ትናንት ሀምሌ 13/2017 ዓ.ም ለስርአቱ ሚሊሻ፣አድማ ብተናና መደበኛ ፓሊስ አባላት አንድ አስቸኳይ ጥሪ አስተላልፌ ነበር።መልእክቱ አዳሩን በየካምፑ ደርሶ ሚሊሻና ፓሊሶች ከፍተኛ ውይይት ሲያደርጉ ማደራቸውንና እርስ በርስ መነጋገሩ ዛሬም መቀጠሉን ለመረዳት ችያለሁ።ይህም የሚበረታታና የሚያበረታታ ሆኖ ስላገኘሁት በየደረጃው ላሉ የአብይ አህመድ አማራ ሹመኞችም የሚከተለውን መልእክት አስተላልፋለሁ፦
ወገኖቼ!
(በአለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ የተሳትፎ መጠንና ጥልቀት ዘራችሁን ሊያጠፋ ከመጣ ወራሪ ጋር ተሰልፋችሁ እናታችሁንና አባታችሁን፤እህትና ወንድሞቻችሁን፤ህጻናትን፤ዛፍና እንስሳውን የምታቃጥሉ እናንተን የምድር ጉዶችን ነው ወገኖቼ የምለው እንግዲህ!!!!)
የእናንተን ስነልቦና በእግዜርኛ ካልሆነ በሰውኛ ለመረዳት ከባድ ነው።ሰው ምኑን ሲያመውና ወደ ምን ፍጡርነት ሲቀየር እንደ እናንተ እንደሚሆን መረዳት አልቻልሁም።ምድሩን በሙሉ በእሳት አቃጠላችሁት።ምድሩን በሙሉ በረሀብ ሞላችሁት።ከተሞችን በሙሉ አምስት ልጆቿን ታበላቸው ዘንድ ኩርማን እንጀራ ባጣች እናት እናታዊ የሰቆቃ ሲቃ ሞላችኋቸው።ሀገሩን የቅጥፈት፣የማስመሰል፣የዝርፊያና የእልቂት ከንቱ መድረክ አደረጋችሁት።አንዳንዱ ሰፈር በዘረፈጅ ወራሪ ጠላት የተወረረ ተስፋ ያጣ ምድረበዳ ሆነ።ምንድን ነው የሆናችሁት?፦አውሬ እንዳትሉኝ።እናንተን የሚመስል አውሬ አልተፈጠረም አይፈጠርምም።ምክንያቱም ምድር ከተፈጠረች እስካሁን የራሱን ዘር በአዋጅ የሚበላ አውሬ አልተከሰተም።ታዲያ ምንድን ነው የሆናችሁት?
አረጋ ከበደ ምን ሆነህ ነው?ተመስገን እንኳን አማራ አይደለሁም እንደሚልም አውቃለሁ(ምን እንደሆነ አንድ ቀን ፍትህ በከስክስ ጎሮሮው ላይ ስትቆም ይነግረናል)።
አረጋ አንተ ምን ሆነህ ነው?በሆድህ ወድቀህ እንዳልልህ በጤና ችግር ምክንያት ባለቤትህ ቤት ያዘጋጀችልህን ምግብ እንኳን መብላት የማትችል በየቀኑ እንደ ባህታዊ ደረቅ ቂጣ ብቻ እንደምትቆረጥም አውቃለሁ።ምን ነክቶህ ነው አንተንም ዘርህንም ለሚፈጁ ሰዎች እየተላክህ ህዝብህን የምታርድና የምታሳርድ?
አብይ አህመድ አንድ ድረስ ሳህሉ የሚባል አስገራሚ ተላላኪ አለው።ባንዳነትም ውፍረትና ቅጥነት አለው መሠለኝ ድረስ የሚደንቀኝ አይነት ባለደረጃ ባንዳ ነው።አባቱ አባ ሳህሉ ጎጃም ቋሪት ለመሬት የገዘፉ ሰማይ ጠቀስ ዝግባ ናቸው።ከቋሪት ተራሮች የሰፉ ጀግና።ልጅየው ድረስ የቋሪት እናቶችን እያስጨፈጨፈ ለአብይ በቀይ እስክርቢቶ ሪፓርት ሲጽፍ ይውላል።ዝግባ እንዴት የብሳና ትል ይወልዳል?።እንቆቅልሽ ነው፤የማይገባኝ ወለፈንዲ።ምን ሆነህ ነው ድረስ?ሌሎቻችሁ ምን ሆናችሁ ነው? በጽፈት ቤቶቻችሁ ውስጥ ነገ የሚባል ቃልና የጊዜ ምእራፍ አይታወቅም!?ነገ ምን ልትሆኑ ነው? ነው ወይንስ አብይ እንደሚመኘው ከስልሳ ሚሊዮን በላይ አማራ በሙሉ ገላችሁ ያለጠያቂ መኖር የምትችሉ መስሏችሁ ነው?
