አንዱ ዓለም ተፈራ
እሁድ፣ መስከረም ፲ ፰ ቀን ፳ ፻ ፲ ፰ ዓ. ም. (09/28/2025)
ኢትዮጵያ እንደ አገር፣ ኢትዮጵያዊነት እንደ የአገር ዜግነት፣ እና በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግሥት አለ ወይ? ተብዬ ተጠይቄያለሁ። በርግጥ መልስ መሥጠቱ ሳይሆን፤ ይሄን ራሱን መጠየቄ አስገርሞኝ፤ ቃላት አጥረውኝ ፈዝዤ ጊዜ ወስጃለሁ። እውነት ኢትዮጵያ አለች ወይ? ኢትዮጵያዊነትስ አለ? ካለስ ምንድን ነው ትርጉሙ? መቼም ትርጉም የሌለው ኢትዮጵያዊነት አስቸጋሪ ነው። እውነት ደግሞ አሁን በኢትዮጵያ በታወጀው፤ ነገር ግን ትርጉም አልባና የአንድ ጎሳ የበላይነት በነገሠበት ሀቅ፤ ኢትዮጵያ የለችም! ኢትዮጵያዊነትም የለም! ከዚህ ልጀምር። ታዲያ መነሻው ይሄ የሆነ እሳቤ፤ መድረሻው ምን ሊሆን ይችላል? ለመሆኑ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ሥልጣን ከጨበጠበት ጊዜ ጀመሮ ምን ተከተለ?
የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር፤ በኢትዮጵያዊነት ሳይሆን በትግሬነቱ ሥልጣን ይዞ ከገዛበት ዕለት አንስቶ፣ እስካሁን፤ ገዢዎቹ፤ መጀመሪያ ትግሬዎች፣ በትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ስም፤ አሁን ደግሞ ኦሮሞዎች በብልፅግና፣ የአክራሪ ኦሮሞዎች ገዢ ቡድን አማካኝነት እየገዙ ነው። ስለዚህ፤ ያለ ምንም ማቅማማት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ በ“ብሔር” ማንነቱ ነው እየተገዛ ያለው። ወደድንም ጠላንም፤ ዐማራም በዐማራነታችን እስከተገዛን ድረስ፤ እንደ ዐማራ ህልውናችንንን መጠበቅ አለብን። ለአንድ ዐማራ፤ በአሁኑ የአገራችን የፖለቲካ መድረክ፤ ዐማራነታችን ምንድን ነው? የዐማራነታችንስ መሠረቶች ምንድን ናቸው? ይሄን ነው በዚህ ጽሑፍ የምዳስሰው።
ለኔ፤ እንደ አንድ ዐማራ፤ የዐማራ ብሔርተኝነት፣ አሁን በአገራችን ያለውን የፖለቲካ መድረክ የምመለከትበት መነፅር ነው። የዐማራ ብሔርተኝነት፤ በታሪክና በሌሎች አገሮች እንዳየነው አይደለም። የዐማራ ብሔርተኝነት ራሱን ያነፀና ልዩ ፈር የቀደደ ክስተት ነው። የዐማራ ብሔርተኝነት፤ ዐማራ የራሱን ማንነት አስምሮ፣ ማንነቱን ጠብቆ፣ መኖሪያውን አክብሮና አስከብሮ፤ ዙርያውን የከበበውን አጥፊ ቡድን አቸንፎ፣ የነገ ህልውናውን የሚያረጋግጥበት እሳቤ ነው። መጀመሪያ፤ እዚህ ላይ የዐማራ ብሔርተኝነት ከሌሎች የተለየባቸውን ላስፍር።
የዐማራ ብሔርተኝነት፤ ኢትዮጵያ በድላኛለችና ከኢትዮጵያ ተገንጥዬ የዐማራ ክልል እፈጥራለሁ! ብሎ ዐማራ የተነሳበት አመፅ አይደለም። ይህ ፀረ-የዐማራ ብሔርተኝነት ነው። የዐማራ ብሔርተኝነት፤ ዐማራ፣ ዓለምን የሚመለከትበትን የራሱን የፍልስፍና ርዕዩተ ዓለም አንግቦ፤ ያንን በሌሎች ላይ ለመጫን የተነሳበት ጉዳይ አይደለም። የዐማራ ብሔርተኝነት፤ ዐማራ፣ ራሱን በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ የበላይ አድርጎ ለመጫን የተነሳበት ግንዛቤ አይደለም። ይህ መታወቅ አለበት። የዐማራን ብሔርተኝነትን የሚገልጡ የሚከተሉት ምሰሶዎች ናቸው።
አንደኛ፤ የዐማራ ዐማራ ሆኖ መገኘት፣ የተፈጥሮ ሥጦታችን ነው። ይህ የራሳችን ማንነት ነው! እንጠብቀዋለን።
ዐማራ ዐማራ የሆንነው፤ በማንም ፍላጎትና ትዕዛዝ አይደለም። ዐማራ ሆኖ መገኘት፤ የተፈጥሮ ሥጦታችን ነው። ለእያንዳንዳችን ዐማራ፣ ይሄን ማንነታችንን የትም ቦታና በማንኛውም ጊዜ ይዘነው የምንኖር፤ የመላ ህይወታችን ዕሴት ነው። በዚህ ከማንም ጋር አንደራደርም። ያንን ለማይቀበሉልንና ለማያከብሩልን፣ ቦታ አንሠጥም።
ሁለተኛ፡ ለዐማራ፤ ኢትዮጵያ፣ ተፈጥሮ የሠጠችን አገራችን ናት! እናከብራታለን! እንጠብቃታለን።
ዐማራ የምንኖረው በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ነው። ኢትዮጵያ፤ ቀደምት ዐማራ የገነቧት አገራችን ናት። በዚህ ሂደት ከሌሎች ጋር ሆነን፤ ከውጪ ወራሪዎች አገራችን በመከላከል፤ ደማችን አፍስሠን፣ አጥንታችንን ከስክሰን፣ አጥር ሆነን ጠብቀናታል። ስለዚህ፤ ከዚች አገራችን ማንም ሊነቅለን አይችልም። የአገራችንን ባለቤትነት፤ ከሌሎች ጋር በትክክል እንጠብቃለን።
ሶስተኛ፤ ዐማራን ሊያጠፋ የተነሳው የአክራሪው ኦሮሞ ገዢ ቡድን፤ ያለ ምንም ቅደመ ሁኔታ መደምሰስ አለበት።
በማንነታችን የተነሳብንን እና ከምድር ሊያጠፋን የተነሳው ወራሪ የአክራሪ ኦሮሞ ገዢ ቡድን፤ የዐማራ ዋና ጠላት ነው። በምንም መንገድ ሆነ በምንም፤ ይህ ቡድን፤ ለህልውናችን ከፍተኛ ደንቃራ በመሆኑ፤ ከዚህ ቡድን ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ሊኖረን አይችልም። የሚኖረን፣ ይሄን ቡድን አጥፍተን፤ ከሊሌች ኢትዮጵያዊያን ጋር አገራችንን አቅንተን በሕዝቡ ተቀባይነት ያለው መንግሥት መመሥረት ነው።