ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
ክፍል አንድ
በተከታታይ በሌሎች በእንግሊዝኛ በተጻፉ ሃተታዎች እንዳሳየሁት፤ አብይ አህመድ ኢትዮጵያን በ“ኦሮሙማ” ርእዮት መርህ እና የኦሮሞ ኤሊት ፖለቲካዊ፣ ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ላይ የተመረኮዘ የአገር እንደገና መዋቅር ማጠንቀቅ ዙሪያ ያለውን ጉዞና ተሳትፎ አቀረብኩ።
ባለፉት ሰባት ዓመታት ዐብይ አህመድ አሊ የአገሪቱን ተቋማት ሙሉ በሙሉ ቀይሯቸዋል። ታሪኳንም በመቀየር ላይ ነው። ይህንን የሚያደርገው ብቻውን አይደለም። ከውጭ መንግሥታት ጋር፤ በተለይ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ይህች አገር ግዙፍ ኃብቷን እየተጠቀመችና እንደ ዐብይ አህመድ ያሉ ተባባሪዎች እየፈጠረች (Domestic collaborators) በሱዳንና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ታይቶ የማይታወቅ የእርስ በእርስ ብጥብጥ እየፈጠረች ነው። በኢትዮጵያ የተከሰተው የእርስ በእርስ ጦርነትና እልቂት ከዚህ ሁኔታ ጋር ግንኙነት አለው።
የዐብይ አህመድ ወዳጅ መንግሥታት የዐብይን የአንድ ዘውግ የበላይነት፤ ቢቻል እምነት፤ የሚያዩት ከራሳቸው ጥቅምና እምነት አንጻር ነው። ይህ የኦሮሞ ብሄር የበላይነት መርህ ያስከተለው አሉታዊ ውጤት ተዘርዝሮ አያልቅም።
በተመሳሳይ ባለፉት አምሳ ዓመታት፤ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር (ህወሃት) በማኒፌስቶው ያወጀው አማራ ጠል ርዮት ስር ሰዶ እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏል። ህወሃት አቅሙን ያጠናክረው በራሱ ችሎታና ቁሳቁስ ብቻ አይደለም። አሜሪካን ጨምሮ የውጭ ድጋፍ ስለነበረው ነው።
ይህ መርህ እስካልተሳበ ድረስ በአማራውና በትግራዩ ጥንታዊ ሕዝቦች መካከል ያለው ግንኙነት ሊታደስ አይችልም። በኔ ግንዛቤ፤ ይህ ግትር የፖለቲካ መስመር (inflexible doctrine) ለማንም አያዋጣም። ሁለቱ ሕዝቦች በእርቅና ሰላም እንዲኖሩ ያልተቆጠበ ጥረት የምናደርግበት ወቅት አሁን ነው።
የኢትዮጵያ መለያ ምንድን ነው?
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ኃብቷ፤ በጀኦግራፊ አቀማመጧ፤ በሕዝብ ስርጭቷ፤ በእምነት ተቻችሎ የመኖር ታሪኳ፤ በጥንታዊ ሥልጣኔዋ፤ ለዓለም ህብረተሰብ እና ለጥቁር ህዝቦች ባቨረከተችው ሚና ወዘተ እጅግ በጣም የምታኮራና የመላው ዓለምን እውቅና ያገኘች አገር ናት። የተባበሩት መንግሥታትን፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ከመሰረቱት መካከል አንዷ ናት። በደቡብ ኮርያ፤ በኮንጎና ሌሎች ቀጠናዎች ጀግኖች ልጆቿ የተጫወቱትን ጀብዱና ሚና ታሪክ መዝግቦታል።
እኛ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የትም አገር ብንኖር ራሳችንን ከፍ አድርገንና ኮርተን ለመናገር የቻልነው ባካበትነው ታሪካችንና መለያችን ነው። ይህ እሴት የሁላችንም መሆኑን አንርሳው። ካወቅንበት፤ ይህ ብቻ ሊሰበስበንና ተቻችለን እንድንኖር ያስችለን ነበር። በስደት ከሌላው ጋር አብረን ለመኖርና ለመስራት ከቻልን፤ ለምን ባገራችን አልቻልነም?
