በጎንደር ጎርጎራ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተመቶ ተከስክሷል June 15, 2025 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email በጎንደር ጎርጎራ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተመቶ ተከስክሷል Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email 1 Comment Leave a Replyጎበዝ የቸገረን እኮ እውነቱን ከፈጠራ ወሬ መለየት ነው። ዘመኑ ተጣርሷል። ለመኖሪያ ብልሃት ያልተሰበረ ወሬ ተሰበረ ተብሎ ይቀርብልናል። ላሰበው ተሰባሪ ወሬ ገና ከጅምሩ አንካሳ በመሆኑ ሙሉነት የለውም። ግን የምዕራቡ የቁስ አካል ፍቅር አይንና ልቡን ያጠነበዘው ዘይቤ ከምስራቁ የፕሮፓጋንዳ አሸንዳ ጋር ተጣምሮ ይኸው ዓለምን ሁሉ በገማ ወሬ አሽቶታል። ለዚህ ነው የግጭትና የጦርነት የመጀመሪያ ሰለባ እውነት ራሷ ናት የተባለው። አሁን በጎርጎራ ተከሰከሰ ስለተባለው ሄሊኮፕተር እውነቱን የሚያውቁት ውስጡ የነበሩት ብቻ ናቸው። ግን እነርሱም አንቀላፍተው ይሆናል። ከምድር ወደ ላይ ሆኖ ተኩሼ ጣልኩ እንዲህ አደረኩ እያሉ ትንፋሽ እስኪያጥር መለፍለፍ መረጃ አልባ ከንቱ ነው። እድሜ የቆጠረ፤ በሃገር የተጠገነ፤ ሄሊኮፕተር ወድቆ መከስከሱ አያስፎክርም። የጠፋው የሃገር ሃብት የሞቱት የቤተሰብና የሃገር ሃላፊዎች ቤተሰብና ዘመድ ጥለው ነው። ይህ በሰው ሞት ሻምፓኝ መክፈትን ወያኔና ሻቢያ ያቃመሱት ከሞት ተራፊ፤ ፍርፋሪ ለቃሚ የፓለቲካ ቱልቱላ ሁሉ ወሬ እያባዛ ቢነዛ ጠቀሜታ የለውም። በሃገር ውድመትና በሰው ሞት ደስ የሚለው የቁም ሙት እንጂ ጤናማ ሰው አይደለምና! ባጭሩ የሃገራችን ፓለቲካ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ሆኗል። ለንገሩ ዛሬ የቀን ሌባው ስለበዛ ከብቶችም የቁም እስረኛ ሆነው በቤት መዋል ከጀመሩ እኮ ቆይቷል። አይ ሃገር ሁሌ በለው ያዘው፤ ገልብጠው፤ ግደለው እያሉ ከአንድ ገራፊና ዘራፊ ወደ ሌላው መሸጋገር። ስንገርም። ዓለም ጥሎን ነጉዷል እኛ ግን ዛሬም ነገም የምናኘከው የዘርና የጎሳ እንዲሁም የቋንቋ ፓለቲካ ጤንነታችን ቀምቷል፤ ቤተሰብ ንዷል፤ ሃገር አፍርሷል። ውጤቱ በዜሮ ማባዛት ብቻ ሆኗል። ስዊዲናዊው ገጣሚ Frans Gunnar Bengtsson ከዘመናት በፊት እንዲህ ብሎ ነበር። The seagull knows a way to rest the human heart, on earth does not know yet! መቸ ነው ቀናችን የፓለቲካ ማስቲካ ከማኘክ ተላቆ መኖር የምንጀምረው? እናቁም ጦርነትን ማዳመቅ፤ ግድያን ማወደስ፤ በሞት ላይ ጉልት ማቆም። እውነት ሄሊኮፕተሩ ተመቶም ሆነ በራሱ ችግር ተከስክሶ ሰዎች መጎዳታቸው ለማንም ቢሆን የደስታ ምንጭ ሊሆን አይገባምና ስለ ራስህ ኑሮና እልፈት እያሰብክ ዛሬን ደስ ብሎህ ማንንም ሳትበድል ኑር። ለነገው ዋስትና የለንምና!ReplyLeave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ
ጎበዝ የቸገረን እኮ እውነቱን ከፈጠራ ወሬ መለየት ነው። ዘመኑ ተጣርሷል። ለመኖሪያ ብልሃት ያልተሰበረ ወሬ ተሰበረ ተብሎ ይቀርብልናል። ላሰበው ተሰባሪ ወሬ ገና ከጅምሩ አንካሳ በመሆኑ ሙሉነት የለውም። ግን የምዕራቡ የቁስ አካል ፍቅር አይንና ልቡን ያጠነበዘው ዘይቤ ከምስራቁ የፕሮፓጋንዳ አሸንዳ ጋር ተጣምሮ ይኸው ዓለምን ሁሉ በገማ ወሬ አሽቶታል። ለዚህ ነው የግጭትና የጦርነት የመጀመሪያ ሰለባ እውነት ራሷ ናት የተባለው። አሁን በጎርጎራ ተከሰከሰ ስለተባለው ሄሊኮፕተር እውነቱን የሚያውቁት ውስጡ የነበሩት ብቻ ናቸው። ግን እነርሱም አንቀላፍተው ይሆናል። ከምድር ወደ ላይ ሆኖ ተኩሼ ጣልኩ እንዲህ አደረኩ እያሉ ትንፋሽ እስኪያጥር መለፍለፍ መረጃ አልባ ከንቱ ነው። እድሜ የቆጠረ፤ በሃገር የተጠገነ፤ ሄሊኮፕተር ወድቆ መከስከሱ አያስፎክርም። የጠፋው የሃገር ሃብት የሞቱት የቤተሰብና የሃገር ሃላፊዎች ቤተሰብና ዘመድ ጥለው ነው። ይህ በሰው ሞት ሻምፓኝ መክፈትን ወያኔና ሻቢያ ያቃመሱት ከሞት ተራፊ፤ ፍርፋሪ ለቃሚ የፓለቲካ ቱልቱላ ሁሉ ወሬ እያባዛ ቢነዛ ጠቀሜታ የለውም። በሃገር ውድመትና በሰው ሞት ደስ የሚለው የቁም ሙት እንጂ ጤናማ ሰው አይደለምና! ባጭሩ የሃገራችን ፓለቲካ ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ሆኗል። ለንገሩ ዛሬ የቀን ሌባው ስለበዛ ከብቶችም የቁም እስረኛ ሆነው በቤት መዋል ከጀመሩ እኮ ቆይቷል። አይ ሃገር ሁሌ በለው ያዘው፤ ገልብጠው፤ ግደለው እያሉ ከአንድ ገራፊና ዘራፊ ወደ ሌላው መሸጋገር። ስንገርም። ዓለም ጥሎን ነጉዷል እኛ ግን ዛሬም ነገም የምናኘከው የዘርና የጎሳ እንዲሁም የቋንቋ ፓለቲካ ጤንነታችን ቀምቷል፤ ቤተሰብ ንዷል፤ ሃገር አፍርሷል። ውጤቱ በዜሮ ማባዛት ብቻ ሆኗል። ስዊዲናዊው ገጣሚ Frans Gunnar Bengtsson ከዘመናት በፊት እንዲህ ብሎ ነበር። The seagull knows a way to rest the human heart, on earth does not know yet! መቸ ነው ቀናችን የፓለቲካ ማስቲካ ከማኘክ ተላቆ መኖር የምንጀምረው? እናቁም ጦርነትን ማዳመቅ፤ ግድያን ማወደስ፤ በሞት ላይ ጉልት ማቆም። እውነት ሄሊኮፕተሩ ተመቶም ሆነ በራሱ ችግር ተከስክሶ ሰዎች መጎዳታቸው ለማንም ቢሆን የደስታ ምንጭ ሊሆን አይገባምና ስለ ራስህ ኑሮና እልፈት እያሰብክ ዛሬን ደስ ብሎህ ማንንም ሳትበድል ኑር። ለነገው ዋስትና የለንምና!Reply