August 28, 2023
7 mins read

አገሩን አርማ ጌዲዮን አድርገህ ወዴት ትሸሻለህ? – በዳዊት ሳሙኤል

Bekele Gerba 3ዛሬ አንድ የፌስ ቡክ ጓደኛየ የአቶ በቀለ ገርባን ሽሽት ከተመለከተ በኋላ የሚከተለውን መልእክት ጻፈ። ” አገሩን አርማጌድዮን አደገህ ብልሆች ወደ ሰሩት አገር በነጻነት ለመኖር ሄድክ? “
አባባሉ እኔንም ወደ ዛሬ ስድስት አመት ትዝታየ ወሰደኝ።
በወቅቱ በቀለ ገርባ፣ እስክንድር ነጋ፣ አንዷለም አራጌ ወዘተ በወያኔ አፋኝ መንግስት ታስረው ፎቶአቸው እየተያዘ Free Bekele Gerba, Free Eskindir Nega.. የሚባልበት ወቅት ነበር። አስደናቂው በጎንደር ህዝቡ የበቀለን ፎቶ ይዞ ሰልፍ ይወጣ ነበር።
መፈታት አይቀርምና ሁሉም ተፈቱ። በዲያስፖራው ትልቅ ደስታ ሆነ። እኛም በጀርመን የምንገኝ የተወሰን ሰዎች አዳራሽ ውስጥ ሁነን በጋራ ስልክ ተመስገን ደሳለኝ ቤት እንዳሉ ሁሉንም የቀድሞ የፖለቲካ እስረኞችን አነጋገርናቸው።
የግብዣ ወረቀት እንደምንልክላቸውና መጥተው የናፈቃቸውን ኢትዮጵያዊ እንዲያገኙት። ከበቀለ ውጭ ሁሉም እሽ አሉ። በቀለ ሰንካላ ምክንያት ሰጥቶ እንደማይችል ነገረን። በማግስቱ ወያኔ ያልተፈቀደ ባንድራ ሰቅለዋል ብሎ ከበቀለ ውጭ ሁሉንም እንደገና አሰራቸው። በጥቂት ቀናትም መልሶ ለቀቃቸው።
ለውጥ መጣ ህዝብ በደስታ ሰከረ። ኦሮማራ ጥምረት ተብሎ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር በፍቅር አበደ።
እስረኞች ሁሉ ተፈቱ። በዚህ ወቅት ህዝብ  በደስታ ጡዘት  ባለበት በቀለ ገርባ ፍጹም ሙልጭ ባለ አረመኔነትና ክህደት በተሞላበት አምስት የኦሮሞ ፖለቲካ ድርጅቶችን ሰብስቦ ራሱ በሚያነበው መግለጫ ሰጠ። አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፣ መኖር የፈለገ መኖር ይችላል። ያልፈለገ ግን ለቆ መሄድ ይችላል የሚል።
እነሆ ታላቁ ጦርነት ተጀመረ!
