አማራን ላሞራ-የወያኔ ሴራ! May 1, 2013 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ይታረድ ፍሪዳዉ ግባልኝ ከቤቴእነሆ የላም ልጅ ከርጎ ከወተቴየእግዚአብሔር እንግዳ እረፍ ከመደቡእግርህም ይታጠብ በወጉ በደንቡያዳም ልጅ እኮ ነን የእጆቹ ሥራተጫወት ወንድሜ እንግዲህ አትፍራ!እንዲህ እንዳልነበር ባህል ልማዳችንዉጣልን አማራ ጥፋ ከፊታችንጫንልኝ ደራርበህ ዳርግልኝ ላደጋጎጃምና ጎንደር ወሎም ሆነ ቡልጋእየገፈተርከዉ በሰደፍ ባለንጋ!እንዳልተሰዋለት እንዳልተዋደቀላገር ስልጣኔ እንዳልተጨነቀለሰንደቅ ዓላማዉ ሌት ተቀን የተጋኢትዮጵያን ያለ ሰዉ የለዉም ወይ ዋጋ?ዘዉዱን ከክህነት ያስተባበራችሁየቅዱሳን አገር ከቶ ምን አላችሁበግሸኗ ማርያም በክቡር መስቀሉአገር እያጠፉ ወገን ሲበድሉባንዳ ሲዘባነን አርበኛዉ ሲጉላላአይታጠንም ወይ ቅዱስ ላሊበላ?ዓይኑ እስኪታክተዉ ጋምቤላን ሲመራህንዱ ካራቱሬ ሊተክል ሊዘራቻይና ኮሚኒስቱ ስንት ግፍ ሲሰራበገዛ አገራችን ሲኮራ ሲዳራምን ዓይነት ልማት ነዉ አማራን ላሞራይናገር መቅደላ ይፋረደኝ ቋራ!!ከፋኑኤል አበበኒዮርክ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email