እኔዎች (እኔያት) – በላቸው ገላሁን September 21, 2022 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email እኔዎች (እኔያት) አንዱ እኔ ሲጠራኝ አንዱ እኔ ሲልከኝ ሌላው እኔ ሲጥለኝ አንዱ እኔ ሲያነሳኝ፣ አንዱ ወደ ግራ ያአንዱ ባለጋራ አንዱ ወደ ደጅ የሌላው ወዳጅ፣ ሌላኛው ወደ ቀኝ ሌሎቹን እንዲዳኝ አንደኛው ወደ ታች ለራሱ ሊያመቻች፣ አንዱ ወደ ላይ ሊነካ ሰማይ አንደኛው ወደ ፊት ሌሎቹ እንዳይቀድሙት አንዱ ወደ ኋላ ሊያጣራ ሊያብላላ፤ አቤት የእኔ መዓት የራሴ ብዛቱ ለየቱ እንቢ ብዬ ልታዘዝ ለየቱ? እኒህ ሁሉ እኔዎች ውስጤ ተከምረው ሁሌ እየተጣሉ አልስማማ ብለው አንድ እኔ ባተለ ፍዳውን ቆጠረ ሌላው ኔ ደስ ብሎት ተኝቶ እያደረ። በላቸው ገላሁን (ነሓሴ 1998) (USA) Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