ኢትዮጵያዊው ላሊሳ ዲሳሳ ባሸነፈበት የቦስተን ማራቶን ቦምብ ፈነዳ

April 15, 2013

ኢትዮጵያዊው ላሊሳ ዲሳሳ ባሸነፈበት የቦስተኑ ማራቶን ማጠናቀቂያ ቦታ ላይ በፈንዱ ሁለት ቦምቦች ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ 3 ሰዎች መሞታቸውንና ከ40 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ታወቀ።

በዚህ ውድድር ላይ ለአሸናፊነት ሲፎካከሩ የነበሩት ገብረ እግዚአብሄር ገብረማርያም እና ላሊሳ ዲሳሳን ጨምሮ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ላሊሳ ይህን ውድድር ለማሸነፍ 2:10:22 እንደፈጀበትም ታውቋል። በውድድሩም ስመጥሩው አትሌት ገ/እግዚአብሄር 3ኛ ወጥቷል።

በቦስተኑ ማራቶን ላይ ከ27 ሺህ የማያንሱ ሯጮች ተሳትፈዋል። ለዚህ ፍንዳታ እስካሁን ኃላፊነቱን የወሰደ ወገን ባይኖርም ፖሊስ ጉዳዩን እየተከታለ መሆኑን ከትንሽ ሰአታት በፊት በሰጠው መግለጫ አስታወቋል። ዛሬ ሰኞ ኤፕሪል 15 ቀን 2013 ከቀኑ 2፡45 አካባቢ ነው ሁለቱ ቦምቦች በሰከንዶች ልዩነት ውስጥ የፈነዱት።
ይህን ቪድዮ ይመልከቱ፦

Medical workers aid injured people at the finish line of the 2013 Boston Marathon following an explosion in Boston, Monday, April 15, 2013. (AP Photo/Charles Krupa)
ኢትዮጵያዊው ላሊሳ ዲሳሳ ባሸነፈበት የቦስተን ማራቶን ቦምብ ፈነዳ 1

 

View slideshow

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

Go toTop