January 7, 2025
17 mins read

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥

¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤

¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17

images 6 1ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን ኢየሱስ ይመጣል ። የመጨረሻው ዘመን ደግሞ ይኽቺ ምድር እንዳልነበረች የምትሆኑበት ቀን ነው ። የኃንስ በራእይ ስለዚህ እውነት ያየውን  በቅዱስ መጽሐፍ አስነብቦናል ። ለ2017 ጊዜ የጌታ ኢየሱስን ልደት ስናከብር ይህንን የእምነት እውነት ማንበብ ጠቃሚ ነው ። ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው እና ለእኛ የመሰማት በግ የሆነው በከንቱ አይደለምና ።

መጽሐፍ ቅዲስ እውነት መሆኑንን  ዛሬ ባለ ፀጋ አገሮች    ከምድረ በታች የሰሯቸው ና ለዓመታት ሊሰወሩባቸው ያሰቡባቸው   ዋሻዎች  ( nuclear bunkers and shelters )     ይመሰክሩልናል ።

” የምድር ነገሥታት መኮንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥

ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቁጣ ሰውሩን ፤ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና … ” ይኸ  ጥቅስ በራሱ ፣ የዓለምን ኃያላን የዛሬ ስጋት በወጉ ይገልፅልናል ።

የዓለም ኃያላን ፣ መደበቂያ ፍለጋ መባዘናቸውንም በጠፈር ምርምራቸው እያስተዋልን የራእዩን እውነት እንረዳለን ። የባለጸጋ አገሮች መደበቂያ ፍለጋ ፣ ዓለም እንደ ጨርቅ ስትጠቀለለ ቢያከትምም   ፤  ሌላ መኖሪያ ፍለጋ ጠፈርን ማሰሳቸውን እና መደበቂያ ታላላቅ የመሬት ውስጥ መኖሪያ መገንባታቸውን ግን በዘመነ መልኩ ዛሬም ቀጥለዋል ።

ይህንን ሃቅ ስናስተውል ፣ ሰው ጠፍቶ ለመቀረት እንደማይፈልግ ዘላለማዊነትንም እንደሚሻ እንገነዘባለን ። ሞት ዘወትር  አፋንጫው ሥር እያለ እንኳ የሚሞት አይመስለውም ። እናም በመገረም ” አይ ሰው ፤ ለህይወት ያለው ጥማት ሞትን እኮ አስረሳው እንላለን ። የህይወት ጥማቱ የሚበርድ ባለመሆኑ  በቃኝ ያለማለትንም በልቡ አነገሰበት ።

በሰው አእምሮ የነገሰው የህይወት ጥማት ብቻ አይደለም ። ተቃራኒ ሃሳቦች ሁሉ ነግሰዋል ። ይኽም በመሆኑ የሰው ተለዋዋጭ ባህሪ ሰለመሞቱ እንኳን በውሎ እንዳያውቅ አድርጎታል   ። ሆኖም ሰው ሞቱን ከፍጥረቱ ጀምሮ የሚሸሽ ሆኖም ተራ ሞች ነው ።

ተራ ሟች ቢሆንም   ፣  በሁለት ተቃራኒ ሃሳቦች እየተናጠ የሚኖር ፤ አንዱ ሃሳብ ሲያይልበት በዛ ሃሳብ   ብቻ የሚነጉድ ነው  ።

በሰው ህሊና ፣ በጎ እና ክፉ ፤ ክፋትና ደግነት ፤ ቸርነትና ንፉግነት ፤ ጥላቻና ፍቅር ፤ ወዘተ ። ዘወትር  ይመላለሳሉ ።

እርግጥ ነው ፤ ዛሬ ፣ ከመልካም ሃሳብ ይልቅ ክፉ ሃሳብ የገነነበት ሰው በዚህ ዓለም እየበዛ መሆኑ በዓለም የሚታየው የየዕለት ሰቆቃ እና አስከፊ ድርጊት ያሳብቃል  ።

ዛሬ ሰዎች ከበጎ ሃሳብ ይልቅ ክፉ ሃሳባቸው እጅግ አይሏል ።  ክፉ መንፈሳቸው ማያሉንም  የሚያሳብቀው የየዕለት እኩይ ተግባራቸው ነው  ።

ለምሳሌ ፣  ሰዎች እጅግ ከገዘፈ ስግብግብነታቸው የተነሳ  ፣  ጥቂቶች ከበቂ በላይ ሆኖ የሚታይ  የተትረፈረፈ ሀብት እያላቸው ፣   ብዙሃኑንን  ምንዱባኖች ፣ ለማበልጸግ ከቶም የማይሹ ሆነው እናገኛቸዋለን ። ይኽ  በራሱ ከስግብግብነትም በላይ ሆኖ ይታየኛል ።

