June 13, 2022
21 mins read

 በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በተከታታይና ያለመሰልቸት የሚደጋገም የጥፋት ዓላማ ይብቃ! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

Abiy Liaras he sees fit his preservat ” Hobbes argues that men are naturally equal in mind and body . As to strength of the body , the weakest has enough strength to kill the strongest. either by assassinating  him secretly or by aligning  himself   with others for the purpose .

Thomas Hobbs remarks   cynically is proof that men are equal rather than unequal .

john Locke in the Hobbes state of nature he said  that,  there is no natural law only natural rights each individual doing ion and enhancement  of power .

ለዚህ ይመሥላል Nicoolo Machiavelli  “ The rules of power have priority over those of ethics and morality. ያለው ። “ Dynamics of illegitimate power .” ይሉሃል ይሄ ነው ።

የማጥፋት   ኃይል ሁሉም ሰው በተፈጥሮ ተሰጥቶታል ። ይህንን ተፈጥሮ የሰጠቺውን ኃይል  ባስገዳጅ ጊዜ እና ወደ እብደት የሚወስድ ገጠመኝ  በአእምሮው ሲከሰት ስው ልጅ ሊጠቀም ይችላል ። በዚህ የጉልበተኝነት ደመነፍሳዊ ክስተትም ፤ ሰው በግልና በተናጥል  በበቂ ምክንያት ና ያለበቂ ምክንያት አምሳያውን ሲያጠፋ ሁሌም ይስተዋላል ፡፡ …

ሰው ፤ በግልፅ ና በሰውር ሴራ  አምሳያውን በሽቅድድም እየገደለ መፎከሩን ዛሬም ቀጥሎበታል ፡፡ ሆን ብሎ አስቦበት ፣ አሥልቶ ፣በጥልቅ አሥቦ ና ግዜ ወሥዶ ፣ ትክክለኛ ቦታ ና ጊዜ መርጦ   ፣ በአመቺ የመግደያ ወረዳ  ውሥጥ ታዳኙ ሰው ሲያጋጥመው ፤ ኃይለኛውን ግለሰብ ወይም ቡድን ደካማ የተባለ ግለሰብ ወይም ቡድን ከምድረ ገፅ ሊያጠፋው ይችላል ፡፡ ይኽንን እውነት  ታሪክ ደጋግሞ  አሳይቶናል ። ( … )

ሆብስም ፣  ጆን ሎክ ና ማኬቬሌ ፣ በዚህ ሃሳብ በእጅጉ ይስማማሉ ። በሞራል አሥተምህሮት ፤ በሎጂክ በመጠቀም ፤ አሥደማሚ እውነቶችን ለደቀመዛሙርቶቻቸው ያካፈሉት ሆብሥም ሆኑ ሎክ እንዲሁም ኒኮል ማኬቬሌ ፣ እያንዳንዱን ግለሰብ የአሁን አቅሙን በመመልከት ብቻ አኮስሶ ማየትና መጨቆን ተገቢ እንዳልሆነ ይመክራሉ ። ” የጠሉት ሊወርስ ይችላል ። የናቁትም ሲነግሥ በማየት ሞትን ሲያስመርጥ ታሪክ አሳይቶናልም   ። ” ይላሉ ፡፡

” የሰው ልጅ በኃይልህ ፈፅሞ አትመካ አንድ አምላክ አለና በኃይሉ ኃይልን የሚለካ ” ሥትል አንድ  የፈጣሪ አመሥጋኝ ፣ የኦ/ተ/ቤ / አማኝ መዘመሯንም እግረ መንገዴን  ላሥታውሥህ ።

እናም በኢትዮጵያም ሆነ በመላው አፍሪካ የምናሥተውለው ፤ ሥልጣንን ለመቆናጠጥ የሚደረግ ትግል  ፤ ኢ _ ዴሞክራሲያዊ እና ዜጋውን ተጠቃሚ ለማድረግ … ህዝብን ያማከለ ፤ በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚደረግ ግልፅ ፣በእውነት ላይ የተመሠረተ ፣ ፍትሐዊ የሆነ ፣ የህዝብን   ሥልጣን ሰጪነት ያረጋገጠ    ፤ የሥልጣን ፈላጊ ፖለቲከኞች ቅቡልነት ያለው የፉክክር  ሂደት  የሚታይበት አይደለም ። በአመዛኙ ፡፡