ኢትዮጵያ ይህንን አስደናቂ ሁኔታ ተጠቅማ ራሷን ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ነጻ አላደረገችም። አዲሱ ትውልድ በጋራ የሚጋራቸውን ((commonalities) ወደ ጎን ትቶ በዘውግ ልዩነቶችና በግል ጥቅም ላይ እንዲረባረብ ከፍተኛ ጥረት ተደሯጓል። የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ የሚያደርገውም ይህንኑ ነው። ድለላና ሺንገላ በሺ በሺ ነው።
ኢትዮጵያ ዘላቂና ፍትሃዊ ልማት ልትመሰርት ያልቻልቸበት መሰረታዊ ምክንያት የመንግሥት ስርዓቱ ከፋፍለህ ግዛውና ብላው ስለሆነ፤ ብሄርተኛነት ስለ ነገሰና ተከታታይ ገዢዎች ሕዝብንና አገርን ተቀዳሚ ባለማድረጋችሀው ነው የሚል እምነት አለኝ። የአገሪቱን ኃብትና ንብረት፤ ተቋማትና ፖለቲካ ማርከው ተስፋ ያላትን ኢትዮጵያን ተስፋ ቢስ አድርገዋታል።
ገዢዎቿ ሕዝቡን ንቀውታል። ምንም ሊያደርግ አይችልም የሚል እምነት አላቸው። ሕዝቡ በቃኝ ብሎ በአንድነት ቢነሳባቸው ምን እንደሚሉ እገምታለሁ። ማረኝ? ሸሺገኝ? ዐብይ አህመድ አማራውንም፤ ኦሮሞውንም ሲሳደብ ንቀቱን ያሳያል። ህዝቡ ደፍሮ ልትከፋፍለኝ፤ ልትንቀኝና ልትጨቁነኝ አልፈቅድልህም፤ አትችልም ማለት አለበት።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሳሳተ ትርክት ምርኮኛ ሆኗል። አንድ ምሳሌ ላቅርብ። የአማራው ሕዝብ ጉልህ የሆነ የስልጣኔ ሚና ተጫውቷል—ፊደል፤ የቀን አቆጣጠር፤ ህብረ-ብሄራዊነት፤ አብሮና ተዋልዶ መኖር፤ የአገር ፋቅር፤ ታታሪነት፤ ነጻነት፤ እርሻ ወዘተ። ይህንን ጉልህ ሚና መጫወዎቱ ባለውለታ ሕዝብ ነው ሊያስብለው ይገባ ነበር። የሆነው ግን የተገላቢጦሽ ነው። ሌላው ቀርቶ፤ ይህ ሕዝብ ለአገሩ ነጻነትና ሉዓላዊነት ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ መኖሩ ለድህነት እንደ ዳረገው እውቅና አልተሰጠውም። አብዛኛው አማራ ድሃ ነው። ድሃ ሆኖ ግን አገሩን ያልታደገበት ወቅት የለም።
ኢትዮጵያ እንደ አንዲት ህብረ-ብሄራዊና ሉዐላዊት አገር እንድትቀጥል ከተፈለገ ጠባብ ብሄርተኝነት፤ የብሄር ትምክህተኛነት፤ የአንድ ብሄር የበላይነት አመለካከት፤ አፍራሽ ትርክትና የኔ ብቻኛነት፤ አድሏዊነት፤ ሌብነት፤ ሙሰኛነት፤ ህገወጥነት፤ ማንኛውም ሽብርተኛነት እና የውጭ መንግሥታት ጣልቃ ገብነት መወገድ አለባቸው። ይህ ሃላፊነት የሁሉም ነው። ለዚህ ያስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል። በዚግነት መብት የሚያምንና ለሕዝብ ተገዢ መንግሥት ያስፈልጋል።
ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ደረጃ የመቀጠል እድሏ ኢምንት ሆኗል። የብሄር ፌደራል ስርዓቱ ለሰላሳ አራት ዓመታት ተሞክሮ እንኳን ብልጽግና ሊያስከትል፤ ሰላምና እርጋታም ምኞት ብቻ ሆነዋል። ለሆዱ አዳሪው ግዙፍ ሆኗል። ህገወጥነት መረን ለቋል። ይህንን ድክመት የውጭ ኃይሎች አባብሰውታል።
ኢትዮጵያ ዜጎች ከቤታቸው ወጥተው በሰላም ሊመለሱባት ያልተቻለባት አገር ሆናለች።፡ የፈለገውን ስያሜ ብትሰጧት፤ ሊካድ የማይቻለው ሃቅ ኢትዮጵያ በመውደቅ አፋፍ ላይ የምትገኝ ሲኦል ሆናለች።
እኔ ኢትዮጵያ እንዳትበታተን፤ እንዳትወድቅ እና እንድትበለጽግ ከሚፈልጉት መካከል አንዱ ነኝ። ለመበልጽግ ሁሉንም ዜጎቿን በእኩልነትና በፍትህ የሚያስተዳድርና የሚያገለግል መንግሥትና አመራር ያስፈልጋታል። ፍትህ ከሌለ ሰብአዊ መብት ሆነ እኩለነት አይታሰብም። ፍትህ ከሌለ ስላምና እርጋታ አይኖርም። አማራው የሚታገለው ለፍትህ ነው። ለእኩልነት ነው።
ለኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፋንታ የሚያገባው አማራውን ብቻ አይደለም። ይህ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ተወቃሽና ተጠቂ እንጅ ተጠቃሚ አይደለም። ሆኖም፤ የዚች ታሪካዊ አገር የወደፊት ሁኔታዋ ያገባዋል። አማራው ከኢትዮጵያ ውጭ ሌላ አገር የለውም። አፋሩም፤ ጉራጊውም ወዘተ። የአማራው ሕዝብ ከሁሉም ብሄረሰቦች ጋር ተጋብቷል፤ ተጋምዷል። የኢትዮጵያን ነጻነት፤ ግዛታዊ አንድነት፤ ተከታታይነት ከአማራው ሕዝብ እኩልነት፤ ተሳትፎና የፖለቲካ ሚና ውጭ ለማየት አልችልም።
እኛ በኢትዮጵያ እድገትና ልማት ከፍተኛ ተስፋ ይዘን የቆየን ግለሰቦችና ስብስቦች ጠባብ ብሄርተኞችን፤ የብሄር ትምክህተኞችን፤ ልሂቃንንና ግንባሮችን በመምከር፤ ዲሞክራሳዊ ህብረብሄራዊነት ያዋጣል፤ ከሌሎች አገሮች ልምድ ተማሩ—ናይጀሪያ፣ ሩዋንዳ፤ ማላይዢያ፤ ኢንዶኔዢያ ወዘተ ብንል ያዋጣል።
ልማትና ህብረቤራዊነት አይጻረሩም። ላወቀበት ፍትሃዊ የመንግሥት ስርዓት ባለበት አገር፤ ህብረ ብሄራዊ አገር ወርቃማ የእድገትና የልማት እድሎች አሉት። ከአኟኩ ከጉራጌው፤ ከአማራው ከኦሮሞው፤ ከሶማሌው ከትግራዩ ወዘተ የሚያገኘው ጥቅም አለ: (untapped complementarities).
አሜሪካን ጠንክራና ሃብታም አገር ያደረጋት ህብረ ብሄራዊነት አይደለም? የፌደራል ስርዓቱ ይህንን ያንጸባርቃል።
ግንባሮች በዚህ አያምኑም። ግንባሮች ተገንጣዮች ሰለሆኑ የሚወክሉትን ሕዝብ ከሌላው ለይተው አዲስ አገር ለመመስረት ያላቸው ፍላጎት ተባብሷል ለማለት እችላለሁ። ግንባር ብሎ ኢትዮጵያን ለመታደግ አይቻልም። ግንባር ብሎ ሰላምና እርጋታን ስኬታማ ለማድረግ አይቻልም። ግንባር ብሎ አብሮነትና ተቻችሎ መኖር አይቻልም።
በተጨማሪ፤ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች፤ ግብፅ፤ ካታር፤ ዩኤኢ፤ ሳውዲና ሌሎች በቀጥታም ሆነ በምስጢር ኢትይዮጵያን ለራስቸው ጥቅም ተገዢ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።
ዐብይ አህመድ አሊ የእነዚህ መንግሥታት ተጠሪና አገልጋይ መሆኑን ወደፊት ታሪክ ያጋልጠዋል። ለአሜሪካ “እቀላለሁ” ማለቱን አንርሳ።
የአማራው ትኩረት ምንድን ነው?
በአሁኑ ወሳኝ ወቅት፤ የአማራው ሕዝብ ዋና ትኩረት ራሱን ከእልቂት መከላከል ነው። አማራ ነን የምንል ግለስቦችና ስብስቦች አንሳሳት። ሌላ አጀንዳ እየፈጠርን አማራውን አንበታትነው። ግራ አናጋባው።
የአማራው ሕዝብ ራሱን ካዳነ ብቻ ነው ክሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ለማዳን መረባረብ የሚችለው። አማራውን በጎጥና ሌላ ይገባኛልነት መበታተን ለማንም አያዋጣም።
የአማራው ጠላት አማራውን የሚጨፈጭፈው ጎንደሬ፤ ወሎየ፤ ሸየ፤ ጎጃሜ፤ ወለጌ፤ ሃረሬ ወዘተ ስለሆነ አይደለም። በአማራ ማንነቱ ነው። በእምነቱ ኦርቶዶክስ፤ ሙስለም፤ ካቶሊክ. ፖሮቴስታንት እና ሌላ ሊሆን ይችላል።
የአማራ ፋኖ አንድነትና ውህደት አስፈላጊ የሚህንው በዚህ ምክንያት ነው። ውህደት ኃይል ነው።
የሃሰት ትርክት ሲደጋገም እውነት ይመስላል።
የሃሰት ትርክት አሉታዊ ውጤቱን እያየን ነው። ይህ ትርክት አገር አፍራሽ ነው። በአማራው ሕዝብ ላይ የሚካሄደውን ዘግናኛና በዓለም የወንጀል ፍርድ ቤት የሚያስከሥስ በሰብአዊ ፍጥረት የሚካሄድ እልቂት እና የሴቶች ድፍረት ወንጀል ብቻ ብንመለከት፤ ቢቢሲ ከዘገባቸውና ካጋለጠው በላይ ነው። ከመቶ ሺህ በላይ የአማራ ሴቶች ተደፍረዋል። የደፈራቸው የዐብይ አህመድ/ብርኑ ጁላ ኦነጋዊ ወታደር ነው።፡
የሰሜኑ ጦርነት ተብሎ በተሰየመው ዘግናኝ ጦርነት ከስድስት መቶ ሺህ እስከ አንድ ሚሊየን ንጹህ ወገኖቻችን ተጨፍጭፈዋል። የጦር ወንጀል ተካሂዷል ማለት ነው። ለዚህ እልቂት ተጠያቄ የሆነ ባለሥልጣን የለም። የህወሃትን ዘግናኝ ማኒፌስቶ የሚያስተናግዱት ግለሰቦችና ስብቦቾ ለምን በዚህ እና በዐብይ አህመድ የዖሮሙሟ አጀንዳ ላይ አይረባረቡም?
