አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ክፍል አምስት
የፖለቲካው ቀውስ
“ጅጅጋ የሚኖር ሶማሌ ያልሆነ ሌላ ኢትዮጵያዊ የማህበረሰባዊ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብት የማይኖረው ከሆነ የመንግሥታችን ስርዓት አፓ ታይድ ነው ማለት ነው። ሌላ ምንም ስም መስጠት አያስፈልግም።”
የሶማሊ ክልል ፕረዝደንት ሙስጠፌ ኡመር
አቶ ሙስጠፌን ታሪክ ሲያወሳህ ይኖራል እያልኩ፤ የተናገረውን ሃቅ ሌሎች ጠባብ ብሄርተኞች እና የብሄር ጽንፈኞች ስር ዓቱ ያስከተልውን ዘርፈ ብዙ ቀውስ እንዲያስቡበት እመክራለሁ።
ወያኔዎችና ኦነጋዊያን አስበውበት የመሰረቱት ሕገ መንግሥትና አፓርታይድ መሰሉ የአስተዳደር መወቅር ለአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሲኦልን ሆኖበታል። የዐብይ መንግሥት ወጥቶ መግባት ብርቅ የሆነበትን ማህበረሰብ ፈጥሯል። ኢትዮጵያን የሚገዟት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ህግንና ስርዓትን ስለማያከብሩ፤ ህገወጥነት፤ ውንብድና፤ ቀማኛነት፤ ውሸት መናገር፤ ሌብነትና ሙሰኛነት፤ የዘውግና እምነት ጥላቻ እና ኢ=ሰባዊነት፤ ኢ-ፍትሃዊትነት የተለመደ ባህሪይ ሆኗል።
ይህንን ትንተና የማቀርበው ከፖለቲካ ኢኮኖሚው አንጻር ይሆናል። የሚሸፍነው የመንግሥት ስርዓቱን፤ የአስተዳደር መዋቅሩን፤ ሥልጣኑን፤ አስተዳደሩን፤ ሕግና ደንቡን ከኢኮኖሚው፤ ከባንኩ፤ ከተፈጥሮ ኃብት ይዞታው፤ ክድህነት ቀረፋው፤ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው መሆኑን የሚያሳይ ስእል ነው። ይህ ግንኙነት ሲተገበር፤ በግለሰቦችና በማህበረሰባዊ ህይዎት ላይ ተጽኖ አለው።
እየገደሉ መደመር አይቻልም።
ምንም ልንክደው የማንችለው ሃቅ ይህንን ይመስላል። የደርግ መንግሥት ስልታዊ በሆነ ደረጃ የአማራውን ልሂቃን–ዲፕሎማቶችን፤ ምሁራንን፤ የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ፤ የሚሊታሪና ሌሎች ተቋማት መሪዎችን፤ ታዋቂ ግለሰቦችን ወዘተ ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ጨፈጨፋቸው። በሶሻሊዝም አመካኝቶ ቤት፤ መሬትና ሌላውን ንብረታቸውን ወረሰው። አማራውን ከፖለቲካው ሚናው አወጣው። ከኢኮኖሚውም አወጣው። የቀሩት ልሂቃን እንዲሰደዱ አደረገ። ባጭሩ አማራው ራቁትን ቀረ ማለት ነው።
ኢህአዴግ ሥልጣን ከያዘበት ወዲህ ደግሞ፤ የአማራው ህይዎት የተሸጋገረው ከድጡ ወደ ማጡ ነው ለማለት ያስችላል። አማራ ጠል ግፍና በደል በመንግሥት ደረጃ መካሄዱ ተባባሰ፤ በተለይ የወያኔን መንግሥት የተካው የዐብይ ኦህዴድ ብልጽግና ሥልጣኑ ከያዘበት ወዲህ።
ጥቂት ምሳሌዎች በቂ ናቸው። የድሮን ጥቃት ዋና ምሳሌ ነው።
ለመሆኑ የት ላይ ነው የድሮን ጥቃት የተካሄደው?
