አንዱ ዓለም ተፈራ
ሐሙስ፣ ጥቅምት ፳ ፫ ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም. (10/23/2025)

የፋኒት በዓለም ዋሴን በአረመኔዎች እጅ የተጎሳቆለ ገላ ሁላችን ተመልክተነዋል። እንደ ሰው፤ ውስጤ ተገለባብጦ ሰውነቴ የሚሆነው ቅጥ አምባሩ ጠፍቶታል። ያንን ማየቱ እንደ አንድ ሰው፣ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ፣ እንደ አንድ ዐማራ፤ ብዙ ነገሮችን ባንዴ አንግሦብኛል። ማዘን፣ መበሳጨት፣ ጨለምተኝነት፣ . . . ምን የቀረ ስሜት አለ! ሁሉም ተጭነውኛል። ምን እየሆነ ነው! ብዬ ለመጠየቅም፤ ማንን? ብዬ ፈዝዣለሁ። አንዳንዶች ለዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ለማሳየት፣ ለመንግሥታት ለማመልከት፣ ባደባባይ ወጥቶ ለመጮህ ይሯሯጣሉ። መቸም አንድ መንገድ ብቻ ነው መፍትሔ ብሎ መነታረክ፤ ተገቢ አይደለም። ሁሉም በሚችለው! እኔ ሌሎች የሚለው ሳይሆን፤” እኔ!” በሚለው ላይ ነው የማተኮረው።
ይህ የዐማራ ህልውና ጉዳይ ነው። በባለም ዋሴ ላይ የደረሰው ልዩ አይደለም። ትላንት ቤንሻንጉል፣ ትናንት ጉራ ፈርዳ፣ ትናንት ሐረር፣ ትናንት ወለጋ፣ ከትናንት ወዲያ ወልቃይትና ጠለምት፣ ራያና መተከል ተፈጽሟል። ትናንት ጎንደር ከተማ፣ ወልድያ ከተማ፣ ደብረ ብርሃን ከተማ፣ ባህርዳር ከተማ ተፈጽሟል። ይሄን ተመልክቶ፤ ለምን! በማለት የአክራሪው ኦሮሞ ጡት ቆራጭ አብይ መሬው ገዢ ቡድን፤ በዐማራ ላይ ያላደረሰው ግፍ አለ ብሎ መጠየቅ ያዳግታል። ሁሉንም ተግብሯል። በርግጥ፤ በተለምዶ የተባበሩት መንግሥታትን ሕግና ደንብ፣ የአፍሪካ ህብረትን ሕግና ደንብ፤ የራሱን የአክራሪ ኦሮሞ ብልፅግና ፓርቲ ሕግና ደንብ ጠቅሶ ጉድለቱን ማሳየት፤ ቀላል ነው። ቁም ነገሩ ግን፤ ይሄ ገዢ ቡድን ሕግና ደንብ ያውቃል ወይ! ነው። ፋኖ ነው ወይንስ ጡት ቆራጩ አብይ የሚመራው የአክራሪው ኦሮሞ ገዢ ቡድን በሕግ የሚገዛው?
ባለፉት ሁለትና ሶስት ዓመታት፤ የአክራሪ ጡት ቆራጩ አብይ ገዢ ቡድን በዐማራ ወገናችን ላይ የድሮን ቦምብ ውርጅብኝ፣ በገፍ ማስርና ማሰቃየት፣ ከቤታቸው ማፈናቀልና መናገር የቻሉትን ማሰቃየትና ማሳደድ፤ የአስተዳደር መመሪያው ማድረጉን ያልተረዳ ካለ፤ የዛሬዋን ኢትዮጵያ አያውቃትም። የፓርላማ አባላት፤ ለምን አብይ የሚለውን አፋችሁን ዘግታትሁ አትቀበኡም ብሎ ለእስራ ዳርጎ እያሰቃዬ ነው። ዐማራም የህልውናና የማንነት ጉዳይ አስገድዶት፤ ትጥቅ እንዲያነሳ ሆኗል። በአሁኒቱ ኢትዮጵያ፤ ስነ ምግባር፣ ሰብዓዊ ርኅራሄ፣ አብሮ መኖርና መተሳሰብ፣ እንደ አገር ማሰብና ነገን በመተማመን የኔ ነው ማለት ርቀዋል። ይቅር በጦርነት ጊዜ ቆስላ የተገኘችውን ፋኒት በዓለም ዋሴን ቀረቶ፤ ዐማራ በመሆኗ ሠርታ የምትበላውን እርጉዝ ሴት በወለጋ ሆዷን ሲቀድና የወደፊት ዐማራ ብሎ ፅንስ ሲገድል፤ ከአራዊት በታች ያለ መሆኑን አስገንዝቦናል። የሰው ልጅ ክብርና ስሜት እንዳልተፈጠረበት ካሳየን ሰንበት ብሏል። እናም ሕግን ጠቅሼ፤ ጡት ቆራጩን አብይን ለመወንጀል ጣቴን አላነሳም። ሁሉም በወጉ!
