የኢሕአግ ሰራዊት በዋልድባ ወታደራዊ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

April 18, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከወያኔው የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ በጠላት ላይ ወታደራዊ የበላይነትን በመቀዳጀት አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈጸምኩ ሲል ለዘ-ሐበሻ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

የድርጅቱ ጋዜጣዉ መግለጫ ” የግንባሩ ሰራዊት በዋልድባ ልዩ ስሙ ሰቋር በተባለ ቦታ በሚያዚያ 8-2005 ዓ.ም የወያኔ አምባገነናዊ አገዛዝ መመኪያ በሆነው የፈጥኖ ደራሽ ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የጠላት ወታደሮችን በመግደል 25 አቁስያለሁ” ካለ በኋላ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9-2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያ መካሄዱንና  በዚሁ እለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት 25 የወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል የተቀዳጀ መቀዳጀቱን ጠቅሶ  በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አትቷል።

“የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረጋቸው አውደ-ውጊያዎች ላይ በድምሩ 46 የፈጥኖ ደራሾችን ከጥቅም ውጭ በማድረግና 64 በማቁሰል የግንባሩ ሰራዊት የተሰለፈበትን ሐገራዊ ተልዕኮውን በመፈፀም በጠላት ላይ ከፍተኛ የሕይወትና የንብረት ኪሳራ በማድረስ አኩሪ የአርበኝነት ጀብድ ፈፅሟል።” ያለው የድርጅቱ መግለጫ ” የግንባሩ ሰራዊት ጥቃቱን በፈፀመበት አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም ስርዓቱ በሚያራምደው የግፍ አገዛዝ ከፍተኛ ምሬትና ተቃውሞ በማሰማት የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊትም የጀመረውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅዖ በማበርከት ሐገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ወደ ግንባሩ ሰራዊት እየተቀላቀሉ ይገኛሉ” ሲል ጋዜጣዊ መግለጫውን አጠናቋል።

የአርበኞች ግንባር በበተነው ጋዜጣዊ መግለጫ ዙሪያ የኢሕአዴግ መንግስት የሚሰጠውን ምላሽ ለማካተት ያደርገነው ጥረት ባይሳካም፤ እስካሁን በይፋ የሰጠው ምላሽም የለም።

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

Go toTop