ጠባብ ብሄርተኛችና የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ በጋራም ሆነ በግል ብዙ ሽህዎች አማራዎች ጨፍጭፈዋል፤ አሁንም እየገደሉ ነው። በአሩሲ የተካሄደው የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ግድያ ከዚህ ዘውግና እምነት ተኮር እልቂት ጋር ቀጥታ የሆነ ግንኙነት አለው። በኔ ግምገማ የዐብይ አገዛዝ እጁን ያላስገባበት መፈናቀል፤ የሴቶት መደፈር፤ እልቂትና ውድመት የለም።
ንጹሃንን እየገደሉ ሲቶችን እየደፈሩ፤ ሃብትን እየሰረቁ፤ ሙስናን እያስፋፉ፤ መሰረተ ልማትን እያወደሙ፤ አገርን እያፈረሱ፤ ውንብድናን ቸል እያሉ፤ አለመረጋጋትን ሁሉ ጊዜ የሚሆን ጉዳይ ነው እያሉ ወዘተ የተለመደ ( Normalization of poor, repressive and corrupt governance) ማድረግ የኢትዮጵያ ሃገር መንግሥት መለያ ሆኗል።
የፈለገውን አይነት የዘላቂ እድገትና ልማት ሞዴል፤ ፍኖተ ካርታ ብናቀርብ ስርዐተ መንግሥቱ ካልተቀየረ “ላም አለኝ በሰማይ” እንዳይሆን እሰጋለሁ። አማራጮችን ማቅረብና ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብና የፖለቲካ ባከድርሻዎች ባለቤት እንዲያደርጓቸው ማድረግ ተገቢ ነው። ለውጥ የማይቀር ሂደት ነው። ጥያቄው፤ ድርጅት፤ ጠንካራ አመራር እና የሕዝብ ባለቤትነት ነው።
እኛ መብታችን ተከብሮልን ውጭ የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ይህንን ዘግናኝ ወንጀል የሰሩትን ባለሥልጣናት በሃለፊነት የመጠየቅ ግዴታና ሃላፊነት አለብን። ይህ ግዴታ ያማራው ብቻ አይደለም። ቢያንስ ቢያንስ ያለ መሰልቸት አቢቱታ የማሰማት ግዴታ አለብን።
የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር እና ብሄርተኞች በኦሮሞ ብሔራዊ ንቅናቄ ውስጥ ጥቅም እንዲያገለግሉ የሚጠቀሙት መሳሪያዎች ልዩ ልዩ ቢሆኑም፣ የሚፈልጉት ዋና ግብ—የኃይልና የሀብት ማዛወር—ስልት አንድ ነው። ይህ ሁኔታ በትግራይ ብሔራዊ ንቅናቄ ውስጥም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው።
የምጠይቀው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ማን ይወክላቸዋል? የሚለውን ነው።
ለለ መገንጠል የሚያስተጋቡት ብሂል መሬቱም፤ ማእድኑም፤ ከተማውም (አዲስ አበባ፤ ድሪዳዋ)፤ ወንዙም፤ የባህር በሩም፤ ግድቡም ጋምቤላም፤ ቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝም፤ ወሎም፤ ሌላውም የኛ ነው የሚል ነው።
ኦሮምያ የሚባል አዲስ አገር ቢመሰረት ከጎረቤት ክልሎችና አገሮች ጋር የዘላለም ጦርነት ይካሄዳል ማለት ነው። ምክንያቱም፤ ይህ ጠባብ ብሄርተኛነት አብሮ የሚጓዘው ከተስፋፊነት ጋር ነው። ተስፋፊነት ቀይ መስመር የለውም። በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተስፋፊነት አያዋጣም።
በተመሳሳይ፤ በዘዲና በኃይል አሰላለፍ ቢለያዩም የትግራይ ኢሊቶችና ፖለቲከኞች የሚጋሩት መሰረታዊ ጉዳይ አንድ ነው። ወልቃይት፤ ጠገዲ፤ ጠለምትና ራያን ወደ ታላቋ ትግራይ ማጠቃለል ነው። አማራው መብትና እምቅ ኃይል እንዳለው ረስተውታል።
የኦሮሞ ኤሊት እንቅስቃሴን የሚያቀናብረው “ኦሮሙማን” ነው። ይህ ርዮትና አስተሳሰብ ታሪካዊ መሰረት አለውና ማስታወሱ አስፈላጊ ነው። ዱብ እዳ አይደለም።
