መፀለይ አሁን ነው ! – አሸናፊ ዋቅቶላ፣ ሕ/ዶ -የውስጥ ሕክምና ባለሙያ March 18, 2023 ግጥም Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email ቋንቋው በረከተ ፣ መግባቢያው ቀነሰ፣አንባጓሮ በዛ፣ ማዳመጥ አነሰ፣ወጣት ጯሂ ሆነ፣ ባዛውንቱም ባሰ፣አማኝ ነኝ የሚለው፣ እዚያም ያልደረሰ፣ሁሉም ዓለም ይላል፣ዓለም ዓለም ዓለም!ከራሱ በስተቀር፣የሚያስብ ግን የለም። ~ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣ መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ!መነጋገር ቢኖር፣ ባለከፋ ነበረ፣በመጯጯህ ብዛት፣ ሁሉም ደነቆረ፣ያጓራል ለብቻው ፣ ያጓራል በጋራ፣ቁልቁል እየሮጠ፣ ትውልድ ሆኖ ተራ፣ያራዳ ጎርምሳ ቤተ-እምነት ዘለቀ፣ቀዳሽ አስቀዳሹም፣ ማዋከብ አወቀ፣ ~ ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣ መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ!ሕዝብን ሜዳ ጥሎ፣ ብር እያሳደደ፣ተው ባዩ ጠፋና፣ ባንድላይ አበደ፣ወርቅ ሰላም ሞልቶ፣ በሁሉ ሰው ቤት፣የብር ግርግር፣ ከተተው አዘቅት፣ሞላጫው ዘራፊ፣ ምኑንም ሳያውቅ፣ፈላስፋ ሆነብን፣በጊዜ መድርቅ። ~ ዘመኑ ጨለመ ፣ ተስፋ መነመነ፣ መፀለይ አሁን ነው፣ ያመነ ያላመነ!አሸናፊ ዋቅቶላ፣ ሕ/ዶ -የውስጥ ሕክምና ባለሙያሲልቨርስፕሪንግ ሜሪላንድ- ዩ ኤስ ኤማርች 18፣ 2023 Facebook X Linkedin Pinterest Telegram Whatsapp Email Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Δ