በአመዛኙ የሥልጣን መተካካት እንኳ ሲደረግ የምናስተውለው ፣  ሥልጣንን ይዞ ፣ ሥልጣን ያሥገኘለትን ጥቅም ፣ ማለትም የተቀናጣ ኑሮ እና  ምቾት ላለማጣት ፣ በተቻለው  አቅም ሥልጣኑንን  ላለመልቀቅ በያዛቸው መንግሥታዊ ማውቀሮች ከለላ እና እገዛ   ሲፋለም ነው ፡፡  ፍልሚያውም አብዛኛውን ጊዜ ፣   በከንፈር ሽንገላ ተጀምሮ ፤   ህዝብን በሠላ ምላስ አደናግሮ በፓርቲ ዓባል ብዛት ኃይሉን አሳይቶ ፤  ዳሃውን ህዝብ ” ዶሮ ማታ ! ”  እያለ ሥልጣን በመያዝ የሚጠናቀቅ ነው ፡፡  በአፍሪካችን በአመዛኙ ፣ ስልጣን ላይ ለመንጦላጦል የሚደረገውም እሩጫ ህዝብን ለማገልገል ሳይሆን በህዝብ ስም ለመገልገል ነው ፡፡ …

ሥልጣን ከያዘው ፣ከገዢው ፖርቲ ጋር  ወደፖለቲካ ግጥሚያ ውሥጥ የሚገቡትም ተቀናቃኝ ፖርቲዎች አብዛኞቹ ፣ ሁሉም ሰው በሚመለከተው ፣ ባፈጠጠው የመንግሥት ችግር ላይ እንጂ በድብቁ የመንግሥት  ውሥጣዊ ችግር  ላይ አያተኩሩም ፡፡በህዝብ ዋነኛ ችግር ፣ በድህነት ላይ  ሲያተኩሩና የህዝቡን ቀዳሚ ጩኸት ሲጮኹ አናያቸውም ። ይህ ጠለቅ ያለ ፖለቲካዊ ትንታኔ የሚጠይቅ የአፍሪካ ፖለቲካ ችግር ነው ፡፡

በአገራችንም ለመንግስት ሥልጣን ሚወዳደሩ ፓርቲዎች ፣ ቁጥራቸው ቢበዛም ፣  የገዢው ፖርቲን የታወቀ ችግር ከመተንተን ባለፈ የህዝብን መሰረታዊ ችግር ስልጣን ብትሰጡኝ በአምስት ዓመት እፈታለሁ ፡፡ በማለት ታማኒ ፕሮግራማቸውን ግልፅ አያደርጉልንም ። …

የገዢውን ፖርቲ ውሥጣዊ ችግር በማጋለጥ ፣የተሻሉ ፖሊሲዎች ሰንጃለሁና እነዚህን ለህዝብና ለአገር የሚጠቅሙ ፖሊሲዎቼን ተግባራዊ ለማድረግ እንድችል የመሪውን ወንበር ፍቀዱልኝ   በማለት ህዝብን አይጎተጉቱም ።  በእውነት ና በቅንነት አገለግላችኋለሁ ፡፡ ሌባ አይደለሁም ፡፡  ” በዓባላቶቼ ውስጥ ሌባ ካለም ፈፅሞ አልታገሰም ፡፡ ”  ሲሉ ከቶም አይደመጡም ። የወደፊቱን የመሪነት ርእዮትም  በግልፅ አያስቀምጡም ።  መንግሥታቸው ቅይጥ ርእዮተ ዓለም ይኑረው ፣አንድ ወጥ  ይሁን ፤ አልያም ደግሞ  ሞናርኪያዊ ፤    ሌበራል እና ኮሚኒሥት ግልፅ  አይዶሎጂ አያራምዱም ፡፡ በቃ አሃዳዊ ነን  ። ወይም ደግሞ ቋንቋን ያላማከለ ፌደራሊዝምን እንከተላለን በማለት በግልጽ አይናገሩም ፡፡ ዙሪያ ጥምጥም ግን ይዞራሉ ፡፡  ለምሳሌ  በመጨረሻ አገራችንን ሲመራ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት   ” አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ፡፡ ” ርእዮተ ዓለሜ ። ልማታዊ መንግሥት ነኝ ። ” ሲለን ነበር ።  እንዲህ ሲል ኮሚኒሥትም ነኝ ። ቡርዣም ነኝ ።  ማለቱ እንደሆነ ማወቅ አልተቻለም ፡፡  ለፖለቲካ ሣይንቲስቶችም ግራ ያጋባ በብዥታ የተሞላ ርዕዮት ነበረ።