በዚህ ረገድ የበለፀጉ ሐብታም ሀገራት   በጣት የሚቆጠሩ ሆነው ሳለ የዓለምን ኢኮኖሚ በሙሉ ተቆጣጥረውታል ። በእነዚህ ሀብታም  ሀገራትም ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች እጅግ ከበደ ምቾት በመነጨ የስሜት አለት  የፈጣሪያቸውን መኖር የመካድ ጉዟቸውም  እያየለ  መጥቷል ።  ስሜታቸውን ከተፈጥሮ ጋራ ለማዋደድ ሳይችሉ ቀርተውም ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ ገብቻን ፈቅደዋል ፣ የወንድ ለወንድ ጋብቻን በህግ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረጋቸው በራሱ በስሜት የመነዳት አባዜ እንደተጠናወታቸው ይመሰክራል ።

ይኽንን ኢ – ተፈጥሯዊ  ጥምረትን በህጋቸው ያጸደቁ መንግስታት   ፣  በተቀሩት ደሃ አገራት እርስ በእርስ መገዳደል ፣ ክፋት ፣ ምቀኝነት ፣ ጠልፎ መጣል  ፣ የተቀነባበረ ሤራ ፣  የገዘፈ ተንኳል እንዲበዛ ምክንያት ቢሆኑ ከቶም አይገርምም ።

የገዘፈ እና አሰቃቂ ወንጀልም ግለሰቦች በተናጠል የሚፈጽሙት እና እራስን ማጥፋት የሚበዛው በእነዚህ አገራት ነው ።

በአውሮፓና በአሜሪካ በግለሰብ ደረጃ ሰዎች በድንገት ሳይታሰብ እየተነሱ አሰቃቂ ድርጊትን የሚፈጽሙትም ህሊናቸው ውስጠ የክፋት ተግባራት በመንገሱ የተነሳ ነው ።

በአፍሪካ ግን ፣ መጥፎ ድርጊቶች በቡድን ደረጃ ነው የሚፈፀሙት  ።  ኢትዮጵያን ምሳሌ ማድረግ እንችላለን ።

” ዜጎቿ  ሰማንያ በመቶ  ኃይማኖተኛ በሆኑባት በእኛዋ አገር ለምን ሰው ሰውን ለመግደል እንዲህ ጨከነ ? ” ብለን ብንጠይቅ ፤ መልሳችን “ ቀስ በቀስ በሰው ህሊና ውስጥ   ከበጎ እና ቅን መንፈስ ይልቅ የተንኳልና የጭካኔ መንፈስ  እየሰረፀ  ስለመጣ ነው  ። ”  የሚል ይሆናል  ።

ገለልተኛ ሆናችሁ ሁኔታውን በአንክሮ ስትገመግሙ  ዛሬ ላይ በዘውግ ፣ በነገድ ፣ በጎሳ ፣ በወንዝ ልጅነት ሰበብ ሰው ሰው መሆኑንን እያደረ በእጅጉ  እየረሳ በመሄድ ላይ ይገኛል ።

ሰው በአደባባይ ሲገናኝ እንኳን እጅግ ወገንተኛ በሆነ መንገድ የሚተያየው ከሚያቀራርበው ጎዳና ውጪ እየተጎዘ እና ሰውነትን በረሳ ሃዲድ ላይ እየተጓዘ   መሆኑንን ያለ ማወቁ ነው ።

የጥላቻ  አስተሳሰብ በህሊናው በማስረፁ የተነሳ የእርሱን መንገድ የማይከተለውን ሁሉ በጠላትነት ይፈርጀዋል  ።

በሚያራርቅ ጎዳና ጉዞአችን መቼ እንደሚያከትም    መቼ እንዴት እና በነማን አርቆ አላሳቢነት ይህ  እኩይ መንገድ እንደተፈጠረ  እንደተፈጠረ  ከ3  ቀን በፊት በፃፍኩት ጦማር ለማሳየት ሞክሬያለሁ ። የአካሄዳችንን ጎጂነትም በወፍ በረር ጠቁሜያለሁ ። “ሰው ሰው እንጂ ሌላ ማንነት የለውም ። “ በማለት ።

