በዛሬው ዕለት ሀምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም የኦህዴድ/ብልፅግና አገዛዝ የወንድማችንን እና የትግል ጓዳችንን የአርበኛ አበበ ፈንታውን አባት አቶ ፈንታው ደርበውን ፀሎት በሚያደርጉበት በቆቦ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ረሽኗቸዋል!
ለወትሮው አማሮች ክርስትና እና እስልምና ሃይማኖቶች የወረራ መሳሪያ ተደርገው በሚታዩበት አካባቢ በሚያመልኩበት ቤተ እምነት በብልፅግና አገዛዝ በግለሰብና በጅምላ መገደላቸው አዲስ ነገር አይደለም። የአባታችንን የአቶ ፈንታውን ግድያ አዲስ የሚያደርገው ክርስትናም ሆነ እስልምና ከፈጣሪ የሚያገናኙ መንገዶች ብቻ ተደርገው በሚወሰዱበት አካባቢ የተፈፀመ መሆኑ ነው::
ግድያው የተፈፀመው ምዕመናን በተሰበሰቡበት፣ ካህናት አምላኪንና ተመላኪን በሚያገናኙበትና በሚባርኩበት አውደ ምህረት ነው:: ይህ ግድያ የሚያሳየው ህዝባችን አምልኮት በሚፈፅበት ቤተ እምነቶች፣ በሚኖርባቸው ከተሞችና መንደሮች፣ በሥራ ቦታዎች እረፍት እንዳያገኝ እና የተረጋጋ ኑሮ እንዳይኖረው የማድረግ ሂደት አካል ነው::
ሌላው የሰማዕቱ አባታችን አቶ ፈንታው ደርበው ግድያ የሚያሳየን የብልፅግና አገዛዝን ፋሽስታዊ ባህሪይ ነው:: ከዚህ በፊት በሀገራችን የተነሱ አንባገነኖች የነፃነት ታጋዮችን ሰቅለዋል፣ በቀይ ሽብር ፈጅተዋል ልዩ ልዩ አሰቃቂ ድርጊቶችን ፈፅመዋል:: የእነ ግርማሜን አባት የሰቀለ ባለዘውድ፣ የእነ መለስንና ኢሳያስን አባት የረሸነ ባለቀይ ሽብር እንዲሁም የእነ ሳሙኤልን አባትና እናት የገደለ ልማታዊ ዴሞክራት ግን አላየንም፣ በእናትና አባት ወይም በልጅና ሚስት ወይም በእህትና በወንድም ላይ የፈፀሙት እስርም ሆነ ግድያም አናስታውስም::
የብልፅግና አገዛዝ ግን ፋሽስቱ የጣልያን ወራሪ በአርበኞቻችን ሲያደርግ እንደነበረው አርበኛ አበበ ፈንታውን ታግሎ መጣል ሲያቅተው የ75 ዓመት እድሜ ባለፀጋ አባቱን ነፃ ርምጃ ወሰደባቸው:: ይህንን ክፉ ስርዓት ልጁ ስለታገለው አባቱን የገደለበት መሰረታዊ ምክንያት የብልፅግና አገዛዝ ዘር ጨፍጫፊ ስለሆነ ነው:: ብልፅግና የልጅን ወንጀል እስከቅደመ አያት ድረስ: የአባትን ወንጀል ደግሞ እስከ የልጅ ልጅ ድረስ መጠየቅ የሚፈልግ አረመኔ አገዛዝ ነው:: ጉዳዩ ከአማራ ሕዝብ ጋር ሲያያዝ ደግሞ ከሰባት ትውልድም አልፎ በማህበረሰብ ደረጃ አማራን መጨፍጨፍ ለስርዓቱ ኩራትና ክብር ጭምር ነው::
የብልፅግና ስርዓተ ‘መንግስት’ ከቀደሙት ስርዓቶች ሁሉ የከፋ ለሚቀጥሉት ዘመናትም ድጋሜ ይታያል ተብሎ የማይታሰብ ፋሽስታዊ ስርዓት ነው:: ስለሆነም ሕዝባችን ይህንን ስርዓት በከበረ ትግሉ መገርሰስ ይኖርበታል!!!
ለሰማዕቱ አባታችን ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘሁ ለወንድሜ አቤም በሁሉም አቅጣጫ እየከፈልክ ላለው መስዋዕትነት ያለኝን ክብር እገልፃለሁ!!!
አርበኛ ሄኖክ አዲሴ
ከትግል ሜዳ
ሀምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም
የታጋይ ፋኖን አባት መግደል፣ የሽንፈት ምልክት ነው