ሳናውቅህ ሙሴ ብለንሀል፡፡ ፎቶህን በቲሸርት አሰርተን ለብሰናል፡፤ደግፈንህም ቆመናል፡፡አሁን አወቅንህ፡፡ ተራ አታላይ ብቻ ሳትሆን እውቀትም ችሎታም የለህም፡ ይህንን የዋህ ህዝብና ይህችን ታላቅ ጥንታዊት አገር ቁማር ተጫወትክባቸው፡፤
በተለይ በኦሮሙማ ታውረህና በአማራ ጠልነት ሰክረህ ከአማራ ጠላቶች ጋር አብረህ አማራውን በየአቅጣጫው አስጨረስከው፡፡ በህይወት የተረፈውንም እንዳያንሰራራ አደረግሀው ፤ በኩሩው ኢትዮጵያዊ በአፋር ህዝብም ላይ እንደሁ አደረግህ፡፤ በትግራይም በወያኔ ሰበብ ህዝቡ ፍዳውን እንዲያይ አደረግከው፡፡ በብዙ መቶ ሽህ የሚቆጠሩ የትግራይ ወጣቶችም እብሪተኛው ወያኔ ለከፈተው ጦርነት ጦስ አስደረግካቸው፡፤ በአጠቃላይ ይህንን ሁሉ ማስቆም በምትችልበት ቦታ ላይ አላግባብና ያለችሎታህ ተኮፍሰህና ሴራ እየጎነጎንክ ለህዝቡ ስደትን.መከራን. ድህነትን. በሽታን. ስቃይን. ሞትንና.እልቂትን ደግስክለት፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆንና የህዝቡ ሰቆቃና የግፉ ጽዋ ሞልቶ መፍሰስ ለአንተ ምንም ማለት አልነበረም፡፡ አሁንም ምንም ማለት እንዳልሆነ በይፋ ወጥተህ ደሰኮርክ፡፡ አቅራራህ፡፡ ቢገባህ ኖሮ በስራህ ባፈርክ ነበር፡
ይህ ሁሉ ሳይበቃህም እንደገና አሁን ላይ ደግሞ በስሌት ከወያኔ ጋር አዲስ ሽርክና ፈጥረህና አማራን ለማጥፋት ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆነህ በአማራው ላይ አለም አቀፍ ዘመቻ ከፈትክበት፡፡ በወለጋና በቤንሻንጉል፣ በሰሜንና በምእራብ ሸዋ አማራን በኦንግ ጦርና በመንግስት ሀላፊወች ጭምር አማራን የማጽዳቱ ስራ በተለይም በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ አማራን ነቅሎ ኦሮሞን የመትከሉ ተንኮልና ድብቅ ሴራ የማይታወቅ እንዳይመስልህ፡ አመንክም አላመንክም እነዚህ ሁሉ የክህደት ሴራወችህ ነቄ ተብለዋል፡፡
በከንቱ ትባዝናለህ እንጅ አገሪቱን ሆን ብለህ እንደዚህ አፈራርሰህ ሰላም አግኝቶ እንዲኖር የምትመኝለት የኦሮሙማ ስሌት ግቡን አይመታም፡፡ አይሳካም፡፡ አገሪቱም የማንም ሳትሆን ትቀራለች፡፡ አንተም ፍርድህን አግኝተህ በታሪክ አተላነት ትታወሳለህ፡፡