520282467 122179922108564511 5340491810937742721 nይህ ሰራዊት ሀገር መጠበቅ ሲገባው ላለፉት ሰባት ዓመታት ባደረጋቸው ውጊያወች እና በፈፀማቸው ጭፍጨፋወች የኢትዮጵያን ህዝብ ማህበራዊ ትስስር እየበጣጠሰ ያለ፣ በክፍለ ዘመኑ ከባዱን ዝርፊያ፣ አስገድዶ መድፈር እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመ እና እየፈፀመ ያለ ነው።
አብይ አህመድ ስልጣን ላይ ከወጣበት ግዜ ጀምሮ ይህ ሰራዊት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ሲባል አንዲትም ጥይት አልተኮሰም። ይልቁንም ኢትዮጵያዊያን ጋር ያለ ማቋረጥ ተዋግቷል እየተዋጋም ይገኛል።
ይህ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከመበተኑ በፊት ለአብይ አህመድ የቅዠት እቅዶች ተገዥ መሆኑን ትቶ ከህዝብ ጎን ካልቆመ በስተቀር መፍረስ ያለበት ሰራዊት ነው።
ይህ ሰራዊት ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለ ሰራዊት ነው።