በብዙ የሰለጠኑ አገራት መረጃን የሚያቀርቡ ሜዲያዎች ከሕግ አውጭው፣ ከሕግ አስከባሪዉና ከሕግ ተርጓሚው የመንግስት ሶስት ቅርንጫፎች በተጨማሪ አራተኛው የ”መንግስት” ቅርንጫፍ ተደርገው የሚቆጠሩ ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የሕዝብ ሜዲያዎች የመንግስት ፕሮፖጋንዳ መሳሪያዎች የሆኑበት፣ የግል ሜዲያዎችም ከፍተኛ ጫናና እንግልት የሚደርስባቸው አገር ሆና ነው የቆየችው።
ዘ-ሐበሻ፣ ይሄንን ክፍተት በተወሰነ መልኩ ለመምሏት፣ በኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር ከ1997 ዓ/ም ጀምሮ፣ ላለፉት አስራ ሰባት አመታት ፣ በኢትዮጵያ ፍትህ፣ ሰላም፣ እድገትና ዴሞክራሲ እንዲኖር፣ ኢትዮጵያዉያን በአገራቸው ጉዳይ ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲያገኙ ለማድረግ በመስራት ላይ ያለ ነጻ፣ ገለልተኛ፣ ከገዢዎች ሆነ ከፖለቲካ ድርጅቶች ተጽኖ ውጭ የሆነ ሜዲያ ነው፡፡