በሰሜኑ ጦርነት (2021 – 2022) በመቀሌ፤ በአላማጣ፤ በአዲግራት፤ በአማራው ክልል ከ2023 ወዲህ በቆቦ፤ በፍኖተ ሰላም፤ በምንጃር፤ በቋሪት፤ በገደብ፤ በደብረ ታቦር፤ በወረታ በተደጋጋሚ ታዛቢዎች እንደሚሉት ከሆነ ወደ ሶስት መቶ የሚጠጋ የድሮን ጥቃት ተካሂዷል። በ February 2026 ብቻ 77 የድሮን ጥቃት ተካሂዷል። ጥቃቱ ያነጻጸረው በአማራ ፋኖ ላይ ቢሆንም እልቂቱ የተካሄደው በንጹሃንና በንብረት ላይ ነው። ይህ የጦር ወንጀል መሆኑ አያከራክርም።
ደረጃው ቢለያይም፤ የዐብይ ሰራዊት ኦነግ ሸኔን ለማምከን በወሰደው እርምጃ በኦሮሞያ ክልል በወልቂቴ፤ በጮቢ፤ በምስራቅ ወለጋ የድሮን ጥቃት አካሂዷል።
በእነዚህ አካባቢዎች ጦርነቱ ተባባሰ እንጅ የዐብይ መንግሥስት የአማራ ፋኖን ሆነ ኦነግ ሸኔን ሊቋቋመው አልቻለም። ጥያቄው ይህ ከሆነ ለምን በንጹሃን ላይ እልቂት ይካሄዳል? የሚለው ነው።
ምንም ልንማር እንችላለን?
የዐብይ ብልጽግና በጭፍንና በጅምላ የሚያካሂደው የድሮን ጥቃት ተቆርቋሪነቱ የሥልጣን እንጅ የሕዝብ ደህንነት የሚያንጸባርቅ ሆኖ አላገኘውም።
የኔ ትኩረት በሶስት መስረታዊ፤ ስርዐታዊና መዋቅራዊ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡
አንደኛ፤ ከላይ እንደገለጽኩት፤ በአማራው ሕዝብ እልቂት (genocide) ተካሂዷል፤ አሁንም እየተካሄደ ነው በሚለው ላይ፤
ሁለተኛ፤ በፖለቲካው የአንድ ጎሳ ፍጹም የበላይነት ላይ፤
ሶስተኛ፤ በኢትጵያ ኢኮኖሚ ውድቀትና አሉታዊ ውጤት ላይ፡፡
1/ በአማራው ላይ የሚካሄደው መንግሥት መር ጭፍጨፋ በጦር ወንጀል ያስከስሳል፡፡
የማይካደው ሃቅ፤ በአማራው ሕዝብ ላይ እልቂት (Genocide) ተካሂዷል። ይህንን ሃቅ እንቀበል። ምክንያቱም፤ የአማራው እልቂት በመረጃ የተደገፈ ከመሆኑ በላይ ድርጊቱ በጀኖሳይድ በሕግ የሚያስጠይቅ ከመሆኑም ባሻገር አገር አፍራሽ ነው። በዚህም ምክንያት፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ስብስቦች በአማራ እልቂት ወይንም ጀኖሳይድ ላይ አቋማቸውን የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው። ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ የምንመኝ ገለሰቦችና ስብስቦች ብሄር ተኮር እልቂትን የማውገዝ ግዴታ አለብን። አገር ያለ ህዝብ ህልውና አይታስብም። የጋዛ ወይንም የሌባነን ሕዝብ ሲጨፈጨፍ እኮ ትኩረት በጨፍጫፊዎቹ የተሰጠው መርህ መሬቱን ከህዝብ መለየት የሚል ነው። የአማራውም ጉዳይ ተመሳሳይነት አለው።
እንደ ማንኛውም አገር ወዳድ እኔም ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን፤ በአማራው ሕዝብ ላይ በተከታታይ የሚካሄደውን ስርዓት ወለድ፤ መንግሥት መር እልቂት ስናውግዝ ነው፡፡ ይህንን ስል በሌሎች ሕዝቦች ላይ ግፍና በደል፤ እልቂት አልተካሄደም ማለቴ አይደለም፡፡ በብሄሩ ተለይቶ በሁሉም ዘርፍ የብሄር ተኮር እልቂት የሚካሄደው ግን በአማራ ሕዝብ ላይ ነው፡፡ ልዩነቱን ላሰምርበት እፈልጋለሁ፡፡ ይህ አጠቃላይ ስእሉ ነው፡፡
ተዛማጁ ሃቁ የዐብይ አገዛዝ የጦር ወንጀል በአማራ ብቻ የተካሄደ አለመሆኑ ነው፡ በሰሜኑ ጦርነት ብቻ ከ600,000 ሽህ እስከ አንድ ሚሊየን ወገኖቻችን መስዋእት ሆነዋል። ለዚህ እልቂት እስካሁን በጦር ወንጀል፤ በሰብአዊ እልቂት በሃላፊነት የተጠየቀ ግለሰብ ወይንም አካል የለም።
የጦር መኮንኖች፤ የፌደራል ባለሥልጣናት እና በየአካባቢው የተሳተፉ ባለሥልጣናት በጦር ወንጀል ለፍርድ መቅረብ አለባቸው። ይህ ካልተደረገ እልቂቱ በምንም አያቆምም።
የኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት በአማራው ላይ አስቸኳይ አዋጅ አውጆ በግምት እስካሁን 300 የድሮን ጥቃት ወንጀል ፈጽሟል። ብዙ ሽህ አማራዎች ተገድለዋል።
እንደ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ያሉ በድሎት የሚኖሩ የዐብይ ጦር ሰራዊት መሪዎች መጠንቀቅ ያለባቸው በጦር ወንጀል መከሰሳቸው የማይቀር መሆኑን ነው።
በኢኮኖሚው በኩል እስካሁን ድረስ የተፈጸመው ውድመት ከ $30 እስከ $40 ቢሊየን ይገመታል። መሰረተ ልማት ሙሉ በሙሉ በሚያስብል ደረጃ ወድሟል። የአማራውንና የትግራዩን ክልል መልሶ ወደ ነበሩብት ለማቆም ብዙ ቢሊየን ዶላር ኢንቬስትመንት ያስፈልጋል ማለት ነው። ሌላ ጦርነት ከተካሄደ የሕዝቡ ኑሮ በበሰጠ ይናጋል። የኑሮ ውድነት ይባባሳል። መላው የአፍሪካ ቀንድ ይታመሳል።
በአማራ ሕዝብ ላይ የተካሄደው መንግሥት እና አጋር ኃይሎች መር እልቂት በዓለም የሰብአዊ መብት ህግ በወንጀለኛነት ያስከስሳል። በቅርቡ የታወቀው ጋዤጠኛ ደራሲ ጀፍ ፒርስ ባደረገው ዘገባ፤ በአማራ ሕዝብ ላይ ከ 2018 ዓ.ም. ወዲህ ብቻ በእቅድ በዐብይ መንግሥትና ተባባሪዎቹ የሚካሂደው አማራውን ኢላማ ያደረገ እልቂት ነው። የፒርስን ዘገባ ያንጸባረቁ ግምገማዎች በአምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ በሁማን ራይትስ ወች፤ በጀኖሳይድ ወች፤ በሌምኪን ኢንሥቲቱት፤ በAAA, በኢትዮጵያ ሰብ አዊኮሚሽንና በተባበሩት መንግሥታት ሰብእዊ ኮሚሽንና ካውንስል ተካሂደዋል።
እነዚህ መረጃዎችና ማስጠንቀቂያዎች የሚያረጋግጡት በአማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደው ብሄር ተኮር እልቂት Genocide የሚለውን ያሟላል፡ በ December 1948 የተባበሩት መንግሥታት አባላት የተቀበሉት አስገዳጅ ሕግ በጥቅሉ በእንግሊዝኛው ሲቀርብ የሚከተሉትን ያሳያል::
‘To prevent and punish the crime of genocide, the 1948 UN Convention outlines key principles and obligations: Defines genocide as acts committed with intent to destroy a national, ethnic, racial, or religious group. Obligates signatory states to prevent and punish genocide, regardless of where it occurs.
Establishes jurisdiction for international courts to prosecute individuals accused of genocide.
Encourages cooperation among nations to investigate and prosecute genocide cases.
Promotes education and awareness to prevent future genocides.
Requires states to enact laws to implement the Convention’s provisions domestically.’
የኔ ትኩረት ጀኖሳይድ አንድን ብሄር፤ ዘውግ ወይንም ሕዝብ በመደምሰስ፤ በመግደል፤ በማቁሰል፤ በማጥፋት፤ በማስራብ፤ በማሰር፤ ልጆች እንዳይወልዱ ውይንም እንዳይማሩ ጫና በማድረግ፤ ከቀያቸው በማፈናቀል፤ እንዲገደሉ ቅስቀሳ በማድረግ የሚካሄድ ወንጀል ማለት ነው፡፡ ይህንን ወንጀል የሚተገብሩ ባለሥልጣናትና አካላት በየትኛውም አገር፤ ቦታ፤ ሁኔታና ጊዜ በሃላፊነት እንደሚጠየቁ ያረጋግጣል፡፡
በነዚህ መስፈርቶች ስገመግመው በአማራው ሕዝብ ላይ እልቂት (ጀኖሳይድ) ተካሂዷል፤ አሁንም
…