አጋቹ: የሰባተኛው መታሰቢያ ግጥሞች April 2, 2025 ዜና Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ያምናው ጆሮ ጠቢየታቻምናው ሰላይሲደረግ የበላይሁሉንም አግቶወህኒ አድርጎታል አገሩን ለሕዝቡ፤ከእርሱ በቀር የለምወደዚህ ወደዚያ የሚል እንደልቡ።ብስክሌት ቢነዳ፣እግር ኳስ ቢጫወት፣ሩጫ ቢወዳደር ፣የልጅነት ሕልሙንሲቀጭ ቢተዳደር፤መውጣትና መግባት፣መታየት መሽቀርቀርየተፈቀደለትየለም ከርሱ በቀር።በጠገበ ድመትእንደተያዘች አይጥ ሁለት ዓይኑ ጠፍቶመጫወቻ ሁኗል ሰው ሁሉ ታግቶ።የሰባ አመት ጓይላበሸገርበሀገርምንድነው ይህ ዘፈን?ሰባት አመት ሙሉ ጆሯችን የሰማውቁርቁዝና ቃሉ ብልጽግና ዜማውጠረፍ አገር ወድቆ ርስቱን የተቀማውቁርጥ ቤት ሲጋፋ ደላላው አሳማውአመቱ ሲመለስ ኡደቱን ተጎዞካምናውም የባሰ እልቂት ፍጅት ይዞየዘር ግጭት ጽፈውበጎራ አሰልፈውካፈጃጁት ወጣት በእድል የተረፈውኦሮሞና ትግሬ አፋሩ አማራውእየተሰደደ እግሩ ወዳመራውሸገር ደሞ ማማውሴትኛ አዳሪኛላይ ላዩን ተቀብቶ በርቶበት ከተማውበቻይና ፌካ ፌክ ሲታይ አሸብርቆመንገዱ በውሃምሽቱ በብርሃን ሳለ ተጥለቅልቆበየጓዳው ግናጨለማ ውስጥ ያለው ሕፃን አፉ ደርቆሴፍቲኔት ሰልፈኛውበልቡ ተራግሞ በአፉ ግን መርቆየበሻሻው አጭቤመያዣ የሌለው የተሙለጨለጨእንደ ሴት አዳሪ እያብለጨለጨብቻውን ሲበላ እያቁለጨለጨአከራይ ተከራይበጠኔ ሲበራይጉዳይ ያለው ሁሉ በጉቦ ታግቶበዘረፋ እንጂመኖር ብርቅ ሲሆን በላብ በወዝ ሠርቶእንደሰው አይተነው ሲሆን እንዳራዊትቁንጫና ትኋን የተባይ ሠራዊትየጨፈሩበትን ያኔ በበሻሻቂም በቀል ሲወጣ ዛሬ በሀበሻሰባት አመት ብቻ አይመስልም ዘመኑበጭንቅ በጣር በጋር ተጎትቶ ቀኑሰባ አመት አርጅቷል አካልም ልቡናስብርብር/ብር ብለን በሰበሩ ዜናየት አግኝተን ሰላም የት አግኝተን ጤናየዘመን ታማሚ የዘመን ታካሚውአላፊ አግዳሚውገጹ ተጨራምቶተርቦ ተጠምቶወዙ ሙጥጥ ብሎ ጠፍቶ የበፊቱአቧራ ነፍቶበት አመድ መስሎ ፊቱታቻምና ተቅሞ ዘንድሮ ሲገረብርስቱ እስከነነፍሱ ተሽጦ ለአረብሞተ እንዳይባል አለ በቁመናአለ እንዳይባል ተስፋው ሆኗል መናበቀቢጸ ተስፋኑሮን እየገፋአይመጣብኝም ሲል ከዛሬ የከፋበነጋው ሰማዩ ላዩ ላይ ሲደፋታግቶ ሲጠፋ መኪና ሙሉ ሰውጉድጓድ ሙሉ አስከሬን ሲቀብሩ አልቅሰውከመድረክ ፊት ለፊትትኩረት ማዘናጊያው ጩኸት ነክቶ ጣራመድረክ በስተጀርባለባዕዳን ተሽጦ የሀገር አንጡራገልታ ገልታ ሚለውበመከራው ጓይላሞተ እንዳይባል አለ አልሞተም ገናአለም እንዳይባልአይለማም አይሰማም ነፍስያው በድናእንዲህ ነው ሚመስለውሰባቱን ሰባ አመት ስናጠቃልለው። Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