ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY)
የብልፅግና ፓርቲ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመሬት ርስት ፓርኮቹ ናቸው፤ አብይ አህመድ በፓርክ ስም መሬቶች ማግበስበስ ከጀመረ አራት አመታት ተቆጥሮል፡፡ ከመሬት ቅርምት (Land Grab) ወደ ፓርኮች ቅርምት (Park Grab) ተዘዋውረናል፡፡ “The landed elite in most developing countries find their power and status in society linked to the ownership of land, which is the main source of wealth.” በብዙ ታዳጊ አገራቶች የመሬት ባላባት ልሂቃን በትረ ሥልጣናቸውን የሚጨብጡት በመሬት ኃብትን በቁጥጥራቸው ስር በማድረግ ነው፡፡ ህወሓት ኢህአዴግና ኦዴፓ ብልፅግና የመሬት ፖሊሲያቸው አንድ ዓይነት ነው፡፡ መሬት የመንግሥት ነው፤ መሬት አይሸጥም አይለወጥም፡፡ በመቃብራችን ላይ!!! አራት ነጥብ፡፡ “Public ownership 1/1995), it decided to keep all rural and urban land under public ownership. According to the Federal Democratic Republic of Ethiopia Constitution (hereafter cited as FDRE Constitution), all urban and rural land is the property of the state and the Ethiopian people (Article 40(3) of the FDRE Constitution).”
አብይ አህመድ መሬት በፓርኮች ሥም፣ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባን መሬት በሜትር ካሬ ሶስት መቶ ሽህ ብር ….አራት መቶ ሽህ ብር የሚያወጣ የመሬት ኃብትን በመቆጣጠር፣ ኢንጂነር ተሃከለ ኡማ የሃገሪቱን መዕድን ሃብት በመቆጣጠር ኢትዮጵያና ህዝቧን እግር ከወርች አስረው በተረኛነትና በዘረኛነት በደም መሬት ወደ ኦሮሙማ እያሸጋገሩን ነው፡፡
ከአብይ አህመድ ፓርኮች የግንባታ ወጪዎች ውስጥ፡-አንድነት ፓርክ 5 (አምስት) ቢሊዮን ብር፣ እንጦጦ ፓርክ 2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ብር፣ አደዋ ዜሮ ኪሎሜትር ፓርክ 4.6 (አራት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ብር፣ መስቀል አደባባይ 2.6 (ሁለት ነጥብ ስድስት)ቢሊዮን ብር፣ ወዳጅነት ፓርክ 2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት ) ቢሊዮን ብር፣ ቢተወድድ ጎሹ ወለወደፃዲቅ ፓርክ 101 (መቶ አንድ) ሚሊዮን ብር፣ አንባሳደር ፓርክ 49 (አርባ ዘጠን) ሚሊዮን ብር፣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እድሳት 2.2 (ሁለት ነጥብ ሁለት) ቢሊዮን ብር ተገንብተዋል፡፡ በተመሳሳይ የወንጪ፣ጎርጎራና ኮይሻ ፓርኮች በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡
ጦርነትና ልማት፣ ጦርነትና ብልፅግና በየፈርጁ የምታስተናግድ እናት አገር፡፡ በኢትዮጵያ ጦርነት ንግድ ሆኖል፣ በጦርነት ውስጥ ከፍተኛ ንግድ አለ፡፡ በትግራይ ክልል ውስጥ ህዝቡ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶል፣ ሆኖም በድንበር ንግድ አምስት ሊትር ዘይት 2200 ብር ይሸጣል፣ አንድ ኪሎ በርበሬ 800 ብር፣ አንድ ኪሎ ጨው 200 ብር፣ አንደ ኩንታል ጤፍ 7500፣ ሃያ አምስት ሊትር ቤንዚን አስር ሽህ ብር (አንድ ሊትር ነዳጅ ከ300 እስከ 400 ብር ይሸጣል)፣ አንድ ክላሽን ኮቭ ጠመንጃ መቶ ሽህ አራት መቶ ብር ይሸጣል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ከየሜዳው የተለቀመ አስር ክላሽን ኮቭ አንድ ሚሊዮን ብር በላይ በደራው ጦርነት ገበያ ላይ ተቸብችቦል፡፡ በጦርነቱ ብዙ ሚሊየነሮች ተፈልፍለዋል፣ የደም ገንዘብ በሶርያ፣ በየመን፣ በሶማሌ፣ በሊቢያ ጦርነት ወቅት የሆነው እንዴ ነው እንዲው እንደዘበት አገር አንዴ ከፈረሰ መልሶ ለማቆም ዘበት ሆኖል፡፡