ሮማን ፕሮቻዝካ በ1935 ዓ.ም. ባወጣው Abyssinia: The Powder Barrel መጽሐፍ ዛሬ ላለው የብሔር ፖለቲካ መሠረት ነው። እንዲህ ብሎ ገጽታ ሰጠ፦
“በኢትዮጵያ ውስጥ በብዙ ቋንቋ፣ በብሔርና በእምነት የተለያዩ ብዙ የሕዝብ ቡድኖች የሚኖሩ ቢሆንም፣ ትንሺ ቁጥር ባላቸው በአቢሲናዊያን (አማራ) በመታሰር ተገዥ ሆነው ተይዘዋል…” የከሰሰው አማራውን ነው።
ይህ የፋሺስቶችን ዓላማ የሚጋራና እንዲስፋፋ የሚመኝ ደራሲ “አቢሲኒያዊ” የሚለውን ቃል የሚጠቅሰው አማራው —ከነጭ ኮሎኒያል ተግዳሮት ጋር በማያሻማ ደረጃ ቅራኔ ያለውና ቅኝ ገዢዎችን የሚታገል፤ ለመላው ዓለም የጥቁር ሕዝብ ነጻነት ተምሳሌት የሆነውን ሕዝብ ነው። ለአማራው ሕዝብ ነጻነቱ ቀይ መስመር ነው። አንጡራ መሬቶችም እንዲሁ።
አማራው የመላው ጥቁር ሕዝብ ባለውለታ ነው ያልኩት ለዚህ ነው።
እንደገናም እንዲህ ይላል፦
“ኢትዮጵያ በብዙ ቋንቋዎች፣ በብዙ ሃይማኖቶችና በብዙ ብሔሮች ተሞልታ ስለሆነ፣ የተገዙት ሕዝቦች ራሳቸውን ለማዳን የ‘ራስን አስተዳደር፤ የራስን አገዛዝ’ መብት መኖሩን ይጠይቃሉ…” የመጠየቅ መብት አላቸው።
ዛሬ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ውስጥ ያለው የ“ራስን መንግሥት የመያዝ መብት፤ የመገንጠልና እና የራስን መንግሥት የመፍጠር” መብት ከዚህ የተወሰደና የመጣ ነው። ሰብሳቢውና ወሳኙ ጥያቄ ከማንኛው ወገን ጭቆና ነጻ ለመውጣት? የሚለው ነው።
ራስን በራስ ማሳተዳደር ስብአዊ መብት መሆኑ አያከራክርም። ማንኛውም ብሄረሰብ በራሱ ቋንቋ የመናገር መብት አለው።የራሱን ባህል የመጠቀም መብት አለው። የተፈጥሮ ኃብቱ ተጠቃሚነት መብት አለው። ሰብአዊ መብቱን የማስከበር መብት አለው። ይህንን መብት በሰላም ስኬታማ ለማድረግ ካልቻለ በትጥቅ ትግል የማስከበር መብት አለው።
አከራካሪውና ከተከታታይ የተሳሳተ ትርክት የተቀዳው ቁም ነገር “የአንድ ብሄር ጭቆና አለ” የሚለው ነው።
አገረ መንግሥት መመስረት ጭቆና ሊሆን አይችልም። አገርን ከውጭ ወረራ መታደግና ነጻነትን ስኬታማ ማድረግ ጭቆና ሊሆን አይችልም፡ ስልጣኔን ማስፋፋት ጭቆና ሊሆን አይችልም። ከሌላው ጋር ተዋልዶና ተጋምዶ አብሮነትን ማጠናከርና አገርን መታደግ ጭቆና ሊሆን አይችልም። ትምህርትን ማስፋፋት ጭቆና ሊሆን አይችልም። አዲስ አበባን መዘመን ጭቆና ሊሆን አይችልም። ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ከፍ እንድትል ማድረግ ጭቆና ሊሆን አይችልም። ለኔልሰን ማንዴላ ድጋፍ መስጠት ጭቆና ሊሆን አይችልም። የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን መመስረት ጭቆና ሊሆን አይችልም ወዘተ.
የአማራው ሕዝብ የኢትዮጵያን ሃገረ መንግሥት ለመመስረትና የአገሩን ሉዓላዊ መብትና ዳር ድንበር ለመታደግ ያደረገውን ተጋድሎ ታሪክ መዝግቦታል። ባለውለታ ሕዝብ ነው የምለው ለዚህ ነው። እኛ አድርባይ ሆነን ካልተቀበልነው በስተቀር፤ ይህንን አስደናቂ ታሪክ ለመቅረፍ አይቻልም። በተገላቢጦሽ ይህንን ቅኝ ገዢነትና ጨቋኝነት ብሎ መክሰስና መወንጀል ስህተት ብቻ ሳይሆን ድንቁርና ነው። የአማራውን የሥልጤኔ ሚና ለማፍረስ ነው። የአማራው መብት መከበር ከኢትዮጵያ ዘላቂነትና ዘላቂ ጥቅም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው።
ኢትዮጵያን እንታደግ ካልን የአማራውን ባለውለታነት እንቀበል።
የራስን መንግሥት መያዝ መጠሪያው ምንድን ነው?