ውላችሁ ስትገቡ ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን በምን አይን ነው የምታዩአቸው?አትቸገሩም?ጎጃም በሬና ገበሬና ስታስገድሉ፤ወሎ ንጹሀን ስታስረሽኑ፤ሸዋ መንደር ሙሉ ሰው ቤት ዘግታችሁ ስታቃጥሉ፤ጎንደር ጨቅላ ስትጨፈጭፉ ውላችሁ ቤት ገብታችሁ፤የለበሳችሁትን ሱፍ አውልቃችሁ ተኝታችሁ ታድራላችሁ?አልጋው በንጹሀን የደም ውቅያኖስ ላይ የተንሳፈፈ ታንኳ አይሆንባችሁም?ምን ፍጥረት ናችሁ?እንደማህበረሰብ በምን ደረጃ ነቅዘን ነው እናንተን ያፈራን?
ዛሬ የጥሪ ደብዳቤ የምሰድላችሁ ይህ ትግል ከእናንተ የመዳንም እናንተን የማዳንም ስለሆነ ድንገት ተሸርፋ የቀረች ሰው መሆን-ሰውነት ጀርባችሁ ላይ ተለጥፋ ካለች ሰው እንድትሆኑ እንድትድኑ እድሉን ለመፍጠር ነው።ራሳችሁን አድኑ።ተመለሱ።
የፋኖን አቅም በሚገባ ታውቁታላችሁ።እንኳን እኛ እናንተ በኛ እየተከበራችሁ እኮ ነው።”እድሜ ለፋኖ አለቆቻችን ሰላምታቸው ሁሉ ተቀየረ፤ከመቀመጫቸው እየተነሱ ኖሩ እያሉን ነው “ስትሉ እኮ እንሰማለን።አብይም ይሰማል።
እመኑኝ አብይ አህመድ ይጠላችኋል።ይጸየፋችኋል።
አብይ አህመድ ከእናንተ ይልቅ ለበሻሻ ከርከሮ ክብር አለው።ቢመራችሁም በየቀኑ የምትጋቱት መራራ እውነት ነው፤ታውቁታላችሁ።
ለራሱ ህዝብ ያልሆነን ባተሌ ባንዳ ለጊዜው ቢጭኑት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ አድርጎ እንደ ከብት ቢነዳው እንጅ ማን ያከብረዋል።ጌታውን የከዳን ውሻ ማን ይወዳል?
ነገ የልጆቻችሁን እጅ ይዛችሁ በየካፍቴሪያው በነጻነት ማኪያቶ መጠጣት ትፈልጋላችሁ? የታሪክ ድኩማን አለመሆንስ ህልማችሁ ነው? እንግዲያውስ ከአሁኑ ፓለቲካዊ ንስሀ ግቡና ከአብዮቱ ጋር ተሰለፉ።።የትግሉ አካል ሁኑ።ትግሉን በአካል ተቀላቀሉ።በያላችሁበት አግዙ።እንደምታውቁት እናንተም እኛም መቼ የሚለውን እርግጠኛ ላንሆን ብንችል እንኳን አብይ አህመድ አገዛዝን የማሸነፋችን ጉዳይ ሰማይ ላይ የተጻፈ እውነት ሆኗል።እና እኛን እንዴት ማግኜት እንደምትችሉ ስለምታውት በየሰፈራችሁ ባለው የፋኖ መዋቅር ዛሬ ነገ ሳትሉ የህልውና ትግሉን ተቀላቀሉ።
አንድ አማራ!!
እስከ ምጻት አማራ!
ክፋት ለማንም በጎነት ለሁሉም!
አዲስ ትውልድ፤አዲስ አስተሳሰብ፤አዲስ ተስፋ!!
አርበኛ ዘመነ ካሴ
ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም