በውጭ ኃይሎች የሚጠመዘዙ የትግራይና የኦሮሞ ኤሊቶች በጠባብ አስተሳሰብ በመታወር በታሪካችንና በህዝባችን ላይ ከፍተኛ የጥላቻ ዘመቻ ከፍተዋል። የባህል ውድመትና በግልጽ በሚያካሂዱት ጦርነትም ህዝባችንን ከመጨረስ ባሻገር የስልጣኔውን መንገድ እያዳፈኑት ነው። እነዚህ ኃይሎች በተለይም የአሜሪካንና የግብረ-አበሮቿ መሳሪያ በመሆን አገራችንን ወደ ጦር አውድማነት ለውጠተዋታል። እነዚህን ጠባብና የውጭ ኃይሎች መሳሪያ የሆኑትን የትግራይንና የኦሮሞ ኤሊቶችን የሚቆጣጠርና የሚገታ ኃይል እስከሌለ ድረስ አገራችን እንደ አገር የመኖር ዕድሏ በጣም የመነመነ ይሆናል። ህዝባችንም በየቦታው በመሰደድ በስቃይ እንዲኖር ይገደዳል ማለት ነው። ስለዚህም በአዳዲስና በተሻለ ሳይንሳዊ ዕውቀት በመደገፍና ሳይንሳዊ ትንተና በመስጠት እነዚህን ኃይሎች በትክክለኛ ዕውቀት መዋጋት ያስፈልጋል። መልካም ግንዛቤ!!
fekadubekele@gmx.de
www.fekadubekele.com
ማሳሰቢያ፤ እንደዚህ ዐይነት ሳይንሳዊ ትንተና ለማንበብ የምትፈልጉ ድረ-ገጼን በማገላበጥና ከላዩ ላይ የሰፈረውን ዶኔት የሚለውን በተን በመጫን አስፈላጊውን ዕርዳታ ማድረግ ትችላላችሁ። ከዚህም በላይ ስለ ተሃድሶና ስለ ሁለ-ገብ ዕድገት በዩቱብ ቻናል (Ethiopian Renaissance) በየጊዜው የማቀርበውን የቪዲዮ ስርጭት በማዳመጥ ደንበኛ በመሆን ስርጭቱን ማገዝ ያስፈልጋል። በዚህ አማካይነት ብቻና የነቁ ኃይሎች የራሳቸውን አስተዋፅዖ ማበርከት ሲችሉ የተሻለ ህብረተሰብአዊ ለውጥ ማምጣት ይቻላል።