ራስን ማስተዳደር ከመገንጠል መብት የተለየ ነው። ራስን ማስተዳደር ሰብአዊና ዲሞክራሳዊ መብት ነው። የብሄር ነጻ አውጭ ግንባር ብሎ ራሱን ከለየ ኃይል ይለያል። ግንባር ፍጹም መለያ ነው። ጠላት አለው። ግንባር የሆነበት ምክንያት ጠላት ስላለው ነው።
ሮማን ፕሮቻስካ የአማራው ብሄር ጨቋኝ ነው ያለውን እናስታውስ። ጭቆናውን የማይቀበሉ ብሄረሰቦች ያላቸው አማራጭ ራሳቸውን ከጭቆና ነጻ ማወጣት ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ነው የደረሰው። The right to self-determination including secession የሚለው መርህ ማለቴ ነው።
የራስን መንግሥት የመያዝ መብት የሚጠየቀው በምን ምክንያት ነው?
በአስተዳደር በደል፤ በግፍ፤ በጭካኔ፤ በፖለቲካና በአስተዳደር ብልሹነት፣ በሕገወጥነት፤ በሌብነትና ሙሰኛነት፤ በሀብት መከፋፈል ውስንነት፣ በመብት መከለልከል፣ በአድሏዊነት፤ በፍትህ መበከል፤ በህገወጥነት፤ በከፋፍለህ ግዛውነት፤ በተረኝነት እና በአእምሮ መታወክ የተነሳ ሊሆን ይችላል። እነዚህ ችግሮችና ተመሳሳዮች በኢትዮጵያ ስር ሰደዋል። ምክንያቶቹን መገንዘብ አስፈላጊ ነው።
እነዚህ ግፎች ነበሩ ወይንስ አልነብሩም? የሚለው አከራካሪ ሊሆን ይችላል። እንኳን ህብረብሄራዊ አገሮች፤ ጣልያኖችም፤ ጀርመኖችም፤ ስፓኒያርዶችም፤ ቻይኒሶችም ወዘተ እርስ በእርሳቸው ተጋድለዋል። ይህ እንዳለ ሆኖ፤ የፈለገውን ያህል ብንከራከር ጎራ የያዙ ኃይሎች ሊቀበሉት የሚችሉት መልስ ለመስጠት አንችልም። ጭፍንና ዝግ ክርክር ነው የሚሆነው።
ትርክቱ ስር ሰዷል፤ ተከታይ ፈጥሯል። ተጠቃሚ ፈጥሯል። የውጭ ደጋፊ አለው። መካከለኛውን መንገድ (መቻቻልን) አያስተናግድም። የምመክረው ወደ መቻቻል እንሸጋገር የሚለውን መርህ ነው።
የአማራው ሕዝብ ለኢትዮጵያ ስልጣኔ፤ ብሄራዊ ነጻነትና ዓለም አቀፍ እውቅና መሪ ሚና መጫወቱን ታሪክ መዝግቦታል። ይህ ሚና በአንድ በኩል ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ ኩራት ሲሆን፤ ለቅኝ ገዢዎችና ለአገር ውስጥ የብሄር ግንባሮች ግን ጠብ ጫሪነትን፤ ቂም በቀልነትንና ጥላቻን ፈጥሯል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ በተከታታይ ከደርግ መንግሥት ጀምሮ እስከ ኦህዴድ ብልጽግና መንግሥት ድረስ በመጭፍጨፍ፤ በመሳደድ፤ በመራብ፤ በመታሰር፤ በመፈናቀል፤ በመሰደብ ወዘተ ላይ ይገኛል። ጭካኔው ስለበረታበት ራሱን ከእልቂት ለማዳንና አጽመ ርስቱን ለመመለስ ቀን ከሌት ይታገላል። በትግሉ ውስጥ ደግሞ፣ ሰርጎ ገቦች፤ ሆዳሞች፤ ከሃዲዎች እንዳይተማመን፤ እንዲተራመስና እርስ በርስ እንዳይተማመን ጠንክረው ይሰራሉ።
ለዚህ ትርምስ መሰረት የሆኑት ብዙ ናቸው። በመንግሥት ደረጃ የሆነውን ማስታወስ ተገቢ ነው። ደርግ ሥልጣን ሲይዝ እድንዲህ የሚል መፈክር ሰምቸ ነበር “ያለ ምንም ደም፤ ኢትዮጵያ ትቅደም።” ትንሽ ሳይቆይ የመንግሥቱ ኃይለማሪያም ቡድን ወደ ጭፍጨፋ ተሸጋገረ። የገባውን ቃል በላው። የኢትዮጵያን ብርቅ መሪዎች፤ ምሁራን፤ መኮንኖች ወዘተ ጨፈጨፋቸው። ንጹሃንን መግደል የተለመደ ሆነ። መንግስቱ ኃይለማሪያም ተሰደደ።
በተመሳሳይ፤ ዐብይ አሕመድ የገባውን ቃል ሁሉ በልቶታል፤ ክድቶታል። ሁለቱም መሪዎች ተመሳሳይነትም፤ ልዩነትም አላቸው ማለት ነው። በጭካኔና በጭፍጨፋ ተመሣሳይ ናቸው። አገርን ለአደጋ በማጋለጥ ተመሣሳይ ናቸው። በሃገር ፍቅር የደርግ መንግሥት ሊተች አይችልም። የሃገር ፍቅር ሲባል ግን ህዝብን ካላፈቀረ ከንቱ ነው።
በመንግሥት ደረጃ የአማራውን ዘውግ ለይቶ ታሪክ ሲጠቅሰው የሚኖረውን ጭካኔና ጭፍጨፋ የሚያካሂደው ግን ዐብይ አህመድና የሚመራው የኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ነው።
በማንኛውም መስፈርት ስገመግመው እንዳሁኑ በአማራው ሕዝብ ላይ ስርዓት መር፤ መንግሥት መር የሆነ ተከታታይ ጭካኔና እልቂት ተካሂዶበት አያውቅም ለማለት እችላለሁ።
