እናት ለነፍሳት ሁሉ የመፈጠራቸው ምስጢርና ምንጭ ናት
እናት ለልጇ ዋሻና ጋሻ ናት
እናት ለልጇ ቀላቢና ተንከባካቢ ናት
2
እናት ለልጇ መመኪያና አለኝታ ናት
እናት ለልጇ ፍቅር ናት
እናት ለልጇ መካሪና አስተማሪ ናት
እናት ለልጇ ሃኪምና ወጌሻ ናት
እናት ለልጇ ጠበቃ ናት
እናት ለልጇ ሁሉም ነገር ናት
ሁሉም ነፍስ ያለው ፍጡር ከእናት ማህጸን የወጣ ነው። ከላይ በምስል የተቀመጠው የወፍ እናትና
የጫጩቶቿን ታሪክ በመከታተል የእናትን ምንነት ትኩረት ሰጥቼ በእናቶች ቀን ይህንን ጽሑፍ
እንዳዘጋጅ ምክንያት ሆኖኛል። የታዘብኩትን ላጋራ።—የእናቶች ቀን