በቡድን ሆኖ ለራሱ ሥም ሰጥቶ  ፣ ፓርቲ ሆኖ በየተራ  ሀገር  የሚያስተዳድርም ሆነ በግለሰብ ደረጃ የሚታይ ዜጋ ሰው እና የሰው ስብስብ ነው ። ሰው እና ነገ አፈር መሆኑንን  እስካልተገነዘበ ጊዜ ድረስ  ፣ በሀገራችን ጦርነት ብቻ ሳይሆን የምዕራቡ ዓለም ጥዩፍ ተግባራቶች እጅግ በባሰ መልኩ ሊስፋፉ ይችላሉ ። እናም መንግስትን የሚፈታተኑ የህዝብን ሰላም የሚያደፈርሱ ወንጀሎች በከተሞች እጅግ እየተስፋፉ ይመጣሉ ።

በኃይማኖትም ሂዱ በፖለቲካ ትንተና የወደፊቷ ዓለም  የተረጋጋች እና ሰላም የሰፈነባት ዓለም  የምትሆነው  ሰው ከክፋት ከምቀኝነት ፣ ከተንኳል ፣ ከጥላቻ ከቂም በቀል ፣ ከጭካኔ የፀዳ ህሊና ሲኖረው ብቻ ነው ። ከነዚህ በተቃራና ያሉ ሃሳቦች እና መሰል አሉታዊ ተግባራትን ያከማቸ ህሊና ያለው ሰው ግን  የሤጣን ተግባራትን አራማጅ ይሆናል ።

ዛሬ እንደሚስተዋለው ፣ ደግሞ እነዚህ  ሰውን እርስ በእርሱ እንዲጠፋፉ የሚያደርጉ ፣ አውዳሚ እንጂ ገንቢ ያልሆኑ የመለያየት እና የመጠላላት ተግባራት በአንዳንድ   የኃይማኖቱ ሰባኪያንና አባቶች ህሊና ጭምር እየነገሰ  እየመጠ እንደሆነ ድርጊቶቻቸው እየመሰከሩልን ነው ። ሳይረፍድ በጊዜ ንስሐ ካልገቡ ደግሞ ለእነሱ የሚመጣው የእግዜር የቅጣት እጅ ለመላው ምእመናኑ መትረፉ አይቀሬ ይሆናል ።

ዛሬ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ፣  ቆም ብለው ይኽንን እውነት በማስተዋል ወደ ፍቅር መመለስን አጥበቀው መሻት አለባቸው  ። በተለይም የፖለቲካ ልሂቃኑ ።

ዛሬ አገራችንን  እና ህዝቧን በብርቱ የሚያሰጋት የመሬት መንቀጥቀጥ ከተኛንበት እንድንነቃ የሚያስገድደን ሆኖ አግኝቼዋለሁ ።

በእርግጥ ሁኔታው የዓለም ፍፃሜን ያመለክታልና ንስሐ ግቡ ለማለት አልዳዳም ።  ምክንያቱም ይኽን ለማለት  እንደመጥመቁ ዮሐንስ መኖርን ይጠይቃልና  ። … ማለት የምችለው ” የፍርድ ቀኑ እየተቃረበ ነው ። ይኽቺ ዓለም ፣ የሰዓታት  ፣ የቀናት  የሣምንታት ፣ የወራት ፣ የዓመታት ፣ የክፍለ  ዘመናት  የመጥፊያ ጊዜ እንደሚኖራት ግን  አትዘንጉ  ። ” ማለትን ብቻ ነው ። የዚህ ዓለም ፍጥረታት ሁሉ ፣ ህይወት ያላቸውና የሌላቸው በእኛ በሰው ቁጥጥር ሥር አይደሉምና ምድሪቷ እንደሸማ መቼ እንደምትቀልጥ  ወይም ከሰማይ በሚዘንብ እሳት  ወይም በኮኮብ ናዳ መቼ ቀልጣ እንደምትጠፋ አናውቅም  እና ቢያንስ ተራ ሟች የሆንን ብዙሃን ሰዎች እና ተራ ሟች ያልሆንን በጣም ጥቂት ልሂቃን  አጭሯን የህይወት ዘመናችንን ተደስተን እንድኖርን ጥላቻን ከህሊናችን አሶግደን ፍቅርን በዓለም ለማንገሥ እንትጋ ። ይህንን ተግባራዊ ካደረግን ምናልባት ከአእምሯችን በላይ የሆነው ፈጣሪ ሊራራልን ይችላል ።…

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop

Don't Miss

Health: ባለቤቴ እኔ የማደርገው አይጥማትም፤ ሁሌ እንጨቃጨቃለን ለምትለው ወንድ 7ቱን ከሚስት ጋር ተስማምቶ የመኖር ጥበቦችን እንካ

“ከባለቤቴ ጋር ስምምነት መፍጠር ተሳነኝ፤ እባካችሁ አንድ በሉኝ” ዕድሜዬ ሰላሳዎቹ