ዛሬሥ ? ዛሬ ኢትዮጵያ እየመራት ያለው አሻጋሪነቱን ይጨርስ አይጨርስ ያለትገነዘብኩለት ገዢ ፓርቲ ( ብልፅግና )  የሚከተለው አይዶሎጂ ወይም ርዕዮት ምንድነው? ወደ ሥልጣን ሲመጣ ያነሳቸውን ሃሳቦች በወጉ ተረድቶ ፣ እውነተኛ ፣ ያልተወናበደና ያልተጭበረበረ ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽግግር መድረክ እንዲፈጥር ለአገሪቱ ፖለቲካ ፖርቲዎች የሚጠቅም ሃሳብ በማዋጣት ሽግግሩን አመርቂ  አድርጓል ወይ ?

አላደረገም ። እንደውም በተወሳሰበ መልኩ የወያኔ / ኢህአዴግን ሌጋሲ እያስቀጠለ ነው ። “አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ ! “የተሠኘው የቴዲ አፍሮ ዘፈን እየተደገመ ነው ። በበኩሌ አብይ መራሹ የብልፅግና ፓርቲ የኢፌዲሪ መከላከያ ና የፖሊሥ ሠራዊት  የሰው ሥብሥብ መሆኑንን የዘነጋ ይመሥለኛል ። ይኽ ዝንጋታ ደግሞ የንጉሡን ታሪክ መድገሙ አይቀርም ። ይኽ እንዳይሆን ነው ያለመሠልቸት ተው የሰው ስብሰቡ የአብይ መንግሥት ወደተነሣህበት መንገድ ተመለሥ እያልን ያሐመታከት የምንጮኸው ።

በእውነቱ ከጅምሩ ቀና ትብብር እስከ ጥግ ያደረጉለት የበዙ ነበሩ ። ከበሁለተኛ ዓመቱ ግን እየቀነሱ ፣ በሦሥተኛ ዐመቱ እየተመናመኑ በአራተኛ አመቱ እየጠፉ መጡ እንጂ ! ( አሁን በጥቅም ብቻ የተቀነበቡ ናቸው ደጋፊዎቹ  ፣ የመጠቃቀም ከሆነ ነገሩ ና ጫወታው ኢህአዴግ ለሚጠቀምባቸው ፣ መሬትና ቤት ሲሰጥ እንደነበር እናውቃለን ። ይሁን እንጂ ሰዎች ኸህሊና ጋር የተፈጠሩ ናቸውና ሁሌም ከግፈኞች ጋር መቆምንም አይሹም ።

እነዚህ ከለውጡ ጎን ያሉ ጥቂት  ግለሰቦች ፣ ዕድሜ ከሠጠን ፣ ልክ እንደ ጥቂቶቹ ተሳዳቢ ዩቲውበረኞች ሲሆኑ ልናይ እንችላለን ። ዛሬ ፣ ዛሬ ፣    ጥቂት  ማህበራዊ አንቂዎች ፣ በበዛ ቅዠት ውስጥ ገብተው እና ሰው መሆናቸውን ዘንግተው ፤ “ ከአሻጋሪነት ወደ መሪነት የተቀየረውን መንግሥት “ ፣  በቀና ሂስ ከማረቅ ይልቅ በውዳሴ ከንቱ ከመንገዱ  ሲወጣ ፣ ዝም ብለው ሲያዩ ከርመው ፤  ዛሬ አላሥፈላጊ ዝርጠጣ ውሥጥ ገብተዋል ።

ከሁሉ የሚገርመኝ የአንዳንድ የቀድሞ የኢህአዴግ አባላት  “ ፖለቲካል   አክሮባት “ ነው ። የትላንት ሤጣንነታቸውን እንደው  እንደዋዛ የምንረሣላቸው መሥሏቸው “ ከእኛ ወዲያ ለአገር ተቆርቋሪ ፖለቲከኛ የለም ። “ እያሉ ያደነቁሩናል ።

እጅግ የበዛ ቅዠት   የሠፈረባቸው  ። ውሸቱን እና ሐሰቱን በመደበላለቅ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይበቀል ባይ ዩቲዩበሮችንም እያሥተዋልን ነው ። እነዚህ በጠባብ ብሔርተኝነት ፕሮፖጋንዳ አገሪቱን የመሥቀል ዳመራ ለማድረግ ዘወትር ሣይታክቱ የሚደክሙ ፣   ለአንደበታቸው ሉጋም አጥተውለት በተራ ስድብ የአገር መጠሪያ የሀነውን መንግሥት  በየዕለቱ የሚያዋርዱ እና የመንግሥት ከፍተኛ ሹማምንቶች ሚዛናቸውን እንዲያጡ በሥነ ልቡና ጦርነት  የሚያሥገድዷቸው በእውነቱ ሰውና የጨዋ ህዝብ ዓባልነታቸውን የዘነጉ ናቸውና በእጅጉ አዝኜባቸዋለሁ ። እንዲህ ሥል እንደሚሰድቡኝ አቃለሁ ። በበኩሌ ድንቡሎ ከማንም ተቀብዬ አላውቅም    ፡፡ በበኩሌ ግን ፣ እነዚህ ትችትን ና ሂስን ከ  ሥድብ ጋር የሚደባልቁ ግለሰቦች ፣ ሰው መሆናቸውን በውል የተገነዘቡ የአገራችን ዜጎች ፣ የሚጠሉትን የማይበጀንን  ጠባብ ብሔርትኝነት በበለጠ ለማፅናት የሚጥሩ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ፡፡ ከሰውነት ተራ ወጥተው እጅግ ጠበው እና  ቀውሰው ንቃተ ህሊናው ዝቅተኛ የሆነውን ዜጋ በብሔርተኝነት ሥም  ሲያሳብዱት እየታዘብኩ ነው  ፡፡ በበኩሌ ሰው እንጂ በቋንቋ የሚጠራ ህዝብ ከ6000 ዓመት በፊት አልነበረም ። የቋንቋ ሰውነት ከአምሥተኛው ክ/ዘ በኋላ አቆጥቁጦ በ18ኛውና በአሥራ ዘጠነኛው ክ /ዘ በተለይም በአፍሪካ  በፖለቲካ ሰበብ የተዘራ የቅኝ ገዢዎች የማሥገበሪያ ረቂቅ መሣሪያ ነው ።

ይኽንን እውነት የካዱ አንዳንድ ተመልካቸ ብዙ  ዩቲይበሮች በቋንቋ ሲሳደቡ ፣የሥድባቸው ብዛት ” ስድ አደግ  ወይም ጨዋ ወላጅ አሰዳቢ ” እንጂ ሌላ ስያሜ  የሚሰጣቸው ሆኖ አላገኘሁትም ፡፡ ጠቅላላ  ድርጊታቸው የሚያንፅ ሳይሆን የሚያፈርስ ነው ፡፡  እንዲህ አይነቶቹን ግልብ ሥሜት ያላቸውን ግለሰቦች ፤ የኢትዮጵያ እንቁ ልጅ ፤ ጸጋዬ ገብረመድህን ፣ እንዲህ በማለት ከዚህ እኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ይመክራቸዋል።

