ሞዐ ተዋሕዶየሞዐ ተዋሕዶም ይሁን የማኅበረ ቅዱሳን አባል አይደለሁም። በአካል የማውቀውም የሞዐ ተዋሕዶ አባል ከአንድ አይበልጥም። ሞዐ ተዋሕዶ ግን ለምን ዓላማ የቆመ ነው?
“የሚታገልላቸው ፯ቱ የኦርቶዶክሳውያን መሠረታዊ ጥያቄዎች*
1ኛ. በሕገ መንግሥት፣ በፖለቲካ ማንፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳውያንን ለጥቃት የሚያጋልጡ መልእክቶች በአስቸኳይ በሕግ ይታገዱ።
2ኛ. ኦርቶዶክሳውያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ሓላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት ዕድሎች የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል ድረስ የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ እንዲቆምና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ።
3ኛ. ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በቋንቋና በተለያዬ ዘውጎች ለመከፋፈል የሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት፣ በጥናትና ምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት እንዲታገዱ።
4ኛ. በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ የአካል፣ የሥነ -ልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማሕበራዊ፣ የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የማግለል እና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ።
5ኛ. እስከ አሁን የተፈጸመው ጥቃት በዝርዝር ተገላጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የተጎዱት እንዲካሱ።
6ኛ.በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳውያን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ።
7ኛ. “…አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የማጥፋት ፖለቲካዊ ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ።”
እነዚህ የኔም ጥያቄዎች ናቸው።
እነዚህን ሰባት ሃሳቦች የሚደግፍን እደግፋለሁ፣ የሚቃወምን እቃወማዋለሁ።
*ZB 6/8/2025