ይህ ጭካኔ የሚካሄደው በሁሉም ዘርፍ ነው፦ ትምህርትን፤ ሃብትን፤ ልማትን፤ ቤትን፤ እምነትን፤ ባህልን ጨምሮ። የዚህ ፍጹም የሆነ የጸረ-አማራ ዘመቻና አማራውን ለማጥፋት የሚደረገው ጥቃትና ጦርነት አሁን አለመጀመሩን ታሪክ ያወሳል። ብዙ ሽህ ዓመታት ይሆነዋል። ምክንያቶቹ ግን የተለያዩ ናቸው። አንዴ በውጭ ጠላቶች፤ አንዴ በሃይማኖት፤ ሌላ ጊዜ በውስጥ፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በቅንጅትና በትብብር። የሚጋሩት እምነትና ስልት ጸረ-አማራነት ነው።
ጸረ-አማራነትን በተናጥል አላየውም። ጥናቶችና ምርምሮች የሚያሳዩት ታሪካዊ ሂደት አለ። በአስራ ስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን (በግራኝ ወረራ) ስንት ብሄረሰቦች/ ነገዶች ጠፉ? ብለን ብንጠይቅ እንደ ጋፋት ያሉ ሃያ ተጨፍጭፈው መሬታቸው ተነጥቋል፤ ማንነታቸው የውሃ ሽታ ሆኗል። ይህ አሰቃቂ ሁኔታ በአሁኑ ወቅት እየተደገመ ነው። ጉራጌው፤ አኗኩ፤ ወላይታው፤ ቦሮምያ የሚኖረው አማራ ወዘተ።
የአማራው ጭፍጨፋ ከመሬት የበላይነት ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንነት አለው። ኦሮሞ ያልሆነውን ሁሉ እየለዩ ከአዲስ አበባ ሲያፈናቅሉት ምን ሊባል ይቻላል? አማራው በሁሉም ዘርፎች እንዲማክን የሚደረግበት መሰረታዊ ምክንያትም ይኼው ነው።
እኔ የማቀርበውን ትንተናና ምክረ ሃሳብ አንቀበልም የምትሉ እንዳላችሁ አውቃለሁ; መብታችሁ ነው። የዐብይ ኦህዴድ ብልጽግና መር አደጋዎች ያስከተሉት ግፍ፤ በደልና አገር አፍራሺነት የውጭ ሜድያዎች እየዘገቡት ነው። ከእነዚህ መካከል የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን December 1, 2025 እና ቢቢሲ (November 2025 ያወጡትን ብቻ ልጥቀስ። “Inside Ethiopia’s Fano insurggency—photo essay” ጋርዲያን የአማራ ፋኖ የትጥቅ እንቅስቃሴ የጀመረበትን ምክንያት በግልጽ አስቀምጧል።
የአማራው ሕዝብ በተከታታይ አምባገነን መንግሥታት በማንነቱ ተለይቶ ከፍተኛ ግፍና በደል ተከሂዶበታል። እልቂት (Genocide) ተፈጽሞበታል። ሰላማዊ ሰልፍና አቢቱታ ቢያቀርብም ሰሚ አላገኘም። የሰሜኑ ጦርነት ካቆመ በኋላ ዐብይ አህመድ አሊ በአማራው ሕዝብ ላይ አስቸኳይ አዋጅ አውጆ ጦርነት ክፈተበት።
የአማራው ወጣት ትውልድ ይህንን አደጋ ዝም ብሎ አላየውም። ዘጋርዲያንና (December 2025 እና ቢቢሲ(November 2025) በሰጡት አስተማማኝ መረጃዎች እደመድማለሁ። ”The situation worsened when the government announced the dismantling of regional special forces, largely consisting of Amhara fighters. This was perceived as a direct threat to their security in a country where ethnic tensions run deep. The Amhara, Ethiopia’s second-largest ethnic group, have been victims of massacres in recent years, particularly in areas where they are a minority. These atrocities, often carried out by insurgents from other ethnic groups – Tigrayans or Oromos – have rarely been punished by the government, fuelling hatred and trauma. Meanwhile, the Fano are also accused of multiple abuses and ethnic cleansing in Tigray, particularly in Wolkait and Raya, territories they annexed during the war.” ‘
በተመሳይ ብቢሲ 18 November 2025 ያወጣው ዘገባ ይዘቱ እንዲህ የሚል ነው።፡ አንዲት የአማራ ወጣት ሴት እንዲህ ብላለች.. “እንደዚህ ከሚያዋርዱኝ ቢገድሉኝ እመርጥ ነበር.”’It would have been better if they’d killed me’: A forgotten war destroying women’s lives” 18 November 2025.
