የሕዳሴን ግድብ በጸነሰው ሰው አላማ መሰረት ለነማን እና ለምን ጥቅም የሚለው ጉዳይ ኢትዮጵያኖች እና የአለም በጎ አድራጊ ሰዎች ጠይቀው መልስ ያላገኙበት ጥያቄ ነው። ግድቡ ተሰርቶ ቢያልቅም ችግሩ አንዳለ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብም የማያውቀውን ዕዳ ተሸክሞ ይገኛል። ግድቡ በሚስጥር ተይዞ ያለ ሕዝብ ዕውቅና እና ፍቃድ ተገንብቷል። ይህ ድርጊት የተፈጸመው በኢትዮጵያ ጠላቶች ትብብር ነው። ለአንድ ሀገር፣ ለአንድ ሕዝብ በእድገቱና ብልጽግናው ጥረት ላይ ከዚህ የበለጠ በደል ሊፈጸም አይችልም። ሕዝብ የመሪውን ድርጊት አምኖ እና ተቀብሎ ይሁን ብሎ አይደለም። በራሱ የተደረገው ጭቆና የማያለዋውስ በመሆኑ ነው። የተማረ ሰው ጠፍቶ አይደለም። ወይም ሽማግሌውና አገር ጠባቂው ከምድሩ ጠፍቶ አይደለም። አገሬቱን በበላይነት የሚያስተዳድረው የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ትሕነግ)በየአንዳንዱ ዜጋ ላይ ከባድ ቁጥጥር በማድረግ አፍኖ ስለያዘው ነው። አንድ አጥፊ መሪ ሕዝብንና አገርን እስኪያወድም ድረስ መጠበቅ የለበትም። በቃ የሚባልበት ግዜ መኖር አለበት። ይህ ጽሑፍ የቀረበው በዚሁ መንፈስ ሲሆን፣ የግድቡ አላማ ለነማን እና ለምን ጥቅም እንደተገነባ ግልጽ ለማድረግ ነው።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ – – ዘውገ ፋንታ