እነዶ/ር ደብረፅዮን እና በጠ/ሚ ዐብይ አህመድ በተሾሙት የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት መሪዎች እነጌታቸው ረዳ መካከል የነበረው አለመግባባት ተካርሮ ሰራዊቱን ወደውግንና አስገብቷል።
የትግራይ ሐይል አዛዦች ትላንት ባወጡት መግለጫ ውግንናቸው ከእነዶ/ር ደብረፅዮን ጋር መኾኑን አስታውቀዋል።
የትግራይ ሐይል አዛዦች በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያለው ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዲረከብ እንደሚሹ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
በሌላ በኩል ፓርቲውን ለማፍረስ እና አመራሩን ለመበተን እያሴሩ ነው በማለት ህወሓት የኢትዮጵያ መንግስትን እና የምርጫ ቦርድን ወንጅሏል። በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራዉ የህወሓት ክንፍ ቁጥጥር ኮምሽን ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ በአስቸኳይ የህወሓት ሕጋዊነት ሰውነት ሊመለስ ይገባል ብሏል።
በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ
የትግራይ ሐይል አዛዦች ያስተላለፉት ውሳኔ በትግራይ ሥርዓት አልበኝነትን የሚያነግስ ነው በማለት አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
መግለጫው እንደሚለው የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች “ከተልእኳቸው ውጭ ለአንድ ሕገወጥ ቡድን ወግነው ግዚያዊ አስተዳደሩን የማፍረስ፣ ስርዓት አልባነት የማንገስ እና ሰራዊት የመበተን ግልፅ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል” ብሏል።
የትግራይ ሐይል አዛዦች በትላንትናው ዕለት ያስተላለፉትን ውሳኔ ግዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀውና “ሕጋዊ ይሁን ሞራላዊ ቅቡልነት የሌለው” ሲል ያመለከተው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር መግለጫ፤ ከዚህ በተጨማሪ የፕሪቶርያ ውልንም ለአደጋ የሚያጋልጥ እና ኃላፊነት የጎደለው ብሎታል።
(ከጀርመን ድምፅ ተወስዶ የተቀናበረ)
የፈጣሪ ረቂቅ ስራው እንዴት ይመረመራል? እኛ ዛሬ ካልሆነ ብለን ያዙኝ ልቀቁኝ እንላለን አምላክ ደግሞ ጠብቅ የኔ የጊዜ ሰሌዳ ዛሬ አይደለም ይልሃል፡፡ እነዚህ የቀን ጅቦች የሃገሪቱን አጥንት ግጠው ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ አገር ተሰብስቦ አንድ እንዳይሆን በህገ መንገስት አገር በትነው፤ የሃገሪቱን ሃብት እንዳሻቸው ሲጫወቱበት ትግሬ ቁጥሩ አንሷቸው ተጎራብች ክልሎችንም የትግሬ ዜግነት ሰጥተው ፤የሚጠብቃቸውን መከላከያ አርደው ይኸው የጥጋባቸው ስበት አመዝኖ ነገሩ ሁሉ ተጠቅልሎ ወደ እነሱዉ ሄደ፡፡
ታዲያ ምን ያደርጋል ትላንት ምንም እንዳላደረጉ ሁሉ ዛሬም ተነቅለው አዲስ አበባ፤ ባህር ዳር፤ ጎንደር ፈልሰው ገብተዋል መቼም ይሉኝታ እንሱ ዘንድ የለችምና፡፡ ነገ ከጉዳታቸው ሲያገግሙ ወደ ተሰሩበት ተንኮልና ሸር ይመለሳሉ፡፡ እስቲ የአቶ ሰረቀ ብርሃን ጸሎት የት እንደሚያደርሳቸው ዝም ብሎ ማየት ነው፡፡ እንደው ሰው አይውጣልህ ተብሎ እንደተረገመ ሁሉ ጠቅላላ ሁሉም ከአንድ ፋብሪካ እንደተሰራ ሳሙና አንድ አይነት ሲሆን ይገርማል፡፡ ባለፈው እናቶች አባቶች በእምብርክክ ሲለምኑዋቸው የተምበረከኩትን እየረገጡ ያለፉት በታሪክ ተመዝግቦ ይቀመጥ ሳይውል ሳያድር ስብሃት ነጋና ቡድኑ ተበለሻሽተው ከዋሻው ሲወጡ ያለውን ትርኢትም አዳምሮ መመልከት ለቋሚ ጥሩ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡
አይ ጊዜ ትላንት ጌቾን ያየ ደ/ጽዮንን ያየ ዛሬ ይሄ ይመጣል ብሎ ይጠረጥራል? አንዱ ጦርነት ባህላችን ነው ሲል ሰየ አብረሃ ጦርነት እንሰራለን ይልሃል አቶ ጻድቃን ደግሞ በታላቅ ኩራት ሌላ ይልሃል አቶ ታደሰ ወረደ ጦሩን አሽመደመድነው ይልሃል፡፡ እረ ተው ቢባሉ አንት ሽንታም ማለት ጀመሩ፡፡ ታዲያ ያ ሁሉ ጥጋብ አልፎ ፕሪቶሪያ ላይ ለጌቾ ያሉህን ሁሉ ፈርመህ ነብሳችንን አድነው ብለው ተማጸኑ፤ ያለንን መሳሪያ ሁሉ እናወርዳለን ተረክቡን አሉ፤ ሬድዋን ሁሴን የመኖር ስጋት አለባቸው አያስረክቡም አሉ ሳይውል ሳያድር ጥጋባቸው ባረቀባቸው፡፡ አሁን አሁን ላይ ጌቾም ነብሷ ተጨንቋል ደ/ጽዮንም ጦርነት ቢከፈት የሚንደባለሉ ትግሬዎች ላይወጡልኝ ይችላሉ ብሎ ስጋት በስጋት ሁኗል ተንደባላዮቹም በየሃገሩ አይን ይብላችሁ ሲባሉ ቀሪውም ትያትሩ ገብቶት ምላሱን ቆልፎ ቁጭ ብሏል፡፡ እስቲ የሚሆነውን ማየት ነው በርቱ
ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ሁኖ ነው እንጅ አብይ የሾመውን ባለስልጣን እንዲህ እንዳይሆን አድርጎ ማባረር ምን ይባላል እዚህ ላይ አይቆሙም እኮ ጻድቃንንም አብረው ሳይሸኙት አይቀሩም፡፡ ጌቾ በዛ በክፉ ጦርነት እንኳን እንዲህ ተጎሳቁሎ አላየሁትም ራያነቱን መዘውበት ይሆን? ነግረን ነበር ሰሚ ጠፋ እሱም ተወደድኩ ብሎ ከቄሱ በላይ ቄስ ሆነ እንግዲህ ማን ያውጣህ አብይም ሆነ ስብሃት፤አረናል ሆነ ባይቶና(ባይተዋር) ከኔ ጋር ይቆማሉ ብለህ አታስብ በእኛ በኩል ስራህ ያውጣህ ነው የምንለው ብዙ ፋይል ውስጥ ያስቀመጥናቸው ቪዲዮ፤ኡዲዮና ማህደሮች ስላሉን፡፡ ንስሃ እንዳትገባ ለነብሱ ያደረ ቄስ በዚያ በኩል የለም፡፡
በትግራይ የሚፈጠር አዲስ ነገር የለም። ያው ከበረሃ እስከ ከተማ በህዝብ ላይና በራሳቸው ታጋዮች ላይ ሳይቀር የፈጸሙት በደል እንቅልፍ ነስቷቸው እንሆ አሁንም ጎራ ለይተው ሊፋለሙ ተፋጠዋል። ይህ እብደት ነው የማይል የትግራይ ተወላጅ ካለ ስለ ትግራይ ህዝብ ደህንነት የማያስብ ቆረንጮ ሃሳብ የተጫነው ነው። እነዚህ የቁም ሙቶች የሞቱት ጓዶቻቸውን በተኙበት ሲረሽኑ፤ ከህዋላ አስተኩሰው ሲያስገድሉ፤ የሰሜን እዝን አመራሮች ራት ጠርተው እጃቸውን በካቴና ሲያስሩ፤ ሌሎችን በተኙበት ገድለው አስከሬን ከበው ሲጨፍሩ ያኔ ነው የሞቱት። ከዚያ በህዋላ ያለቀው የትግራይ ልጅ መሳሪያውን አዙሮ እነርሱን ነበር መፋለም የነበረበት። ግን ዝንተ ዓለም ኤርትራ ጠላትህ ናት፤ አማራ የችግርህ ሁሉ መንስኤ ነው እየተባለ የተንኮል ፓለቲካ የተጋተ በቀላሉ መንቃት አይችልም። በዚህም የተነሳ ሶስት ጊዜ ከብልጽግና ጋር ተፋልሞ ዋጋ ከፍሎና ሌሎችን አክስሮ መቀሌ ላይ በመሰብሰብ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለው የወያኔ መንጋ ሰውንም ፈጣሪንም የማይፈራ ጥርቅም ነው። ያኔ ያን ሁሉ መሳሪያና ታንክ ይዞ በአሜሪካ እየተረዳ ያልሆነለት አሁን ማን ይሙት ሌላ ጦርነት የትግራይ ህዝብ ምርጫ ነው። እነዚህ ሙታን ወታደራዊ አዛዦችንና እሳት ቆስቋሾችን አንድ ላይ አጠራቅሞ እስርቤት መዝጋት ነው። እነርሱ ቆመው እየሄድ የትግራይ ህዝብ ሰላም አያገኝምና!