“The Ethiopian army was carrying out searches of homes in the Amhara region on 5 January this year, as part of a crackdown on a growing rebellion launched by local militias known as Fano. Enat says three men, dressed in army uniform, entered her home in South Gondar and began asking questions about her family background and whether Fano fighters had visited the beer hall where she worked.—After asking questions about her family background, Enat says the soldiers began insulting her, then threatened her niece with a gun when the little girl started crying. Enat says one of the soldiers then raped her in front of her niece while the others kept guard.
አስቡት፤ እባካችሁ ብላ ብትማጸንም ደፈሯት። “I begged them not to hurt me. I called on the saints and begged them. But their hearts didn’t pity me. They violated me.”
ቢቢሲ እንዲህ ብሏል። “Thousands of reports of rape and assault” ተካሂዷል።
“Enat, who is from the Amhara ethnic group, the second largest in Ethiopia, is among thousands of women believed to have been sexually assaulted and raped since the conflict between the Ethiopian army and Fano started in August 2023.
Sexual violence in the region is largely undocumented, but the BBC has collated data which shows there have been thousands of reports of rape between July 2023 and May 2025, with victims as young as eight and as old as 65.
የዐቢይ ወታደሮች እንደዚህ ያለ ወንጀል እየፈጸሙ ነው።
የዐብይ መንግሥት አማራው ሲጨፈጨፍ, ብዙ ሺህዎች የአማራ ሴቶች በላካቸው ወታደሮች ሲደፈሩ አንድም ቀን ወንጀል የሰሩትን በሃላፊነት አልቀጣቸውም። ሌሴቶቹ ደርሶላቸው አያውቅም። ይህ የሆነበት ምክንያት የአገዛዙ እጅ ስላለበት ነው። የዐብይ ሰራዊት በድሮን የሚጨፈጭፈው ማንን ነው? ለምን ነው? ሴቶችን ሲደፍር ማንን ነው? ለምን ነው? ብለን የማጋለጥ ግዴታ አለብን።
በኢትዮጵያ ዘላቂነት ፍትሃዊ ልማት ለሚያምኑት ሁሉ የምለግሰው ምክረ ሃሳብ ዘረኛነት፤ ጠባብ ብሄርተኛነት፤ የብሄር ተተኪነት የኔ ጥቅም ብቻነት ይከበርነት ለህብረ ብሄራዊቷ ኢትዮጵያ በምንም አያዋጣም የሚል ነው። ከሁሉም በላይ ሊዘገንነን የሚገባው ድርጊት በሲቶች ላይ የሚሄድወው ዘግናኝ ወንጀል ነው።
ዐብይ አህመድ ሴቶች ልጆች እንዳሉት ሰምቻለሁ። ይህንን አረመኔ ሰው የምጠይቀው የራስህ ሴት ልጆች ወይንም ባለቤትህ ቢደፈሩ ምን ትላለህ? ነው;።
በመጨረሻ፤ የአማራው፤ የኦሮሞውና ሌላው ሕዝብ ተዋልዷል፤ ተጋምዷል። ህብረ ብሄራዊነት ከዲሞክራሳዊ አገዛዝ ጋር ሲጣመርና ለአገርና ለሕዝብ ተቆርቋሪና ታዛዥ የመንግሥት አመራር ሲኖረው ሕዝብ ተአምር ሲሰራ የሚችልበት እድል ይፈጠራል። የአድዋ መንፈስ የሚያስተምረኝ ይህንኑ ነው። ዐብይ አህመድ በዚህ አያምንም። ሥልጣን አስክሮታል። የበላይነት አስክሮታል። ከያዘው አጥፊ አላማ ወደኋላ አይመለስም። እመኑኝ!!
በኔ ግምገማ፤ ጸረ-አማራነት፤ ጸረ-ኢትዮጵያና ጸረ-ኢትዮአዊነት የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ናቸው። ይህ ተግዳሮት መንግሥት እና ፓርቲ መር ሆኗል። ይህ ሁኔታ ከአድዋ መንፈስ ጋር አብሮ አይሄድም። እትዮጵያን አይመጥንም።
ኢትዮጵያን ለመታደግ ከተፈለገ ባለድርሻዎች ሁሉ ጸረ-አማራነትን ሙሉ በሙሉ የማውገዝ ግዴታችንን መወጣት አለብን።
December 4, 2025
Part I: Ethiopians Deserve Good Government, Competent and Inclusive Leadership | Dr. Aklog Birara