ሁሉ ነገር ትርምስምሱ ወጣ። በየ አቅጣጫው የቃላት ውርወራው ተጀመረ። ሟቹ የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ዶ/ር አምባቸው ፍርጥም ያለ መልስ ስለ ጉዳዩ ሰጡ። እነ በቀለ የዲቃላ ፖለቲካን ጀመሩ። ኦሮምኛ ላላወራችሁ እቃ አትሽጡ አለ በኢፋ ወጥቶ። በሰበብ ባስባቡ ረብሻ በማስነሳት የሰው ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ። መቀሌ ሂዶ ከቀድሞ አሳሪዎቹ ጋር በይፋ ተጨባበጠ። ከሰማኒያ አመት በፊት በጀርመን የነበሩ ናዚዎች የተጠቀሙበትን ቃላት ሁሉ በይፋ በየሚድያው ሰበኩ።
የቀድሞው የእስር ቤት ጓደኛው፣ ከተፈቱም በኋላ አብረው በአንድ ቤት ውስጥ በስልክ ያወራናቸው ጓደኛው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ጓደኞቹ በአዲስ አበባ ካሳንችስ ባልደራስ በተባለ ቦታ ያን በንዴት የጦፈን የአዲስ አበባ ወጣት ስብሰባ ጠርተው መጀመሪያ እንደ ሲቪክ ማህበር በኋላ የፖለቲካ ድርጅት የሆነን ፖርቲ አቋቋሙ። የለውጡ ሞተር ነን የሚሉት መንገዳቸው ቁልቁለቱ የዚያን ግዜ ጀመረ።
በቀለና ጓደኞቹም በየቦታው እየዞሩ የዘረኝነቱን ስብከት ቀጠሉበት። እነሱንም ተከትሎ በዘረኝነት የሰከሩ ወጣቶች ጅምላ ግድያውን ገፉበት። ምድሪቱ ሲኦል ሆነች። በመጨረሻ በቀለም እስክንድርም እንደገና እስር ቤት ገቡ። እስክንድር ለምን እንደገባ እስከ አሁን ለኔ ምንም ግልጽ ምክንያት አላገኘሁም።
ዛሬ ያ በየስርቻው ለአምስት አመት ደሙ የፈሰሰው ሚስክን የአማራ ገበሬ በደሉ ተሰምቶ ሁሉን አቀፍ የነፍጥ ውጊያ በመላው አማራ ክልል ተከፈተ። በሌሎች ቦታዎችም ህዝቡ የራሱን ጥያቄ ይዞ ተቃውሞ እየወጣ ነው። ነገሮች በፍጥነት እየተቀያየሩ ነው። በዚህ ወቅት በቀለ ገርባ  እሱ ችቦውን የለኮሰው የጥፋት እልቂት ባመጣው ጣጣ ህዝብ እምቢ ብሎ ሲነሳ እሱ ብልሆች በጥንቃቄ በህግና በስርአት ወደሰሯት ታላቋ አሜሪካ ገብቶ ጥገኝነት ጠየቀ። ከአማራ ጋር አትጋቡ፣ ንግድ አትነግዱ ወዘተ እያለ በአንድ ሀገር ውስጥ መኖር ያልቻለ ሰው በሰው ሀገር ከነጭ ጋር አብሮ ሊኖር ተሰደደ።
እውነተኛው ፍርድ በመጣ ግዜ የትስ ቢገባ ማምለጥ ይቻላል። የእነዛ አገር ደህና ብለው በየጎጆአቸው ተቀምጠው የነበሩ ሴቶችና ህጻናት፣ አዛውንቶች አማሮች በከንቱ የፈሰሰ ደም በምድርስ በሰማይስ ያስቀምጣል ወይ?
ማጠቃለያ፣
ባንድ ወቅት የነገረኝን ሰው ብረሳውም። የበቀለ የቅርብ ዘመድ ህዝቡ የእሱን ፎቶ ይዞ በየሰልፉ ሲወጣ አይቶ። ” አየ የኢትዮጵያ ህዝብ በቀለን ቢያውቀው ምንኛ ያዝን” አለ የተባለውን ሳስታውስ የኢትዮጵያ ህዝብ እጅጉን አንጀቴን ይበላኛል። ላለፉት አርባ አመት በላይ የሚፈልገውና እየሆነበት ያለው ነገር ከሰማይና ከምድር የተራራቀ በመሆኑ ወደፊት እጅግ ጥንቃቄ የተሞላበት ጉዞ ማድረግ እንዳለበት እመክራለሁ።
በቄ ሆይ የለኮስከው ጦርነት የድሀውን ልጅ ብቻ በልቶ አይቀርም። አንተንም ለፍርድ አደባብይ ያቀርብሀል።
ይዘገያል እንጅ ወንጀለኛ ለፍርድ ይቀርባል!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop