ጭራቅ አሕመድ ያማራን ሕዝብ በልቶ ለመጨረስ ቆርጦ የተነሳ የኦሮሙማ አውሬ ቢሆንም፣ አውሬውን እንደ እንዝርት የሚያሾረውና ባማራ ሕዝብ ላይ የሚያሰማራው ግን ‹‹ቀድሞ የይፋ አሁን የሕቡዕ አለቃየ›› እያለ አለቅጥ የሚሽቆጠቆጥለት፣ በመሠሪነቱ ወደር የሌለው ሸለመጥማጡ ለማ መገርሳ ነው፡፡ አሁን ላይ ግን ጭራቅ አሕመድ ለለማ መገርሳ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ ስለመጣ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ረሽኖ ያስወግደዋል፡፡ ለምን እና እንዴት የሚለውን ደግሞ ባጭሩ እንመልከት፡፡
በፖለቲካ ብስለታቸው አንቱ የሚባሉትን ጨምሮ አያሌ ጉምቱ ሰወች ጭራቅ አሕመድ ለማ መገርሳን ከስልጣን አስወግዶ፣ ከሀገር አስወጥቶ ከጨዋታ ውጭ አርጎታል እያሉ እጅጉን ሲሳሳቱ ይደመጣሉ፡፡ ይህን ትልቅ ስህተት የሚፈጽሙት ደግሞ የለማ መገርሳን የመሠሪነት ጥልቅት ባለመረዳትና፣ ዐላማውን በምን መንገድ እንደሚያስፈጽምና ማስፈጸም እንደሚፈልግ ባለማወቅ ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ ጃዋርን አሰረው የተባለው፣ እስክንድርን ለማሰር ጭራቅ አሕመድና ጃዋር ሙሐመድ የተጫወቱት ቀልድ እንደነበረ ሁሉ፣ ጭራቅ አሕመድ ለማ መገርሳን አባርረው የሚባለው ደግሞ አማራን ለማታለል ጭራቅ አሕመድና ለማ መገርሳ የተጫወቱት ቀልድ ነበር፡፡
ጭራቅ አሕመድን ጨምሮ ሁሉንም ኦሮሙሜወች በየመደበላቸው የሥራ ድርሻቸው የሚያሰማራቸውና የሚከታተላቸው የኦሮሙማ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆነው ኦቦ ለማ መገርሳ ነው፡፡ የኦሮሙማ ፕሮጅከት ሊሳካ የሚችለው ደግሞ በኦነግ ጥንካሬ ሳይሆን ባማራ ድክመት እንደሆነ ከለማ መገርሳ በላይ የሚያቅ የለም፡፡ ያማራ ድክመት ደግሞ ካማራነቱ በላይ ኢትዮጵያን ማፍቀሩ ነው፡፡ ስለዚህም፣ ለማ መገርሳ የኦሮሙማ ፕሮጀክቱን ማስፈጸም ይችል የነበረው ኢትዮጵያን የሚያፈቅር መስሎ በመቅረብ ነበር፡፡ የወያኔ የደህንነት ኃላፊ ሆኖ ኢትዮጵያን ሲያጠፋ እንዳልነበር፣ ወያኔ ሊወድቅ ሲንገዳገድ በድንገት ተነስቶ ኢትዮጵያ ሱሴ ያለውም ኢትዮጵያ ሱሱ ሁናበት ሳይሆን በኢትዮጵያ ፍቅር የወደቀውን አማራን ለማነሁለል ሲል ብቻ ነበር፡፡
ያዲሳባ የዲሞግራፊ ቅይራ ንግግሩ ይፋ ከወጣበት በኋላ ግን ለማ መገርሳ አማራን ማታለል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ የነ ዲባቶ (ዶክተር) አምባቸው የባሕርዳር ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ጭፍጨፋውን ያካሄደውን መከላከያን ይመራ የነበረው እሱ መሆኑ ደግሞ የለማ መገርሳን ማንነት ይበልጥ ይፋ አደረገው፡፡ ስለዚህም አማራን እያዳከመለት የኦሮሙማን ፕሮጀክት ለመፈጸም እስካስቻለው ድረስ፣ ጭራቅ አሕመድን ከፊት አድርጎ ከኋላ ሁኖ ከመምራት ውጭ ምርጫ አጣ፡፡
አሁን ላይ ግን ጭራቅ አሕመድ አማራን የሚያታልልባቸውን ትሪኮቹን (tricks) ተጠቅሞ ጨርሷል፡፡ ካሁን በኋላ ጭራቅ አሕመድ በኃይል ካልሆነ በስተቀር አማራን በማታለል ሊፈጽም የሚችለው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ባማራ ሕዝብ ላይ ይፋ ጦርነት የከፈተውም በዚሁ ምክኒያት ነው፡፡ ጭራቅ አሕመድ አማራን ማታለል ካልቻለ ደግሞ ለለማ መገርሳ የኦሮሙማ ፕሮጀክት ምንም ጥቅም የለውም፡፡ እንዲያውም ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ስለዚህም ባስቸኳይ ያስወግደዋል፡፡
ጭራቅ አሕመድ ስለነጻነት ምንነት ምንም ባማያውቅበት ዕድሜው፣ ኦሮሞን ካማራ ነጻ ለማውጣት ጫካ የገባ የኦነግ የሕፃን ወታደር (child soldier) ነበር፡፡ የኦነግ የሕፃን ወታደር የነበረ በመሆኑ ደግሞ በኦነግ አለቅጥ የተነወረ (ነውር የተፈጸመበት abused) የነውር በሽተኛ (abused child) ነው፡፡ የኦነግ የሕፃን ወታደር የነበረ ከመሆኑ በላይ አናቱ አማራ ናቸው መባሉ፣ ያባቱ ማንነት ደግሞ በውል አለመታውቁ በኦነግ የተፈጸመበትን ነውር ይበልጥ የከፋ አድርጎታል፡፡ የተማረ ነው ይባል የነበርው ሃይሌ ፊዳ፣ አባቱ የመናዊ በመሆናቸው ምክኒያት በማንነቱ ያን ያህል ተሰቃይቶ ኦሮሞነቱ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳይገባ ሲል ብቻ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ልሁን ካለ፣ አናቱ አማራ ናቸው የሚባሉት ምንም ትምህርት የሌለው ጭራቅ አሕመድ ደግሞ አሮሞነቱ እንዳይጠርጠር ሲል ብቻ አማራን ከምድረግጽ ሊያጠፋ ቢነሳ ምንም አያስገርምም፡፡
እንደ ጭራቅ አሕመድ ያለ፣ ከሕፃንነቱ ጀምሮ አለቅጥ የተነወረ የነውር በሽተኛ፣ /ነዋሪወቹን/ (ነውር የፈጸሙበትን) ለማስደሰት ሲል ምንም ከማድርግ አይመለስም፡፡ መዱስ (መጽሐፍ ቅዱስ) እንደሚያስተምረን አብርሃም ለጌታው /ያለውን/ ታማኝነት ለማስመስከር ልጁን ይስሐቅን ለእርድ እንዳቀረበ፣ ጭራቅ አሕመድ ደግሞ ‹‹ቀድሞ የይፋ አሁን የሕቡዕ አለቃየ›› ለሚለው ለጌታው ለለማ መገርሳ ያለውን ታማኝነት ለማስመስከር አማራን ማረድ ሳይሆን ልጆችህን እረድ ቢለው በደስታ ያርዳል፡፡
ያንድ ብሔር አባል አለመሆኑ የሚጠረጠር ግለሰብ ወዶም ሆነ በነውር ተገዶ የዚያ ብሔር ብሔርተኛ ከሆነ፣ ጥርጣሬውን ለማስወገድ ሲል ብቻ ማናቸውንም አረመኔያዊ ድርጊት ለመፈጸም ቅንጣት አያቅማማም፡፡ ሂትለር ይሁዳወችን ያለ ርኅራኄ የጨፈጨፈበት አንዱ ምክኒያት፣ የይሁዳ ደም አለበት የሚባለውን ጭምጭምታ ለማስተባበል ነበር፡፡ ምሥራቅ አውሮጳውያን (ቸኮች፣ ፖሊሾች፣ ዩክሬኖች፣ ክሮአቶች…) ካንግሎ ሳክሶኖች በከፋ ሁኔታ ዘረኛ መስለው ለመታየት የሚጥሩት፣ ከነጭ አይቆጥሩንም ለሚሏቸው ለምዕራብ አውሮጳውያን ነጮች መሆናቸውን ለማስመስክር ሲሉ ነው፡፡ ያሜሪቃ ጥቁር ፖሊስ ከነጭ ፖሊስ የበለጠ በጥቁር ላይ የሚጨክነው፣ ታማኝነቱን ለነጭ አለቆቹ ለማሳየት ነው፡፡ ባባቱ አማራ ነው የሚባለው ጌታቸው አሰፋ ያማራ ሳጥናኤል የሆነው፣ ትግሬነቱን ለማስመስከር ነበር፡፡
ጭራቅ አሕመድ ደግሞ በናቱ አማራ ነው ከመባሉ በላይ የተጋባው ጎንደሬ ናት ከምትባል ሴት ጋር ነው፡፡ ስለዚህም በጎጠኝነት የሰከሩት የኦሮሞ ጽንፈኞች ጭራቅ አሕመድን ከአሮሞ አይቆጥሩትም፡፡ እንደማይቆጥሩት ደግሞ እሱ ራሱ በደንብ ማወቅ ብቻ ሳይሆን አልቅጥ ያስጭንቀዋል፡፡ ኦሮሞነቴን ማንም አይሰጠኝም፣ ማንም አይነፍገኝም፣ እናቴ አማርኛ አትችልም እያለ ሳይጠይቁት የባጥ የቆጡን የሚቅባጥረው ይሄን ጭንቅቱን ለማለዘብ ነው፡፡
ጭራቅ አሕመድ በኦሮሞነቱ ስለማይታመን ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቅና እያንዳንዷ ድርጊቱ ባጉሊ መነጽር እንደምትመረመር አሳምሮ ያውቃል፡፡ ትንሽ ቢሳሳት ግዙፍ ውለታው መና ቀርቶ ከሃዲ እንደሚባል ነጋሪ አያስፈልገውም፡፡ እስከጣፈጠ ድረስ ተላምጦ የሚተፉ አገዳ መሆኑን በደንብ ያውቃል፡፡ ስለዚህም ጥፍጥናውን ላለማጣት ሲል ብቻ ማናቸውንም ፀራማራ ድርጊት ለመፈጸም ቅንጣት አያቅማማም፡፡ የሱ ጽኑ ፍላጎት ደሞ ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት ስለሆነ፣ ትናንት ከጣፈጠው የበለጥ ዛሬ መጣፈጥ ነው፡፡ ስለዚህም ጥፍጥናውን ለመጨመር ሲል፣ ትናንት ቶሌ ላይ ያማራን ሕጻናት ግዳይ እንደ ጣለ፣ ነገ ጉለሌ ላይ፣ ከነገ ወዲያ ደግሞ ቦሌ ላይ ግዳይ ለመጣል ሙሉ ዝግጁ ነው፡፡
በለማ መገርሳ እይታ ግን፣ የጭራቅ አሕመድ ጥፍጥና አማራን ማታልለና ማዘናጋት መቻሉ ሲሆን፣ ይህን ጥፍጥናውን ደግሞ ሙሉ በሙሉ በማጣት ታኝኮ የተጨረሰ አገዳ ሁኗል፡፡ ስለዚህም ለማ መገርሳ በቅርቡ ይተፋዋል፡፡ ጭራቅ አሕመድን ተፈቶ ሲጠለው ደግሞ፣ ቱሲወች (Tutsi) የሁቱወችን (Hutu) መሪ ሃብያሪማናን (Habyarimana) እንደገደሉት አማሮች የኦሮሞወችን መሪ ዐብይ አሕመድን ገደሉት በማለት እልፍ አእላፍ አማሮችን ባንድ ጀምበር በመጨፍጨፍ የኦሮሙማ ፕሮጀክቱን ከግብ ለማድረስ ይጠቅምበታል፡፡ ጭራቅ አሕመድ በለማ መገርሳ ቀጭን ትዕዛዝ ግርማ የሺጥላ ላይ የፈጸመውን፣ ለማ መገርሳ ደግሞ በራሱ በጭራቅ አሕመድ ላይ ይፈጽምበታል፡፡ የጭራቅ አሕመድ መፃኢ ዕጣ በለማ መገርሳ ቀጭን ትእዛዝ በሽመልስ አብዲሳ መረሸን ነው፡፡
ስለዚህም ያማራ ሕዝብ ሆይ፣ ጭራቅ አሕመድ ግርማ የሺጠላን አስወግዶ ይፋ ጦርነት እንደጀመረብህ፣ ለማ መገርሳም ጭራቅ አሕመድን አስወገዶ ይፋ ጭፍጨፋ ሊጀምርብህ መሆኑን አውቅህ፣ ራስህን ከጭፍጨፋ ለማዳን ማድረግ ያለብህን ሁሉ ከወዲሁ አድርግ፡፡
መስፍን አረጋ
mesfin.arega@gmail.com