‘የአብይ አሀመድ አገዛዝ የምናስወግደው እንጂ የምንደራደረው አይደለም” አርበኛ ማርሸት ጸሀዩ July 6, 2025 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email የአብይ አሀመድ አገዛዝ የምናስወግደው እንጂ የምንደራደረው አይደለም” አርበኛ ማርሸት ጸሀዩ Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email 4 Comments Leave a Replyየሰላም ድርድርን አሻፋረኝ የሚል ማንም ታጣቂ ሃይል የአለም ፓለቲካ ያልገባው የዛገ አስተሳሰብ ያለው ብቻ ነው። ለዘመናት ከቱርክ ጋር የተፋለመው የከርድስታን ፒኬኬ ተፋላሚ ከዘመናት በህዋላ ለሰላም እጅ መስጠቱ የሽምቅ ውጊያ ጊዜ ያለፈበት መሆኑን ያሳያል። ዛሬ ወያኔና ሻቢያ ደርግን ድል አደረግን ብለው በየዓመቱ ከበሮ እንደሚደልቁት አይነት ውጊያ አሁን ላይ የለም። በእስራኤልና በኢራን የሆነውን አይናችን አፍጠን አይተናል። ከተነገረን ይልቅ የተደበቀው የዚህ ግጭት ዜና ብዙ ነው። በዚህ ላይ የየመን ሁቲዎች ከቀይ ባህር ማዶ የተወነጨፈው ነገሪያቸው እስራኤልን መምታት መቻሉ የጊዜውን በፍጥነት መቀየር ያሳያል። በጫካና በየመንደሩ በመሽሎክሎክ የሚደረጉ ውጊያዎች ደግሞ ነጻ እናወጣሃለን የሚባልለትን ወገን በሁለት ተፋላሚ ሃይሎችም መካከል አስገብቶ ደሃና ሰርቶ አዳሪን የሚያስጨርስ በመሆኑ ፍሬው መራራ ነው። 70 ዓመት ሙሉ የተደነፋበት የሩሲያው የቁስ አካል ፍልስፍና ያ ሁሉ ሃብትና የሰው ሃብት ፈሶበት ነፋስ እንደመታው ድቄት በአንዴ ነው በኖ የጠፋው። ፓለቲካ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው። አይ አልገባኝም የሚል ካለ Secondhand Time: The Last of the Soviets By Svetlana Alexievich የጻፈችውን ማንበብ ነው። የሚያሳዝነው ትውልዷ ዪክሬን ነው። ያኔ አብረው በፍቅር ይኖሩ ነበር አሁን ደግሞ መቧቀስ ከጀመሩ ሶስት ዓመት አለፈው። በሩሲያና በዪክሬን ጦርነት ሳቢያ ሁሉ እየታጠቀ እንደሆነ ከአውሮፓና ከሰሜን አሜሪካ የሚፈልቁ ወሬዎች ይናገራሉ። ዛሬ ላይ ማሰልጠኛ ምልምል ወታደር ገብቶ ሰልጥኖ እስኪወጣ አይጠብቁም ራሱ ማሰልጠኛውን ነው ድምጥማጡን የሚያጠፉት። የአብይ አህመድን አገዛዝ የምናስወግደው እንጂ የምንደራደረው አይደለም መባሉ አላዋቂነት ነው። ቢቻል ነገርን በሰላም መጨረስ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ግን እሺ ያሰብከው ይሁንና አርበኛ ማርሸት ለመሆኑ ምን ዋስትና አለህ አሁን ካለው የከፋ ሌላ መንግስት ነኝ ባይ በሃበሻ ምድር ላለመምጣቱ? ታሪካችን እንደሚያሳየን ከሆነ ከክፋት ወደ ክፋት አንድ አፍራሽ ሌላ አፍራሽ ሲተካው እንጂ የተሻለ ነገር አላየንም። በጠመንጃ አፈሙዝ የሚመጣ ማንኛውም ለውጥ መሰል ነገር ባለንበት በዚህ ዘመን ለሃገርም ለወገንም አይጠቅምምና የፓለቲካ ጥያቄአችሁን በጥቅል አቅርቡና ከመታኮስ ይልቅ በመደራደር ለመጨረስ ብትጥሩ መልካም ነው እላለሁ።Replyአንተ ሰውዬ ክፍሉን መማሪያ ሳይሆን መደበሪያና ሀሳብ ማጨናገፊያ ነው ያደረግኸው። የምትጽፈውንም የምታውቅ አይመስለኝም እንደ ኮፒ ፔስት አይነት በነጋ በጠባ የምትጽፍልን ይህንኑ ነው። ማርሸት ያንተ ልጅ ይሆናል በትምህርቱም ሁለተኛ ዲግሪውን ይዟል መኖር ቢችል ሽቶውን እየተቀባ ባማረ ፍራሽ ይተኛ ነበር እንጅ በሀሩርና በቁር ከጥይትና ድሮን እየተባረረ መከራውን ባላየ ነበር። ከማርሸት ጋር ብዙ ምሁራንና ፕሮፌሰሮች አሉ እነዚህ በሞታቸው የቆረጡ በተመሳሳይ ሁኔታ መኖር ስላልቻሉ ስላጠፉ ሳይሆን በማንነታቸው ግድያ እስር መፈናቀል ውርደት የእለት ተእለት እጣቸው በመሆኑ ነው ይህንን መንገድ የመረጡት። እንዲህ አልፎ አልፎ እዛና እዚህ በረገጠ ጽሁፍ ስትነጅሳቸው አያለሁ ። ሌሎች ሰዎችም ይህ ጥራት የጎደለው ትችት አእምሮ ያቆሽሻል ለእውቀትም አይጠቅምም ተው ቢሉህም እምቢ ብለሀል።አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ ብልጽግናን የሰራነው ያቀድነውን አላማ ለማስፈጸም ነው ኦርቶዶክስና አማራን እናጠፋለን ብለው በእቅድ ጦርነት ከፍተው ፍዳውን እያሳዩት ነው። አርቆ አሳቢ ይመስል ብዙ ጊዜ እነማርሸትን ስትወግማቸው አያለሁ። ወዳጄ ማሰቢያህን አትቆልፈው ብዙ አዋቂ ሰዎች እዚሁ አምድ ላይ ጠቃሚ ጽሁፍ ያወጣሉ አንብብ በእውቀት ያልካበተ አስተያየት ቀሊል ይሆናል። ተነባቢ ሀሳብ አልኝ ካልክ እራስህን ችለህ አርቲክል አውጣ። ሌሎች የደከሙበትን መዝናኛና መደበሪያ አታድርገው ውርድ ከራስ። ጊዜ አልሄድ ካለህ ሌላ መደበሪያ ነገር ፈልግ በማንኛውም መመዘኛ ካንተ በተሻሉ ልጆች ላይ አታላግጥ ሲሆን ምስጋና በተገባቸው እንደማንኛውም አድር ባይ ስልጣንን ረግጠው ለህዝብ በመቆማቸው። ያም ቢቀር እንዳንተ ስደት ጠይቀው ለመኖር የሚያግዳቸውም አልነበረም። እንደ ፈለገው የሚንሳፈፈውን ሀሳብህን ልጓም ብታበጅለት መልካም ነው ጽሁፍህ አስተማሪ ካልሆነም መልሰህ በግል አድራሻህ ላከው ያንባቢን ጊዜ አታባክን። አመሰግናለሁReplyወስላታና ነገር አውደልዳይ በአንተ አልተጀመረም። አይተናል፡ ኑረንበታል። በሩቅ በሽታቸው ለይተን እናውቃቸዋለን። ከፋትን ተላብሰው ክፋት እንደጫሩ አፈር ተመልሶባቸዋል። እንዳንተ/ቺ ላሉት ከእውነት ጋር ለተጣሉ አውደልዳይ የፓለቲካ አተሎች ሥፍራና ቦታ የለንም። የጻፍኩትን ጽፌአለሁ። ዛሬም ወደፊትም ሰላም እንጂ በለውና በይው ትርፍ የለሽ የአስረሽ ምቺው ፓለቲካ ነው። የአንተና መሰሎችህ የሰው ጥላቻ የራስህን መደንቆር ያሳያል እንጂ ሌላውን አያሳምንም። ዝም ብትል ለአንተም ለሌላውም ትርፍና ሰላም ነው። እባክህ ዝም በል።Replyልሞክር ብዬ ነው እንጅ ማገዶ መጨረስ እንደሆነ ከተገነዘብኩ ቆይቻለሁ። አሁንም ቢሆን ሀሳብ ካለህ እራስህን ችለህ ጽሁፍ ላክ ታረም ማለት ያን ያህል ሊያስከፋህ ባልቻለ ነበር ተያያዥ ችግሮች ተደራርበው ባረቀብህ እንጅ። በል እንግዲህ ምን ይባላል ስድብ ሀሳብ ስላልሆነ ብትችል ቀንሰው መዝገበ ቃላትህ በስድብ ከታጨቀ ከንቱ ድካም ነው በርታ ማለቱ ይሻላል የሰላም ሰው።ReplyLeave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ
የሰላም ድርድርን አሻፋረኝ የሚል ማንም ታጣቂ ሃይል የአለም ፓለቲካ ያልገባው የዛገ አስተሳሰብ ያለው ብቻ ነው። ለዘመናት ከቱርክ ጋር የተፋለመው የከርድስታን ፒኬኬ ተፋላሚ ከዘመናት በህዋላ ለሰላም እጅ መስጠቱ የሽምቅ ውጊያ ጊዜ ያለፈበት መሆኑን ያሳያል። ዛሬ ወያኔና ሻቢያ ደርግን ድል አደረግን ብለው በየዓመቱ ከበሮ እንደሚደልቁት አይነት ውጊያ አሁን ላይ የለም። በእስራኤልና በኢራን የሆነውን አይናችን አፍጠን አይተናል። ከተነገረን ይልቅ የተደበቀው የዚህ ግጭት ዜና ብዙ ነው። በዚህ ላይ የየመን ሁቲዎች ከቀይ ባህር ማዶ የተወነጨፈው ነገሪያቸው እስራኤልን መምታት መቻሉ የጊዜውን በፍጥነት መቀየር ያሳያል። በጫካና በየመንደሩ በመሽሎክሎክ የሚደረጉ ውጊያዎች ደግሞ ነጻ እናወጣሃለን የሚባልለትን ወገን በሁለት ተፋላሚ ሃይሎችም መካከል አስገብቶ ደሃና ሰርቶ አዳሪን የሚያስጨርስ በመሆኑ ፍሬው መራራ ነው። 70 ዓመት ሙሉ የተደነፋበት የሩሲያው የቁስ አካል ፍልስፍና ያ ሁሉ ሃብትና የሰው ሃብት ፈሶበት ነፋስ እንደመታው ድቄት በአንዴ ነው በኖ የጠፋው። ፓለቲካ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው። አይ አልገባኝም የሚል ካለ Secondhand Time: The Last of the Soviets By Svetlana Alexievich የጻፈችውን ማንበብ ነው። የሚያሳዝነው ትውልዷ ዪክሬን ነው። ያኔ አብረው በፍቅር ይኖሩ ነበር አሁን ደግሞ መቧቀስ ከጀመሩ ሶስት ዓመት አለፈው። በሩሲያና በዪክሬን ጦርነት ሳቢያ ሁሉ እየታጠቀ እንደሆነ ከአውሮፓና ከሰሜን አሜሪካ የሚፈልቁ ወሬዎች ይናገራሉ። ዛሬ ላይ ማሰልጠኛ ምልምል ወታደር ገብቶ ሰልጥኖ እስኪወጣ አይጠብቁም ራሱ ማሰልጠኛውን ነው ድምጥማጡን የሚያጠፉት። የአብይ አህመድን አገዛዝ የምናስወግደው እንጂ የምንደራደረው አይደለም መባሉ አላዋቂነት ነው። ቢቻል ነገርን በሰላም መጨረስ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ግን እሺ ያሰብከው ይሁንና አርበኛ ማርሸት ለመሆኑ ምን ዋስትና አለህ አሁን ካለው የከፋ ሌላ መንግስት ነኝ ባይ በሃበሻ ምድር ላለመምጣቱ? ታሪካችን እንደሚያሳየን ከሆነ ከክፋት ወደ ክፋት አንድ አፍራሽ ሌላ አፍራሽ ሲተካው እንጂ የተሻለ ነገር አላየንም። በጠመንጃ አፈሙዝ የሚመጣ ማንኛውም ለውጥ መሰል ነገር ባለንበት በዚህ ዘመን ለሃገርም ለወገንም አይጠቅምምና የፓለቲካ ጥያቄአችሁን በጥቅል አቅርቡና ከመታኮስ ይልቅ በመደራደር ለመጨረስ ብትጥሩ መልካም ነው እላለሁ።Reply
አንተ ሰውዬ ክፍሉን መማሪያ ሳይሆን መደበሪያና ሀሳብ ማጨናገፊያ ነው ያደረግኸው። የምትጽፈውንም የምታውቅ አይመስለኝም እንደ ኮፒ ፔስት አይነት በነጋ በጠባ የምትጽፍልን ይህንኑ ነው። ማርሸት ያንተ ልጅ ይሆናል በትምህርቱም ሁለተኛ ዲግሪውን ይዟል መኖር ቢችል ሽቶውን እየተቀባ ባማረ ፍራሽ ይተኛ ነበር እንጅ በሀሩርና በቁር ከጥይትና ድሮን እየተባረረ መከራውን ባላየ ነበር። ከማርሸት ጋር ብዙ ምሁራንና ፕሮፌሰሮች አሉ እነዚህ በሞታቸው የቆረጡ በተመሳሳይ ሁኔታ መኖር ስላልቻሉ ስላጠፉ ሳይሆን በማንነታቸው ግድያ እስር መፈናቀል ውርደት የእለት ተእለት እጣቸው በመሆኑ ነው ይህንን መንገድ የመረጡት። እንዲህ አልፎ አልፎ እዛና እዚህ በረገጠ ጽሁፍ ስትነጅሳቸው አያለሁ ። ሌሎች ሰዎችም ይህ ጥራት የጎደለው ትችት አእምሮ ያቆሽሻል ለእውቀትም አይጠቅምም ተው ቢሉህም እምቢ ብለሀል።አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ ብልጽግናን የሰራነው ያቀድነውን አላማ ለማስፈጸም ነው ኦርቶዶክስና አማራን እናጠፋለን ብለው በእቅድ ጦርነት ከፍተው ፍዳውን እያሳዩት ነው። አርቆ አሳቢ ይመስል ብዙ ጊዜ እነማርሸትን ስትወግማቸው አያለሁ። ወዳጄ ማሰቢያህን አትቆልፈው ብዙ አዋቂ ሰዎች እዚሁ አምድ ላይ ጠቃሚ ጽሁፍ ያወጣሉ አንብብ በእውቀት ያልካበተ አስተያየት ቀሊል ይሆናል። ተነባቢ ሀሳብ አልኝ ካልክ እራስህን ችለህ አርቲክል አውጣ። ሌሎች የደከሙበትን መዝናኛና መደበሪያ አታድርገው ውርድ ከራስ። ጊዜ አልሄድ ካለህ ሌላ መደበሪያ ነገር ፈልግ በማንኛውም መመዘኛ ካንተ በተሻሉ ልጆች ላይ አታላግጥ ሲሆን ምስጋና በተገባቸው እንደማንኛውም አድር ባይ ስልጣንን ረግጠው ለህዝብ በመቆማቸው። ያም ቢቀር እንዳንተ ስደት ጠይቀው ለመኖር የሚያግዳቸውም አልነበረም። እንደ ፈለገው የሚንሳፈፈውን ሀሳብህን ልጓም ብታበጅለት መልካም ነው ጽሁፍህ አስተማሪ ካልሆነም መልሰህ በግል አድራሻህ ላከው ያንባቢን ጊዜ አታባክን። አመሰግናለሁReply
ወስላታና ነገር አውደልዳይ በአንተ አልተጀመረም። አይተናል፡ ኑረንበታል። በሩቅ በሽታቸው ለይተን እናውቃቸዋለን። ከፋትን ተላብሰው ክፋት እንደጫሩ አፈር ተመልሶባቸዋል። እንዳንተ/ቺ ላሉት ከእውነት ጋር ለተጣሉ አውደልዳይ የፓለቲካ አተሎች ሥፍራና ቦታ የለንም። የጻፍኩትን ጽፌአለሁ። ዛሬም ወደፊትም ሰላም እንጂ በለውና በይው ትርፍ የለሽ የአስረሽ ምቺው ፓለቲካ ነው። የአንተና መሰሎችህ የሰው ጥላቻ የራስህን መደንቆር ያሳያል እንጂ ሌላውን አያሳምንም። ዝም ብትል ለአንተም ለሌላውም ትርፍና ሰላም ነው። እባክህ ዝም በል።Reply
ልሞክር ብዬ ነው እንጅ ማገዶ መጨረስ እንደሆነ ከተገነዘብኩ ቆይቻለሁ። አሁንም ቢሆን ሀሳብ ካለህ እራስህን ችለህ ጽሁፍ ላክ ታረም ማለት ያን ያህል ሊያስከፋህ ባልቻለ ነበር ተያያዥ ችግሮች ተደራርበው ባረቀብህ እንጅ። በል እንግዲህ ምን ይባላል ስድብ ሀሳብ ስላልሆነ ብትችል ቀንሰው መዝገበ ቃላትህ በስድብ ከታጨቀ ከንቱ ድካም ነው በርታ ማለቱ ይሻላል የሰላም ሰው።Reply