ዳንዔል ክብረት የሚታወቅበትን ተረት ተረት ትቶ ፉከራ ላይ ተጠምዷል – መሳይ መኮነን

August 10, 2023

አንዴ ከሳትክ፡ ጨርቅህን ጥለህ ካበድክ መመለሻም የለህ። የአብይ አህመድ ራፖር ጸሀፊ፡ ቃለጉባዔ ያዥ፡ ሶፍትና መሀረብ አቀባይ፡ እራቱን ሲበላ ሻማ ያዥ፡ የፈለገውን የመሆን መብቱ የተጠበቀ ነው። የ100ሺህ የአዲስ አበባ ህዝብ ድምጽ ይዞ የአቢይ እግር ስር መርመጥመጡን በተመለከተ ግን ድምጽ የሰጠው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሊያስብበት ይገባል። የጎባጣ አሽከር ለምን አጎንብሰህ ትሄዳለህ ቢሉት ጌታዬን ለመምሰል እንዳለው፡ ዳንዔል በፖለቲካ ክስረት ለጎበጠው አብይ ጎብጦለት ቀርቷል። ታማኝነቱ እስከቀራኒዮ ነው። የምን ክርስቶስ?! የምን ሃይማኖት?! አብይ ሁለቱንም ተክቶለታል። ጋሽ ስብሃት ገብረእግዚያብሄር ‘እኔ በአይኔ ያየሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ቼጉቬራን ነው’ እንዳለው ዳንዔልም ክርስቶስን በአይኑ አይቶታል – ‘አብይን’። እንደሌላው ክርስቲያን ህዝብ የክርስቶስን ዳግም መምጣት አይናፍቅም። ክርስቶስ መጥቶለታል። አግኝቶታል። ለዳንዔል ከዚህ በላይ ምን ዓለም አለለት?!

ከዚያች ከቤተመንግስት ነጯ ቢሮ ቁጭ ይልና ‘ጃውሳ’ እያለ ሲፎክርና ሲሸልል ይውላል። በደህና ጊዜ ብልጽግና የሚሉት ሸለፈት ፓርቲ የማያላምጥ፡ ዝም ብሎ የሚውጥ ግሪሳ ሰብስቦለታል። የወፍ ጫጩት አፏን ከፍታ የእናቷን ጥሬ እንደምትጠብቀው ዳንዔልም ለግሪሳው ቀለብ የምትሆን ወሬ ጣል ለማድረግ ከነጯ ቢሮ ነጭ በርጩማ ላይ ቁጢጥ ይላል። ‘ጃውሳ’ ብሎ ይጀምራል። ግሪሳው ጠብ ሲል ጠብቆ ላፍ ያደርጋል። የሚገርመኝ የዳንዔልን ቤተመንግስት ገብቶ ከአብይ እግር ስር መውደቅ ሲረግሙና ሲያጣጥሉ የሰነበቱት የኦሮሞ ብሄርተኞች ሰሞኑን ፕሮፋይል ፎቶአቸውን በዳንዔል ፎቶ ቀይረው ‘ጀባዱ ሌንጫ አባ ቢያ’ እያሉለት ነው። የፖለቲካ ውስልትናና አንሶላ መጋፈፍ ብልጽግና መንደር የወርቅ ዋንጫ የሚያሸልም ሆኗል። ዳንዔል ብዙ ዋንጫ እያገኘ ነው።

ዳንዔል ቀረርቶውን ቀንሶ ቅኔውን ቢጨምርበት የሚል ጭላንጭል ተስፋ ይዤ ነበር። ህዝብን ጨፍጭፎ፡ ህጻናትን ረፍርፎ፡ ህንጻና ቅርስ አውድሞ ከተማ የገባን የአብይ ሰራዊት ጭካኔ እንደ ድል ቆጥሮ ‘ከጃውሳ ጋር ድርድር የለም’ እያለ ይፎክራል። ቆይ ትንሽ ታገስ ቢባል ጆሮዬን የዝሆን ያድርገው እያለ ነው። የአብይ አፍ ሆኖ ይሸልላል። የብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት መሪነትን ቦታ ይዞ ‘እስቲ ወንድ የሆነ ይሞክረን’ አይነት ፉከራ ጀምሯል። የለገሰ ቱሉን ስራ ነጥቆታል። ‘ከዳመና በላይ’ እንደንስር የሚለው የለገሰ ቱሉ ቅዠት ሳይሻል አይቀርም። ለገሰ እንደአሽሙረኛ ነገረኛ ባልቴት አንገቱን እየነቀነቀ ‘ጉም ውስጥ ከሚበረው፡ ሰማየ ሰማያትን ከሚቀዝፈው ብልጽግና ጋር ወደፊት’ ሲል ይደንቀኝ ነበር። ዳንዔል መጣና በአስር ክንድ ገፈተረው። የለገሰን የእንጀራ ገመድ እንዳይበጥስበት ያሰጋል። ዳንዔል ቁልቁለቱን ተያይዞታል። መጨረሻዬን ያሳምረው’ ማለትም አንድ ነገር ነው። ለንሰሀ መብቃትም እኮ መታደል ነው። እንደሰው ኖሮ እንደእንስሳ ከመሞት ይሰውረን። ዳንዔል ስለራሱ በመጻፉ ግን ልናደንቀው ይገባል።

366278610 6560095337369386 7998301712599287287 n 1 1

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

Go toTop