የብልፅግናው መሪ አብይ አህመድ የአማራን ህዝብ በሀይል ረግጨ እገዛለሁ በሚል የቀቢፀ ተስፋ ቅዠት ከጥር ወር 2015 ዓ /ም ጀምሮ ወታደር በማዝመት ውጊያ የጀመረ ሲሆን በወቅቱ ያሰበው እቅድ ባለመሳካቱ ወረራውን ህጋዊ ለማድረግ ሀምሌ 28 / 2015 ዓ/ም አስቸኳይ አዋጅ በማወጅ ይህንንም በማራዘም ሁሉን አቀፍ እርምጃዎች በመውሰድ ያሰበውን ማሳካት አልቻለም ።
አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ የጥፋት እቅድ በማውጣት የተቀናጀ የአየር ሀይል ጥቃት ለመፈፀም ተዘጋጅታል።
አብይ አህመድ የሚመራው ሚስጥራዊ ቡድን
፩፦ ከኢትዮጵያ ካርታ ስራዎች ድርጅት ፣
፪፦ ከኢንሳ ፣
፫፦ ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የተወጣጡ የጂኦ ስፓሻል ባለሙያዎችን በመምረጥ በአይሮፕላን ለ21 ቀናት በአማራ ክልል የአሰሳ ጥናቶችን አድርጎ ቦታዎችን የመለየት ስራዎችን አጠናቋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉት ቦታዎች ተለይተዋል ፦
1. በሰሜን ጎንደር የተለዩ ቦታዎች ፦
ቋራ እና መተማና አካባቢው፣
2. በደቡብ ጎንደር ፦
እስቴ እና ስማዳ እና አካባቢው፣
3. በምስራቅ ጎጃም ፦
አማኑኤል ዙሪያ ፣ ፈንድቃ ፣ መሶቢት ፣ ፣መርጦለማሪያም፣ሞጣ እና አካባቢው፣
4. ሰሜንወሎ፦
ወልዲያ፣ሲሪንቃ፣ ተኩለሽ እና ቃሊም እና አካባቢው፣
5. ሰሜንሽዋ፦
ይፋት እና ሬማ እና አካባቢው፣
እነዚህ ተለይተው ኦፕሪሽን ሊሰራባቸው የታቀዱ 15 ቦታዎች ናቸው።
አብይ አህመድ ይህን ሚስጥራዊ ቡድን የሚሰበስበው እና የመለየት ስራዎችን የሚሰራው እንዲሁም ህዳር 02 / 2017 ዓ/ም የአየር ሀይል አዛዡን ይልማ መርዳሳን እና የሰሜን ምዕራብ አየር ሀይል ቀጠና አዛዡን ከባህርዳር በማስመጣት የዘመቻ ትዕዛዝ የሰጠበት የቢሮው አድራሻ አዲስአበባ ወሎ ሰፈር የኢንሳ ዋና መስሪያ ቤት 14ኛ ፣ 15ኛ ፣16ኛ ፎቆችን የሚጠቀም መሆኑ ተረጋግጧል።
በአማራ ክልል ከላይ የተመረጡ 15 ቦታዎችን መደብደብ የታቀደው በተዋጊ ጀቶች ፣ በሂሊኮፍተር እና በድሮን ሲሆን ለዚህ ተልዕኮ የሚሆኑ 3 ተዋጊ ጀቶች እና 4 ሂሊኮፍተር ባህርዳር ምድብ አየር ሀይል ውስጥ ይገኛሉ፤ ተፈላጊው ተተኳሾች ፣ ነዳጅ እና መለዋወጫ እቃዎች ገብተዋል።
በመሆኑም በተጠቀሱት ቦታዎች የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት እና ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ መረጃው ይድረሳቸው።
በቀጣይ የምድቡ አዛዥ እና አብራሪዎችን ስም ዝርዝር እነገልፃለን ።
ከታማኝ ውስጣዊ የመረጃ ምንጭ የተገኘ
አሳየ ደርቤ
–