https://youtu.be/9l6iNo9Mbf8?si=Jz_eY-hhufDLqVNE
የአማራ ፋኖ በጎጃም አንድ ወጥ አማራዊ ድርጅት ለመፍጠር የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ የቆዬ መሆኑ ይታወቃል
ይህንን በመፍጠር ሂደት ውስጥ በርካታ ውጣ ውረዶችን ከታለፈ በኃላ ለአመራር እጩነት የተቀመጡትን መስፈርቶች የማያሟላ ግለሰብ ለእጩነት ካልቀረብኩ በሚል ምክንያት ያስነሳውን ውዝግብ ተከትሎ በቃለ-መሃላ ጭምር ያፀደቅነውን መስፈርት በመጣስ እና የተስማማንበትን ህግ እና አሰራር በሚጣረስ መንገድ የተጀመረዉን የእጩ ምልመላ አካሄድ በህግ በማስረጃ እና በምክንያት አስደግፈን ተቃውሞ አቅርበናል::
ይሁን እንጅ ለቀረበው መከራከሪያ እና ተቃውሞ እልባት ባልተሰጠበት ሁኔታ ከተቀመጡት የእጩነት መስፈርቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑትን ማሟላት የማይችል ግለሰብ ከዚህ በፊትም ያደርግ እንደነበረው ራሱን ሰብሳቢ አድርጎ መሾሙን በሚዲያ መነገሩን ሰምተናል::
መሪር መስዋዕትነት የሚከፈልበትን ትግል ለግለሰቦች ያልተገራ ፍላጎት አሳልፎ መስጠት እንደማይገባ ስለምንረዳ በወሰድነው አቋም ምክንያት በሚዲያ የተገለፀው ጉዳይ የማይመለከተን መሆኑን እናሳውቃለን::
በመሆኑም የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራር ትግሉን የመምራት ብቻ ሳይሆን አብዮቱን ከጠላፊወች የመጠበቅ ግዴታውንም ጭምር በሚገባ የሚወጣ መሆኑንም እናረጋግጣለን::
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
አስረስ ማረ ዳምጤ
ያለፉ ድምፆች አሁንም ሰሚ ይሻሉ…
pic.twitter.com/Fjte3Q9SPq— JusticeIsNotFree (@Amharafirst88) July 17, 2024