የሀገራችን ብርሃነ ትንሣኤ ጭላንጭሉ እየታዬ ይመስላል፡፡ ሰሞኑን በፋኖ ዙሪያ የምንሰማቸው ነገሮች ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ማስጠሎ ቢሆኑም አንዳንዶቹ ወርቅ ናቸው፡፡ “ቂጣም ከሆነ ይጠፋል፤ ሽልም ከሆነ ይገፋል” የመባሉን ሥነ ቃላዊ ብሂል እያስታወስን ጊዜ የሚያመጣውን በረከተ እግዚአብሔር በተስፋ የምንጠብቅ ብዙዎች መሆናችን ደግሞ ገሃድ እውነት ነው፡፡ እሱን ያመነ ወድቆ አይወድቅምና፡፡
ኢትዮጵያ የነሱ ብቻ የምትመስላቸው፣ መሬቷንም ሆነ በላይዋ ላይ የሚገኙ ሕይወት ያለውንና ሕይወት የሌለውን ነገር ሁሉ እነሱ እንደፈጠሩት የሚያምኑ ከንቱ ወንድሞቻችን በተለይ ላለፉት ዐርባና ሃምሣ ዓመታት ዕድል ገጥሟቸው የአራት ኪሎን ቤተ መንግሥት መቆጣጠር በመቻላቸው ያሳለፍነውና እያሳለፍነው የምንገኘው መከራና ስቃይ በዕንባ ካልሆነ በቃላት ሊገለጽ አይችልም፡፡ ጤናማ አስተሳሰቡንና ኅሊናውን የተነጠቀ ግለሰብም ይሁን ቡድን የመጨረሻውን ትልቅ ሥልጣን ሲይዝ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ከእኛ ከኢትዮጵያውን የበለጠ ሊገነዘብ የሚችል የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ብዙ ጨካኝ መሪዎች፣ ብዙ ሙሰኛ ገዢዎች ገጥመውናል፤ እንዳሁኑ ያለ ልዕለ-ጭራቅ መሪ ግን ገጥሞን አያውቅም፡፡
የሶቪየት ኅብረቱ ጆሴፍ እስታሊን፣ የጀርመኑ ሂትለር፣ የጣሊያኑ ሙሶሊኒ፣ የቺሊው ፒኖሼ፣ የካምቦዲያው ፖልፖት፣ የማዕከላዊ አፍሪካ “ሪፓብሊኩ” ቤዴል ቦካሣ፣ የዩጋንዳው ኢዲ አሚን … እና ሌሎችም የጥንትና የአሁን ምናልባትም የወደፊት ጨካኝ አምባገነኖች ቢዋሃዱ አቢይ አህመድ አሊን የሚስተካከል አጋንንታዊ ተፈጥሮና ይህ ቀረሽ የማይባል ዐረመኔያዊ ባሕርይ ሊኖራቸው አይችሉም፡፡ እነዚህ የተጠቀሱት አምባገነኖች አገርና ሕዝብ ነበራቸው፡፡ የተወሰነ የርህራሄና መንፈስና ምሕረት የማድረግ ዝንባሌም ነበራቸው፡፡ በጥቅሉ ሰው ሰው የሚሸት ተፈጥሮ እንደነባረው መረዳ አይከብድም፡፡ አቢይ አህመድ ግን የጭካኔና የግድያ መናፈስቱን ካወረሱት የሕወሓት ጎምቱ ባለሥልጣናት ሊነጻጸር እንኳን በማይችል ደረጃ በርኩስ መንፈሱ ምሪት ኢትዮጵያን ድባቅ መታት፤ ሕዝቧን በዘርና በቋንቋ በታተነ፡፡ የተላከበት የጥፋት ተልእኮ አካልንም መንፈስንም ማድቀቅ እንደመሆኑ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ አንድም ጤናማ ዜጋ የሌላት እስክትመስል ድረስ ከመቶ ሚሊዮን በላይ የሚገመተው ሕዝቧ በስማም እንደተባለበት ሰይጣን ፈዞና ደንዝዞ በምዕራቡ ዓለም የሚታወቀውን ዞምቤ ሆኗል፡፡ ይህም ጉዳይ ትውልድን ተክቶ ከማለፍ አኳያ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ አእምሮውን ሆዱ ውስጥ የደበቀ ትውልድ፣ ትምህርትን በሆዱ የለወጠ ትውልድ፣ እውነትን በዳቦና በእንጀራ የተካ ትውልድ፣ ሃይማኖቱን በገንዘብ የሸጠ ትውልድ፣ ግደል ሲሉትና ቢሉት “ማንን” እንጂ “ለምን” ብሎ የማይጠይቅ ከሌላው የእንስሳት ዓለምም ሳይቀር የተለዬና በእጅጉ ያፈነገጠ ትውልድ ዛሬ ሀገር ከጅቦችና ዓሣማዎች አገዛዝ ነጻ ብትወጣ ማን ሊረከባት እንደሚችል ነፃ ካለመውጣቷም በላይ ያስፈራል፡፡ እኔ ከዛሬ ይልቅ ነገን እፈራለሁ፡፡ በትምህርቱ ዜሮ፣ በአስተዳደጉና በቤተሰባዊ ዳራው (background) ዜሮ፣ በሞራልና በባህላዊ ዕሤቶች ዜሮ፣ በመግባባትና በማኅበራዊ ግንኙነቱ ዜሮ … በሁሉም ሰብኣዊ ባሕርያት ባዶ የሆነ ሰው ሀገርን እንዲመራ ጠባብ ዕድል ቢያገኝ ምን ሊከሰት እንደሚችል አቢይ አህመድ ብቸኛው ማስረጃችን ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ታኅተ-ሰብዕ (subhuman) በጥቂት ቀናት ውስጥ ቢሊዮነር መሆን ይችላል፡፡ እንዲህም የሚሆነው ለሥልጣኑ ያሰጋኛል ብሎ የሚጠረጥረውን ሁሉ ያላንዳች ርህራሄ በመግደልና በማስገደል፣ ህግን በመጣስና ለራስ የሚስማማ ህግ በማውጣት፣ ሌሎችን ከማንኛውም የጨዋታ ህግ በማውጣት፣ ኢፍትሃዊነትን በማንገሥ፣ ግድቦችንና ማዕድናትን ጨምሮ ሀገርንና የሀገር ክፍሎች በመሸጥ፣ ወዘተ. ነው፡፡
በዚህ ሰዓት ነው በሰሜን በኩል ንፋስ ሲነፍስ እኔም ከደበቡ ይቺን ማስታወሻ መጻፍ የፈለግሁት፡፡ የኔ አካባቢ እጅግ ድንቅ ኢትዮጵያውያንን እንደምታፈልቅ አውቃለሁ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ጄኖሣይድ የታወጀባቸው አማሮች ከገዳዮቻቸው ጋር ተሰልፈው የገዛ ነገዳቸውን ሲያጠፉ ወንድሜ ታዲዮስ ታንቱ ስለአማራ እውነቱን በመናገሩ ብቻ በመጦሪያ የእርጅና ዘመኑ በእሥር ቤት እየማቀቀ ነው፡፡ ከኦሮሞና ከትግሬዎችም ቢሆን ጥቂት የማይባሉ ዜጎች ለኅሊናቸው አድረው ለአማራ ኅልውና እየታገሉ ሳሉ በሚገርም ሁኔታ የአማራ ፋኖ አመራር የነበሩ በጣም የምናውቃቸው ሰዎች ወደአማራ ማረጃ ቄራ እጅ እየሰጡና የመታረጃ ቀናቸውን እየጠበቁ መገኘታቸው የክፍለ ዘመናችን ዕንቆቅልሽ ለመሆን በቅቷል – ሰውን አውቀዋለሁ ማለት ከንቱ ነው ወገኖቼ፡፡ ሰው የሚታመነው በርግጥም ሲሞት ብቻ ነው፡፡ በዚህ ረገድ መማር አለመማርም፣ በልምድና በተሞክሮ መብሰል አለመብሰልም ፋይዳቢስ ነው፡፡ ቀን አይጣልህ ወንድሜ፤ ዘመም አይበልብሽ እህቴ፡፡ ለማኛውም የቄራውን ባለቤቶች የሀሰተኝነትና የአጭበርባሪነት ተፈጥሮ የምንረዳው ደግሞ ሸኔዎች ሲገቡ በማግሥቱ ትላልቅ የፌዴራል ተብዬ ሥልጣን ሰጥተው የወታደር መለዮም አልብሰው በከፍተኛ ደሞሞ እንዳላሰማሩ እነዚህኞቹን በጎች “አራት ኪሎ ሲያምርህ ይቅር፤ በምርኮ እንጂ በመሪነት አታየውም” በሚል ስላቅ ሊጫወቱባቸው ፈልገው “ 4 ኪሎ ፕላዛ” በሚል እዛው አካባቢ የሚገኝ መናፈሻ ፎቶ አንስተው ለቀቁባቸው፡፡ ማፈሪያነት ከዚህ በላይ የለም፡፡ አሳፈሩን፡፡
በመሠረቱ አሁን ከአዲስ አበባ የሚያመልጡበት እንጂ በምንም ምክንያት ቢሆን ወደ አዲስ አበባ የሚገቡበት ጊዜ ላይ አይደለንም፡፡ ስለሆነም እነዚያ ስማቸው በጥቁር ቀለም በታሪክ መዝገብ እንዲሰፍርላቸው የመረጡ አንዳንዶቹ ለሀገራቸው ብዙ የደከሙ ዜጎች “ዐይጥ ወልዳ ወልዳ ጅራቷ ሲቀር ሲጥ አለች” እንዲሉ ሆኖ በዚህን የመጨረሻ ሰዓት ወደጊሎቲን መምጣታቸው ማሳዘኑ አልቀረም፡፡
ከዚህ በላይ ምን እንዳልኩ በውነቱ ብዙም አይገባኝም፡፡ ብዙ ነገር መናገር የሚፈልግ ሰው ጥቂት ሲናገር ተያያዥነትና ምክንያታዊነትም ጭምር ሊጎድለው ይችላልና ይቅርታ ልበል፡፡ ይህን የዐውሬ የኦሮሙማ መንግሥት አስወግደን ግን የጥንቲቷንና ከአሁኑ ጋር ሲወዳደር የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት ያለባትን አንዲት ኢትዮጵያ ለመመሥረት እንታገል፡፡ ሰማንያ አራት ነገድና 84 ቋንቋ ከ200 በላይ ሥነ ልሣናዊ ዘዬዎች (dialects) ባሉባት ሀገር በየመቶ ዓመቱ አዲስ ብሔራዊ ቋንቋና አዲስ ብሔራዊ ትውፊት ለማቆም መሞከር ከጅልነትም ያለፈ ገልቱነት መሆኑን በተለይ ባለፉት ስምንት ዓመታት ስላየነው ጨርሰን ሳንጠፋ ሁላችንም ለማይቀረው ነጻነታችን እንተባበር፡፡ አሁን የምናየው ኦሮምኛንና የኦሮሞን ባህል የማንገሥ ሞኛሞኝ ጥረት አማራን ብቻ ሳይሆን ሌሎቹንም ሁሉ ጨፍልቆ ዱዳ የማድረግ ጅማሮ ነውና ጨርሰን ሳንጠፋ በቶሎ መልክ እናሲዘው፡፡ እንደቀልድ የተጀመረና የትም አይደርስም ተብሎ የሚናቅ ነገር ምን ያህል ጥፋትና ውድመት ሊያስከትል እንደሚችል የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶችን በማየት መረዳት ይቻላል – ኧረ ጎንደርም ገብቷል አሉ፡፡ ቋንቋም ከጉዳይ ተቆጥሮ “የኛ ቋንቋ፣ የነሱ ቋንቋ” በሚል እልህና ጥላቻ የተሞላበት አካሄድ ብዙ ነገር ጠፍቷል፡፡ እኔማ በየትምህርት ቤቶችና በየሆስፒታሎች ስሄድ በማየው ነገር በሀፍረት እየተሸማቀቅሁ በነገው የኦሮሞና የኢትዮጵያ ግንኙነትም ምን ሊከሰት እንደሚችል እያሰብኩ በጭንቀት ማለቄ ነው፡፡ በሦስት ሆሄ ሊጻፍ የሚችል ቃል በአሥር የላቲን ፊደል መደርደሩ ሌላ ጉዳይ ሆኖ 84 ቋንቋዎች በሚነገሩባቸው ሀገር ከህገ መንግሥት ውጪ ገና ለገና አራት ኪሎን ይዣለሁ ብሎ ለቃሉ ይቅርታ ይደረግልኝና ይህን ያህል ማሽቃነጥ ትናንትንና ነገን ያለማወቅ ድድብና የፈጠረው ሌላ ድድብና ይመስለኛል፡፡ ሆ! “ወያኔ ማሪኝ” የሚያስብል ቅብጠት ነው የቀበጡት፡፡ ግዴለም፤ በኔ ይሁንባችሁ ይህም በቅርቡ ይስተካከላል፡፡ ወጪው ግን ብዙ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ብዙ ለቀቅናቸዋ! ክፉኛ ማርጠዋል፡፡
አሁን አፋብን የተባለ ትልቅ ተቀባይነት ያለው የሚመስለኝ አደረጃጀት በአማራው አካባቢ ተፈጥሯል፡፡ አማራ በመሠረቱ እርስ በርስ እየተፋጨ ቀሳጢ በዝቶበት እንጂ ቆርጦ በአንድነት ከተነሣ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለመላው አፍሪካ የሚበቃ ሕዝብ ነው – የዛሬን አያድርገውና፡፡ እናንተ ባታውቁት እኔ አውቀዋለሁ – ቀልዴን አይደለም፡፡ በምልዓትም ሆነ በታሪክ፣ በሥነ ጽሑፍም ሆነ በባህልና በሃይማኖት ከቀደምት ሕዝቦች አንደኛው ነው – ማንም ደንቆሮ ማይም ጊዜ ሰጠኝ ብሎ የሚሞላፈጥበትም የአማራ ጨዋነትና በሃይማኖቱም “ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ቢመታህ ግራህን አዙርለት” እየተባለ ለዘመናት በሰማው ስብከት ሞራላዊ ዕሤቱ ስለታሸ እንጂ ልጨክን ቢል ይሄኔ ማንም እየመጣ አይጸዳዳበትም ነበር፡፡ ነገር ግን የዚህ ሁሉ ባለውለታነቱ ያመጣበት መርገምት ጄኖሣይድ ሆነና በ50 እና 60 ሚሊዮን የሚገመተው ትልቁ ሕዝብ የብሔርኝነትና የዘረኝነት ስሜት የሌለው በመሆኑ እንዲሁም በችግር ወቅት እንኳ የመተባበር ልምዱ ከዜሮ በታች በመሆኑ ስድስት ሚሊዮን እንኳን የማይሞላ ሕዝብ ባለው ንዑሥ ነገደ ሴም እስከመደፈርና በማፌስቷቸው ሳይቀር “አማራንና ኦርቶዶክስን ካላጠፋን እንቅልፍ አይዘንም” የሚል የአቋም መግለጫ እስከማውጣት ደርሰው በእጅጉ አጠቁት – ንቀት ነበር፤ ግን እነሱስ ተጠቀሙ? አልተጠቀሙም ተጎዱበት እንጂ (ደግሞስ ገና ምን አየንና! የዕንባና ደም መለኮታዊ በቀል ቀላል አይደለም – የአሁኖቹን ተዋቸው – እናየዋለንም)፡፡ በሌላም በኩል አማራን ለዚህ ንቀት የዳረገው በውስጡ የሚገኙ ሆዳም ባንዳዎችና ራሱን ከውድመት ለማዳን ሲባል መተባበር ያለመቻል ችግር ስላለበት ነው፡፡ እንጂ ባለፉት 8 ዓመታት በተለይ በአማራ ላይ ያልደረሰ ግፍና በደል አለ እንዴ? አማራ በተረት አንደኛ ይመስለኛል – የቤቱ በር ሳይዘጋ ብዙ ሰዎች ተኝተዋል አሉ፤ ሌሊት ጅብ ይመጣና በሩ ላይ የተኛውን ሰው እግር መጎረዳደም ይጀምራል፡፡ ከውስጠኛው ጥግ ከተኙ ሰዎች አንዱ ነቅቶ ያዳምጥ ነበርና “ ኧረ ምንድነው የሚሰማኝ ድምጽ?” ብሎ ቢጠይቅ በጅብ እየተበላ ያለው ሰው “እባክህን ዝም በል እንዳታስጨርሰን፤ ጅቡ የኔን እግር እየበላ ነው” አለው ይባላል፡፡ አማራ በዚህን ሁኔታ ውስጥ ያለ ሕዝብ ይመስላል፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ ታውቁታላችሁም፡፡ ችግሩ ማወቅ ምንም ማለት አለመሆኑ ነው፤ ሰይጣንም ብዙ ያውቃልና፡፡
እንግዲህ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው ነገሩ – አለዚያ ድንጋይ ነህ ተብሎ መወርወርም አለ ለማለት ነው፡፡ አማራ መነሣት አለበት አሁን፡፡ ሆዳምነትን መጸየፍ አለበት፡፡ ሁሉም ጎራዴና ሠይፍ ይዞ ጦር ሜዳ እንደማይወጣ ግልጽ ነው፡፡ ሜዳውም አይበቃም፤ መሣሪያም አይኖርም፡፡ ነገር ግን በየሚችለው ሁሉ ይሣተፍ፡፡ ጆሮውን ከትግሉ አይለይ፡፡ ሁሉም በየአቅሙ ይሠለፍ፡፡ የታወጀበት የዕልቂት ዐዋጅ ዓለም አቀፍና በፍጹም የማይምረው ነው፡፡ የተራ ጉዳይ እንጂ እንኳንስ አማራ ትግሬም ሆነ ሌላው አይቀርለትም፡፡ ስለሆነም ሌሎቻችንም ከአማራ ጎን እንቁም፤ ጥቅ የጋራ ነውና፡፡ ሌሎቹን እኮ እስኪያንገሸግሸን አየናቸው፡፡ አማራ ላይ የተነሱ ጠላቶች እንቅልፍም ዕረፍትም የላቸውም፡፡ አማራ “ባሪያና ሎሌ ሆኜላችሁ ልኑር” ቢል እንኳን አይፈቅዱለትም፤ ሞቱ ነው የሚያስደስታቸው፤ መጥፋቱ ነው የጮቤ ረገጣቸው ምንጭ፤ ለዚህም ነው የአማራና የኦህዲድ ብልጽግና ችግር በድርድር እንደማይፈታ ሰው ቀርቶ ፈጣሪ እንደሚገነዘበው በበኩሌ የምረዳው፡፡ በአማራና በአክራሪ ኦሮሞ መካከል ድርድርና ስምምነት ከመጠበቅ ይልቅ በጅብና በአህያ ወይንም በነብርና በሚዳቋ መካከል ላለመደራረስ ዕርቅ ወረደ ቢባል ይታመናል፡፡ እነእንትና ድርድር ሲሉ እስቃለሁ – ያልተነካ ግልግል ያውቃል፤ አዲስ አበባ እምብሯ ላይ ስለምኖር ኦሮሙማን ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ አማራን የገጠመው የላም አሸናፊ ነው፡፡ ላም አንዴ ተሳክቶላት በሬን ካሸነፈች ገደል እስከሚገባ ታሯሩጠዋለች እንጂ ምሕረት አታውቅም፤ አሸንፋው አታውቅማ!! ስለዚህ አማራ ያለው ብቸኛ አማራጭ በኅብረት ታግሎ የታወጀበትን የዕልቂት ዐዋጅ መሻርና ኅልውናውን ማረጋገጥ ነው፡፡ ኅልውናው እንደሚረጋገጥ ከደቡብ አባቶች ሲወራ በልጅነት ሰምቻለሁ፡፡ ግን ቀኑ ራቀና የምንጓጓውን የወንድማችንን አማራ ትንሣኤ ሳናይ እንዳንሞት ሰጋሁ፡፡ ሊነጋ ሲል መጨላለሙ ግን ይገርማል፡፡ ቢበቃኝስ ጃል!