የሚያሳዝነው አንዳንድ የፓለቲካን ክስረትና ጠመዝማዛ መንገድ ለይተው የማያውቁ ፋኖ ሲደመር ኦነግ ሲደመር ወያኔ ጥሩ ሃይል ይወጣዋል እያሉ ሲጽፉ ሳይ የሃበሻው የፓለቲካ እብደት ጭርቅ ማስወለቁን ለመረዳት አይከብድም። ለሃገራችን የሚያስፈልገው ሰላም ነው። ሌላው የድምርም ሆነ የተናጠል የውጊያ ስልት አይተነዋል አይረባም። አያዋጣም። ጀግና እንደ አቶ ልደቱ አያሌው ሞትም ቢሆን መኖር ለእኔ ሃገሬ ይሻለኛል በማለት ወደ ሃገሩ በሰላም ገብቶ ለመፋለም ቆርጦ መሄድ እንጂ እዚህ በየስርቻው ተስጠው የህዝባችን መከራ ለማራዘም በብሄርም ሆነ በሌላ የፓለቲካ ስብጥር ውስጥ ሆነው በስማ በለው በለው የሚሉ ሁሉ እብዶች ናቸው። የብልጽግናው መንግስት አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ሃገሩ ሲመለስ ቢያስረው የመንግስቱን ክርፋት ያሳያልና እንዳያደርገው እንመክራለን። ለሰው ልጅ መኖርም መሞትም የማይቀር ነው። አቶ ልደቱ ሊታሰር አይገባውም። የሚያደርገው የሰላም አስተዋጾ ካለ ይመቸው ብሎ መተው ነው። ግን እየገደሉና እያሰሩ እኔ የለሁበትም ማለቱ ግን ዞሮ በራስ ላይ መከራን ያመጣልና ከእንደዚህ ያለ ድርቡሻዊ ድርጊት ብልጽግና ሊቆጠብ ይገባል። መንግስትን በግድያና በጅምላ እስራት ማሰንበት ይቻላል ዘላቂነት ግን አይኖረውም። ፈታ ለቀቅ ይበል ህዝቡ!
ወደ ወያኔ እንዘጥ እንዘጥ ስንመለስ ከላይ ተፈርዶ ከሆነ እርስ በእርስ ተጨራርሰው ትግራይ ሰላም ትሆን ይሆናል። እስከ መቼ የትግራይ እናቶች ያልቅሱ? የቁም ሙቶች ይሙቱና ሰላም ይወረድ! 50 ዓመት ሙሉ መከራ አይበቃም? ትግራይ ሰላም መሆን የምትችለው ወያኔ ሲከስም ብቻ ነው። ለግምገማ፤ ለስብሰባ፤ ለመግለጫ ወዘተ የሚያጠፉትን ጊዜና ሰአት ለሥራ ቢጠቀሙበት ጦርነት ለመማዘዝና ሌላውን ወደ እሳት ለመማገድ ጊዜ ባላገኙም ነበር። በመጨረሻ አንድ ትዝ ያለኝን ነገር ላካፍላችሁ።
ከመቀሌ በአውቶብስ ተሳፍረን ወደ አዲስ አበባ እየሄድን ነው። ሹፌሩ ቀጅቃጃ ከመሆኑ የተነሳ ሥጋት ይዞናል። ወደ 50 ሰዎች ተጭነናል። እረፍት ልናረግ ስንወርድ ሾፌሩን ምነው አውቶብሱ ስም የለውም አልነው። አይ ሰሞኑን ነው ቀለም የቀባነው አለ። እንዴ አዲስ እኮ አይደለም ስንለው አዎን ከአዲስ አበባ አምበሳ አውቶብስ የነበረ ነው ወደ መቀሌ አምጥተን ቀለም ቀባነው አለንና ሁላችን ሳቅን።አዲስ አበባ በሰላም በተሰረቀ የህዝብ ሃብት ደረሰን። አይ ጊዜ ስንቱን ነገር ወያኔ አተራመሰው። ስንቱ በየጥሻው በወያኔ ካድሬዎች በጥይት ተደብድቦ ሞተ? ለነገሩማ ማንን እንግደል ብለው ስብሰባ የሚቀመጡ እብዶች አይደሉምን? የእውቋ ዘፋኝ የአበበች ደራራ አባት አምቦ ላይ የተገደሉት በዚህ ስልት አይደለምን? የአቶ ደራራ ደም ዛሬም ለፍትይ ይጮሃል! የሚገርመው እዚያ ስብሰባ ላይ ቁጭ ብለው እጅ አውጥተው አዛውንቱ ነጋዴ እንዲገደሉ ያደረጉት በሰላም ይኖራሉ። ስናሳዝን። የደም እንጀራ እየጎረሱ መኖር። ሞት ይመረጣል!