ይህ የአንድ ወታደር፣ የአንድ የመቶ አዛዥ፣ የአንድ ብርጌድ ስህተት፣ ወይንም የክፍለ ጦርና የአንድ ጀኔራል መጥፎ ተግባር አይደለም። ይህ የአሠራራቸው መገለጫ ነው። ይህ ለሴቶች ያላቸውን አመለካከት፣ ለወጣቶች ያላቸውን ዕይታ፣ ለዐማራ ያላቸውን ጭካኔ ያሳዩበት ተግባር ነው። የውስጣቸውን የነገሩን እንጂ፤ በስህተት የተፈጸመ ድርጊት አይደለም። ለምርኮኛ ያላቸውን የአያያዝ መመሪያ ነው የተገበሩትና ያሳዩን። ለዓለም አቀፍ ሕግና ደንብ ያላቸውን ተገዢነት ነው ያሳዩን። ይህ ተግባር፤ ሰብዕናቸው ምን እንደሆነ ይናገራል። ለዚህ መልሱ፤ እነሱ ያደረጉትን ማድረግ አይደለም። መልሱ፤ “ይሄ በኔ አገር መደረግ የለበትም”! ብሎ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከያለበት ገንፍሎ በመነሳት፤ “ከምድራችን መታጠብ አለበት!” ብሎ የአክራሪውን ኦሮሞ ገዢ ቡድን አጥለቅልቆ ማስወገድ ነው። አገር ፈላጊ ከፋኖ ጋር መቆም አለበት። ለፋኒት በዓለም ዋሴ ይሄን ከትቤያለሁ።
እህቴ ፅኝልኝ፣ ዘለዓለም አብሪልኝ!
ዐማራ ሆነሽ ነው
ሴት በመሆንሽ
ይሄ ሁሉ ስቃይ
የደረሰብሽ፤
ፀሐይዋ ስትወጣ
ፀሐይዋ ስትገባ
ቀን ውሎ ሲጨልም
በነጋ በጠባ፣
በአያቶችሽ ቀዬ
ባማራ ምድር ላይ
ሰው ሆነሽ ተፈጥረሽ
የቀን ብርሃን ሲታይ፤
ግፍ ስቃይ አብዝተው
መታሰር መገረፍ
መሰደድሽ አንሶ፣
ሊያረክሱሽ ሲቆሙ
ሰብዕናሺን ደፍረው
አረመኔ ነግሦ፤
በሩቅ ሆኜ በሰው አገር
ቀሪ ህይወት ለመኖር፤
ያንቺን ማንነት ማጣት
ያንቺ ሰብዕና መገፈፍ
መታሰርና መገረፍ፤
እንቅልፍ ነስቶኝ ስገላበጥ
ባንቺ ጭንቀት
የውስጥ ማንነቴ ሲሟጠጥ፤
ያንቺ ማንነት የኔ ሆኖ
ዐማራነቴ ጀግኖ፤
ጥቃትሺን ሁሉ ቋጥሬ
ከፅናትሽ ተምሬ፤
ተፈጥሮ ያደለሺን የሰውነት ፀጋ
የማንነትሽ የውስጥሽ በጋ፤
የትናንቶች የሠጡሽ ዕሴት
የተረከብሺው ዐማራነት፤
በዛሬው ማንነትሽ አሳምረሽ
ለነገዎቹ ልታስረክቢ ተሸክመሽ፤
በህይወትሽ ህይወት ዘርተሽ
ለሌሎቹ መብራት ሆነሽ፤
ዓለምን አሳምረሽ አልፈሻል
ያንሺ ታሪክ አብሪ ሆኖ
በመላ ዐማራ ልብ ተጽፏል።
የታሪክ ኃላፊነትሽን ተወጥተሻል
አሸብረቀሽ አምረሻል፤
መሬቱ ይቅለልሽ እህታለም
ለዛሬና ለነገዎች
ጧፍ ሆነሽ አብርተሻል።
አንዱ ዓለም ተፈራ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት ፲ ፩ ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም. (10/21/202