እረኝነት … ትልቅ ኃላፊነት … መሆኑንን አውቃለሁ ። ግን እኔ ለወንድሜ መልካም እረኛ ሆኛለሁ ? ወይስ እኩይ ቅናት ስላደረብኝ የመጥፊያውን ጉድጎድ እቆፍራለሁ ? ” ከእኔ ቀድሞ በሞተ ! ” ቢዬ እፀልያለሁ ። ……………………………….. ግን ፣ ግን ፣ መቼ ነው ? ሰው ለሰው መልካም እረኛ የሚሆነው ? አንዱ ለሌላው ሥኬት ፣ እንቅፋት የማይሆነው ? መቼ ነው ? ከጠብ መንጃ አጥር ወጥቶ … ህይወትን የሚኖራት በጋራ ተስማምቶ ? መቼ ነው ፤