ይህ ጽሑፍ እጅግ በልብ የሚነካ የአስታውሳት እና የህዝባዊ ትዝታ ማስታወሻ ነው። መስከረም 7 በቡራዩና አካባቢው በተከሰተው አሰቃቂ ግድያ ሕዝቡ እንዴት በቁጣ ተነስቶ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳዘጋጀ ይገልፃል – ዘ ሐበሻ
በወቅቱ በቡራዩ እና አካባቢው በተከሰት አሰቃቂ ግድያ እና መፈናቅል ተከትሎ ሕዝባዊ ቁጣ ቀስቅሶ ነበር።በቀኑ ከሽሮሜዳ የጀመረው ሕዝባዊ ቁጣ ገና ከጠዋቱ 12 ሰዐት ነበር የጀመረው። በዋዜማው ድርጊቱን ለማውገዝ ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ሰላማዊ ሰልፍ በ7/01/2011/ ከቀኑ በ8:00 ሰዐት በምንሊክ አደባባይ ተጠርቶ የነበረ ቢሆንም ይህን መታገስ ያልቻለው የሽሮሜዳ አካባቢ ወጣት ገና ወፍ ሲንጫጫ ነበር ሰላማዊ ሰልፍን አሃዱ ያለው።
ሰልፉ ወጥ እና የሚመራው አካል ባለመኖሩ ሰልፉ በተለያዩ ፍላጎቶች ተሞልቶ ነበር። ከሽሮሜዳ የተጀመረው ሰልፍ ቁልቁል ወደ ስድስት ኪሎ አመራ ይህንን የሰሙ የፈረንሳይ ፣የቤላ እና የምንሊክ ሰልፈኞች ሰልፍን ተቀላቅለው ወደ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት አመራ ቤተመንግስት እንደደረስም ሰልፈኛው:-
“አብይ ደመረን ጃዋር ቀነሰን”
“ስማ በለው አብይን ስማ በለው”
” በአዲስ አበባ ግዚያዊ የባላደራ አስተዳደር ይቋቋም”
“ቄሮ ሌባ ቄሮ ሌባ ቄሮ ገዳይ ቄሮ ፣ ቄሮ ዘራፌ”
“ጅብ ሲወጣ አህያው መጣ”
“አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ” እና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ከቤተ-መንግስት በአብዮት አደባባይ አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ድምፁን እያሰማ ነጎደ። እዛም እንደደረሰ በርካታ ሰልፈኞች ድምፃቸውን እያሰሙ ስለነበረ ከእነሱ ጋር ተቀላቅሎ ድምፁን ማሰማት ጀመረ።
ሰልፋ መሪ አልባ እና የተቀናጀ ስላልነበረ ቀጣይ ምን መድረግ እንደነበረበት አልታወቀም። ለኢቲቪ ድምፁን ካሰማ በኃላ ሰልፈኛው ወደ ፋና ቴሌቭዥን አመራ ግን ብዙ ሳይጓዝ በፌደራል ፖሊስ እንዲመለስ ተደረገ። በዚህ የተከለከለው ሰልፈኛ 8:00 ሰዐት ላይ ቀጠሮ ተይዞበት ወደ ነበረው ምንሊክ አደባባይ (ጊዮርጊስ) አመራ።
ጥቁር አንበሳን ሽቅብ ወጥቶ ቴድሮስ አደባባይ ሊደርስ ሲል ሌላ ግዙፍ ሰልፍ ከመርካቶ ፣ አቶብስ ተራ ፣ ተክላይማኖት ሰልፈኞች ተቃውሞ እያሰሙ ሽቅብ የሚመጣውን ሰልፍ ተጭነው ወደመጣበት እንዲመለስ በማድረግ ጉዙውን ወደ መሰቀል አደባባይ አደረገ። አምባሳደር አካባቢ የሚገኘው መከላከያ ሚኒስተር ጋር ሲደርስ ግን ሰልፋ ከበድ የሚል እና ከፌደራል ፖሊስ አቅም በላይ መሆኑን የተረዳው መከላከያ ሰልፉን ለማገድ ቆረጠ።
በርካታ የመከላከያ ተሽከርካሬዎች ሰልፈኛውን ከበቡ። ሰልፈኛው እልህ ስለነበረበት ፌት ለፌት መከላከያን ጥሶ ወደ መስቀል አደባባይ ለማምራት ጥረት ሲያደርግ መከላከያ በመሰራያ መበትን ጀመረ ወዲያውም አምስት ወጣቶች በአልሞ ተኳሾች ተመተው ህይወታቸው እንዲያልፍ ሆነ። በርካቶች የጥይት ቁስለኛ ሆኑ።
በዚህ መሃል ግን በአካባቢው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አዛዦች አባላቶቻቸውን “እናንተ እንዳትተኩሱ እነሱ እንደጀመሩ እነሱ ይጨርሱ” ሲሉ ትህዛዝ ሰጡ። ከዛም ሰልፈኛው በያቅጣጫው ተበታትኖ ዳግም አብዮት አደባባይ ተገናኘ። ሰልፉን እስከ ቀኑ አስራ አንድ ሰዐት ጨዋነት በተሞላው መልኩ አሰምቶ ወደ መጣበት ተመለሰ። በአምስት ወጣቶች ሞት ክፋኛ ያዘነው ወጣት ዳግም ሌላ እመም ተጨመረበት።
ዘይኑ ጀመል የወቅቱ የፌደራል ፖሊስ ኮመሽነር ወጣቶቹ” መሳሪያ ሊነጥቁ” ሲሉ ነው የተገደሉት ብሎ ተሳለቀ። ይህ በቦታው ለነበረነው ሰዎች ግን ልብ ይሰብር ነበር። ከጥይት ከተረፍንም ሰዎች ውስጥ ስለነበርን ወጣቶቹ መሳሪያ ሊነጥቁ የሚችሉበት ሁኔታ እንደሌለ እኛ ምስክር ነን።
ከዘይኑ መግለጫ በኃላ በአዳስ አበባ ኔትወርክ ተቋረጠ። ማምሻውን በሽሮሜዳ ፣ በፈረንሳይ፣ ቤላ፣ በምንሊክ ፣ በቀጨኔ፣ በአውቶብስ ተራ፣ በአዲሱ ገበያ፣ በሳሬስ ፣ በኮልፌ፣ በተክላይማኖት ፣ በቄራ፣ በጨርቆስ ከሰልፍ የተመለሱ ወጣቶች መታፈሳቸው ተነገረ። የታፈሱ የአዳስ አበባ ወጣቶች የት እንደሄዱ ሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፋ። ከቀናት በኃላ ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ እስር ቤቶች እንዳሉ ተረጋገጠ። ከወራት የእስር ግዜ በኃላ ስልጠና ወሰደው ተፈቱ ተባለ።
ሚያዚያ 7/01/2011 ዓ.ም ከጥይት የተረፍንበት ቀን ነው። በሰዐቱ ህይወታቸውን ያጡ አምስት ወጣቶችንም የምንዘክርበት ቀንም ነው።
እግዝሓብሔር ነፍሳችሁን በገነት ያኑር!!