ኣንድ የፋኖ ድርጅት ወይንስ ኣንድ የፋኖ መሪ?
ኣንድ መሆን ለምን ኣቃታን ዘመነ ካሴ?
ኣንድ መሆን ለምን ኣቃታን ዘመነ ካሴ?
ፋኖ ታምራዊ እድገት ኣሳይቷል:: ግዙፍ ድርጅት በኣራቱም የኣማራ ክፍለ ሀገራት ፈጥሯል:: ነገር ግን ኣራቱ ኣንድ ለመሆን ጊዜ ወሰደ:: የህዝቡንም መሰዋትነት ጨመረ:: ኣማራ ጠሉ መንግስት ግልፅ የሆነ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ነው:: ፋኖን መመክት ሲያቅተው ፋኖ ሲያጠቃው መደዳውን የኣማራን ህዝብ መጨፍጨፍ ቋሚ ኣካሄድ ኣድርጎታል:: ይህ ኣካሄድ በኣስቸኯይ መቆም ኣለበት::
ፍኖ ኣንድ መሪ መምረጥ የበለጠ ያስቸገረው ይመስላል:: ኣንድ መሪ ቢመርጥም ለምን ጎጃም ለምን ወሎ ለምን ሽዋ ለምን ከጎንደር በሚል ኣኩራፊ ሊበዛ ይችላል:: ኣኩራፊዎች ደግሞ ትግሉን ሊጎትቱት ይችላሉ::
ስለዚህ ፋኖ ኣንድ መሪ ሳይሆን ኣንድ ድርጅት ነው የሚያስፈልገው:: የቡድን ኣመራር ማለት ነው:: ኣራቱ ክፍላተ ሀገራት በጋራ ለመስራት ምንም ችግር የለም:: ስለዚህ ቀጥሎ መምጣት ያለበት በመጀመሪያ የስራ ዘርፎችን መለየት ማለትም የጦር መሪ ምክትል መሪ ህዝብ ግንኙነት ምክትል ፀሐፊ የውጭ ጉዳይ ስትራቴጂስት የፖለቲካ ሃላፊ ሎጂስቲክ ወዘተ በማለት የስራ ዘርፎችን ማውጣት::ለምሳሌ ኣስራ ስድት የስራ ዘርፎች ካሉ ከኣራቱ ክላፋተ ሀገራት ኣራት ኣራት ፋኖዎች በመምረጥ ኣስራ ስድት የስራ ዘርፎች ላይ መመደብ:: መሪ የሚባል ሳይኖር በቡድን መምራት::
ለምሳሌ ኣብይ የሚባል ጠቅላይ ሚንስቴር ባይኖር ኢትዮጵያ ይህንን ያህል እልቂት ኣይደርስባትም ነበር:: ሰራዊቱን መካላከያ ሚንስቴር ቢመራው ግብርናውን ግብርና ሚንስቴር ጤናውን ጤና ሚንስተር ወዘተ ሆኖ በቡድን ቢመሩ ኣምባ ገነን ኣብይ ኣይኖርም ነበር:: ስለዚህ ኣንድ መሪ የሚለውን ኣጥፎቶ ፋኖ ኣንድ ድርጅት የሚለው ላይ ቢያተኩር ጥሩ ነው ምን ትላላችሁ?