ከጥቅሱ በፊት ፤

በእውነቱ የአንድ ባለአእምሮ ግለሰብን ወይም መሪን መሻት ለማወቅ እጅግ መቅረብ አሥፈላጊ ነው ። በሩቁ መቃወምም ሆነ እጅግ የተጋነነ ፍቅርን መግለፅ ለግለሰቡ አይጠቅመውም ። ሥድብ እና ገፅታ ሜበላሸትም መሪውን ብቻ ሣይሆን አገርን እንደሚጎዳ መታወቅ አለበት ። እንዲህም ሥል በነፃነት ሃሳባቸውን ፣ ሂሥም ሆነ ትችትን የሚሰነዝሩ ዜጎችን  በአሣፋሪ መልኩ መንገዴ ፍቅርና መደመር ነው  ብሎ በተናገረ  መሪ ባለበት አገር ውሥጥ ማሠር መወገዝ የለበትም እያልኩ አይደለም ። የጋዜጠኞቹና የማህበራዊ አንቂዎቹ መታሠር እጅግ አሣፋሪ ከመሆኑም በላይ የአገሪቱን ጠ/ሚ ሥም በእጅጉ የሚያጠለሽ ነው ። በግል ጋዜጠኞቹ እንዲታሠሩ ትዕዛዝ ሠጥተዋል ብሎ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም  ሥህተቱ በአሥቸኮይ እንዲታረም ከመርሃቸው አኳያ ማድረግ እንደነበረባቸው ይኽ ፀሐፊ ያምናል ። ለድርድሩ ብሎ ነው ያሠራቸው የሚባለውን አሉባልታ አልቀበለውም ። ህዝብን አይንህን ጨፍንና ላሞኝህ ማለት እንዴት ይቻላል ። በ1967 ዐ/ም ፤ በ1983 ዓ/ም እና 2010 ዓ/ም እንዳልተቻለ ታይቷል ። ነገም የህዝብን አይን መሥጨፈንና ሥልጣንን ዘላለማዊ ማድረግ ከቶም አይቻልም ።

ጥቅሱ

” በማንኛውም ቡድንም ሆነ ግለሰብ ባህሪ ውሥጥ የኢትዮጵያዊነት የባህል ብቃት ና የመንፈስ ኩራት ያለውን   ቡድን  ወይም ግለሰብ ፣ በነገር ቀደም ተከታትሎ ፣ መልከፍ ና ማሥለከፍ ፣ በመሠሪ መውጋትና ማስቆጣት ፣ ወደሥህተት መግፋትና ማዘናጋት  ፣ ብሎም ማዋረድና ዋጋ ማሳጣት ፣ ሁልጊዜም በተከታታይና ያለመሰልቸት የሚደጋገም የጥፋት ዓላማ ነው። …”

ሎሬት ባለቅኔ ፣ፀሐፊ ተውኔት ፣የቋንቋ ተመራማሪና ሊቅ ፀጋዬ ገብረመድህን

ይህ ለአገርና ለህዝብ ደንታ ቢሥ የሆነ አውዳሚ አሥተሳሰብ ነው። ማንም ግለሰብ ሆነ ቡድን የማጥፋት ኃይል እንዳለው ከላይ የጠቀሥኳቸው ፈላሥፎች ከረዢም ዓመት በፊት በሚሥብ ቋንቋ አሳውቀውናል ።  መጠፋፋት ለማንም አይበጅም ።  ዛሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያሥፈልገው ፍቅር ነው። አንድነት ነው ።  ህብረት ነው ።  የእገሌ ዘር ፣ የእገሌ ክልል እየተባባሉ  ዝም ብሎ በጸጥታ ለመብላት እኮ ዜጎች  መንግሥት አያስፈልጋቸውም ። ለመብላት ብቻ ለመኖር ብዛ ቢል እረኛ ብቻ ነው የሚያሥፈልገው ።   እረኛ ብቻ እንዲኖር ደግሞ ከተፈለገ ፖርቲዎችን በጉልበት ማጥፋት በቂ ነው።   ያን ጊዜ በብትሩ ሃይ እያለ ለሆድ ብቻ የሚያኖር መንግሥት መፍጠር ይቻላል ።

የግለሰብ ሥብሥብ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ  ለመብለት ብቻ ለመኖር ፣  በሴራ ና በጡንቻ ብቻ ተጠቅሞ ለመበልፀግ ለሚፈልገው  በር ለመክፈት   ከመቸውም ጊዜ ይልቅ ዛሬ ዝግጁ እንዳልሆነ ገዢው ፓርቲም ሆነ ተቃዋሚ ( ለመንግስት ስልጣን ተወዳዳሪ ፓርቲዎች )  በውል ቢገነዘቡ መልካም ነው ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop