ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ ዜጎች ለኛ መሰቃየት ተጠያቂው ብአዴን ነው አሉ

April 15, 2013

ከሚኖሩበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በፍኖተሠላም ሰፍረው  የነበሩት አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች  “እንድፈናቀል ያደረገንና ለደረሰብን  ጉዳት ተጠያቂው የአማራ ክልላዊ  መንግስት ገዢው ፓርቲ ብአዴን ነው፡ ፡” ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡  ተፋናቃዮቹ እንደሚሉት “ስንፈናቀል  ስድብ፣ዛቻ ድብደባ፣እስራትና ዝርፊያ  የደረሰባቸው አሉ፡፡ የስነ ልቦና ጉዳት  ደርሶብናል፡፡ ሀብትና ንብረታችን ጥለን  በ24 ሰዓት ከአካባቢው እንድንወጣ  ተደርገናል፡፡ ለዚህ ሁሉ ድርጊት ግንባር  ቀደም ተጠያቂው ብአዴን ነው” በማለት  ፓርቲውን ወቅሰዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ ለዝግጅት ክፍላችን  እንደሚያስረዱት “በሠላም ሠርተን  በምንኖርበት ቦታ ልዩ ኃይል (ፌዴራል  ፖሊስ) አዝምቶ ያስደበደበንና ከሥራና  ከመኖሪያ ቦታችን ያስወጣን የቤኒሻንጉል  ጉምዝ ክልላዊ መንግስት የአካባቢው  አስተዳዳሪዎች ናቸው፡፡

ምን አጠፋን? ምን በድለናችሁ ነው?  እንዲህ የምታሰቃዩን ብለን ስንጠይቅ   ፤ የክልላችሁ መንግስት የማዳበሪያ  ገንዘብ ዕዳ አለባቸው ፤ነፍስ ገዳዮች  አሉበት፤ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሽፍታ  ማጠራቀሚያ ሆኗል፡፡ ህዝቤን መልሱልኝ   ብሎ ስጠየቀን ነው፡፡ ብለውናል፡፡ ይህ  ሁሉ ድብደባና ዝርፊያ ሲፈፀምብን  ብአዴን ዝም ብሎ ይመለከታል፡፡
ስለዚህ ለደረሰብን ጉዳት ሁሉ ግንባር  ቀደም ተጠያቂው ብአዴን ነው፡፡ ” ሲሉ  በስፍራው ለተገኙት የፍኖተ ነፃነት  ጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡  
ቁጥራቸው በግምት ከ 3ሺ በላይ የሆኑ  እንዚህ ተፈናቃዮች በጊዜያዊነት ሰፍረው  በነበረበት ፍኖተ ሰላ ከተማ ተገኝተው  ለነበሩት የፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኞች  እንዳስረዱት “ቤት ንብረታችንን  እንዳለ ጥለን እንድንወጣ ተደርገናል፡ ፡ ያመረትነውን ሰብል አልሰበሰብንም፡ ፡ የእርሻ በሬዎቻችንን ሜዳ ላይ ጥለን  እንድንወጣ ተደርገናል፡፡  ደብድበናል፤  ፖሊስ ጣቢያ ታስረን ለእያንዳንዳችን  ለትራንስፖር ብር 350 እየከፈልን  ከአካባቢው እንድንወጣ ተደርገናል፡ ፡ ፍኖተሠላም ከመጣን በኃላ ከእኛ  መካከል የማዳበሪያ ዕዳ ያለበት ማነው?  ነፍስ ገድሎ የተሸሸገስ ማነው ብለን  ብንጠይቅ የብአዴን ተወካዮች እኛ እንዲህ አላልንም እያሉን ነው፡፡ እናንተ  እንዲህ ካላችሁ ይህ ሁሉ ድርጊት  ሲፈፀምብን ለምን ዝምታን መረጣችሁ?  ብለን ስንጠይቅ መልስ አይሰጡንም ”  በማለት በፍፁም ምሬት ተናግረዋል፡፡  በቀን ሁለት ጊዜ በ4 ሰዓትና በ11 ሰዓት  መንግስት ምግብ ያቀርብላቸው እንደነበር  የሚናገሩትት እነዚህ ተፈናቃዮች  ኖተሠላም ለበሽታ አጋላጭ በሆነ ስፍራ(ቄራ) ላይ ያለመጠለያ ሜዳ ላይ  እንዲያድሩ በደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ ከ1995 ዓ/ም ጀምሮ በአካባቢው እንደኖሩ የሚናገሩት እነዚሁ ተፈናቃዮች “ከነበርንበት ቦታ ከወጣን በኃላ የነበርንበት አካባቢ ባለሥልጣናት የዘረኝነትና የጥላቻ ቅስቀሳ ፈጽመውብናል” በማለት ወደቤንሻንጉል ከተመለሱ በኋላ አደጋ እንዳጋጥማቸው መስጋታቸውን ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

Go toTop