(ዘ-ሐበሻ) የአቶ መለስ ዜናዊን ለጋሲ እናስፈጽማለን የሚሉት አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ወገኖች ጋዜጠኛና መምህርት ርዕዮት ዓለሙን በ እስር ቤት እያሰቃዩ፤ በ ጡቷ ላይ የወጣውን እጢ እንዳትታከም ምክንያት እየፈለጉ ቢበቀሏትም ጋዜጠኛዋ ግን የዩኒስኮ ጉዋልርሞ ካኖ የአለም የፕሬስ ነፃነት ሽልማት አሸናፊ በመሆን ተሸለመች።
“ይቅርታ ጠይቀሽ እንፍታሽ” “በሰዎች ላይ መስክሪና ትፈቻለሽ” ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች እስር ላይ ባለችበት ወቅት እየደረሳት እርሷ ግን ‘ለእውነትና ለሕሊናዬ እኖራለሁ” በሚል የተፈረደባትን የ እስር ጊዜ ከመፈጸም በቀር ይቅርታ አልጠይቅም በሚለው አቋሟ የጸናቸው ጋዜጠኛና መምህርት መንግስት የሚያደርሳቸውን የተለያዩ ጫናዎች ተቋቁማ ለፕሬስ ነፃነት ላበረከተችው አስተዋጨፅኦ ይህ ሽልማት እንደተበረከተላት የጠቆመው ዩኔስኮ ለዚህ ሽልማት የታጨችውም ተቋሙ ውስጥ ባሉ ገለልተኝኛ የሚዲያ ባለሙያዎች መሆኑን አትቷል።
መንግስት ከዚህ ቀደምም የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እና ጋዜጠኞችን በግፍ ቢያስርም አለም ዓቀፍ ተቋማት ግን በግፍ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያንን ላደረጉት አስተዋጾ ሲሸልሙ እንደነበር ይታወሳል።
የዘ-ሐበሻ ጋዜጣና የዘ-ሐበሻ ድረገጽ አዘጋጆች በጋዜጠኛዋ ሽልማት የተሰማቸውን ደስታ እየገለጹ ለመላው የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ አድናቂ ወገኖቻችንና ለጋዜጠኛ ር ዕዮት ዓለሙ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን።
የመለስ ሌጋሲ አስፈጻሚዎች ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙን በእስር ቤት ቢያሰቃዩም ዩኔስኮ ጋዜጠኛዋን ሸለመ
Latest from Blog
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::
እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!
በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት
ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!
ፋኖ አገዛዙ ላይ ከባድ ጥቃት ፈፀመ /የመቀለ ውጥረትና ታጣቂዎች የፈፀሙት /በኦሮሚያ ተደራጅታችሁ ታጠቁ ተባለ
ፋኖ አገዛዙ ላይ ከባድ ጥቃት ፈፀመ /የመቀለ ውጥረትና ታጣቂዎች የፈፀሙት /በኦሮሚያ ተደራጅታችሁ ታጠቁ ተባለ
አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት
አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