እርማት ለጃዋር መሐመድ፡ በነጭ ውሸት ላይ የተመሰረተ ትንተና የት ያደርሰን ይሆን?
በቴዎድሮስ በላይ አቶ ጁዋር ሲራጅ መሃመድ በቅርቡ ከአቶ ደረጀ ደስታ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ (http://ethsat.com/video/esat-yehager-lij-activist-juwar-mohamed-10-may-2013/) በአጽንኦት ተከታትያለሁ። የሰውየው ግለ ታሪክና ያደረጋቸው ጉዞዎች መሳጭ ቢሆኑም አንዳንድ እርማት የሚያስፈልጋቸው የተሳሳቱና የተዛቡ ታሪኮችን እንደገና እንዲፈትሽ፤