የብልፅግና ህወኃት የማይቌጨው የጦርነት ንግድና የዋጋ ንረት የኢትዮጵያን ህዝብ በእንፉቅቁ እንዲሄድ አድርጎታል፡፡ ለብልፅግናና ህወሓት ካድሬዎች የጦርነት ኢኮኖሚ ተመችቶቸዋል፣ የጫካ ምጣኔ ኃብት ህግ ምንም ይሁን ምን፣ አንበሣና ካድሬ በፍፁም ሳር አይበሉም!!! በኢትዮጵያ ሁለት አመት ሊሞላው ወራቶች የቀረው የማይቌጨው የጦር አበጋዞች የጦርነት ንግድና የ2.5 (ሁለት ነጥብ አምስት) ቢሊዮን ዶላር የመሠረተ-ልማት ውድመት አስከትሎል፡፡ ናሙና መረጃዎች በማቅረብ ጥናቱን ቀጥለን እናቀርባለን፡፡
{1} የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዶክተር ይናገር ደሴ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት ቅርንጫፍ ባንኮች ተዘርፈዋል፡፡ ከደሴ ንግድ ባንክ ብቻ ስድስት ቢሊዮን ብር ተዘርፎል፡፡ ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የዘረፉት ገንዘብ በሃገሪቱ የባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረሱ የጥሬ ገንዘብ ችግር በባንኮች ውስጥ እንደተከሰተ ደንበኞች እማኝነታቸውን ይሰጣሉ፡፡ የባንኩ ገዥ ይናገር ደሴ ስለተዘረፉት ባንኮች አንድም ቀን ለህዝብ ገልፆ አያውቅም፡፡ በወያኔና ኦነግ የተዘረፉ ባንኮችን ሳይቀንሱ ‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን የባንክ ገበያ የአንበሳውን ድርሻ ይዞ በመጎዝ ላይ ሲሆን፣በተጠናቀቀው የ2013 ዓ/ም ሙሉ የሒሳብ አመት ከታክስና ከሌሎች ተቀናሾች በፊት 20.3 (ሃያ ነጥብ ሦስት) ቢሊዮን ብር አትርፎ እንደነበር አይዘነጋም፡፡››…….‹‹የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2014 ዓ/ም የመጀመሪያው ሩብ አመት አገኛለሁ በሎ ካቀደው ገቢ ከ10 (አሥር) ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ገቢ ማግኘቱንና የትርፍ ምጣኔውንም ከዕጥፍ በላይ ማሳደጉ ገልፆል፡፡››………(1)
የኢትዮያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ሀብት ከ1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡ የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቢ ሳኖ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ የባንኩ ሀብት ከ1.1 ትሪሊዮን ብር በላይ የደረሰው የ2013 በጀት ዓመት መጣናቀቂያ ድረስ መሆኑን ተናገረዋል፡፡ እንደ ፕሬዝደንቱ ገለፃ፣ የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን የጠቆሙት አቶ አቢ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የክልል የጸጥታ ኃይሎች ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የሃገርን ህልውና ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ተጋድሎ ለመደገፍና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች፣ ባንኩ 300 ሚሊዮን ብርና ሠራተኛው 500 ሚሊዮን ብር በድምሩ 800 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቢ ሳኖ በሃገሪቱ ምንም ጦርነት የሌለ ይመስል ስለተዘረፉት ባንኮች ዝም ብለዋል………(2)
በሁለቱ የጦር አበጋዞች ፍልሚያ የአብይና ደብረፂዎን የሥልጣን ሽሚያ የተነሳ ላለፈው ሁለት አመታት በትግራይ ክልል ውስጥ መቶ በላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ባንኮች ተዘግተዋል፡፡ ሁለት ሚሊዮን የባንክ ደንበኞች ነበሯቸው፡፡ የጦርነቱ ሰለባ የሆነው ህዝብ በገንዘቡ ገዝቶ መጠቀም ባለመቻሉ ለችግር ተዳርጎል፡፡ የባንኩ ፕሬዝደንት ይናገር ደሴና አቶ አቢ ሳኖ ስለ ትግራይ ባንኮች ትንፍም ብለው አያውቁ፡፡ በአንፃሩ ከዘመድ ጋር ስልክ ግንኙነት በማስደረግ የገንዘብ ዝውውር ንግድ በድንበር አካበቢ ደርቶ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በግል ባንኮች የከፈቷቸውን የባንክ ሂሳቦች እንዲዘጉ ታዘዋል ትዕዛዙን ያልፈፀ መሥሪያ ቤቶች በጀት አይለቀቅቸውም ተብሎል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካዝናዎቸ በገንዘብ እጦት ድርቀት ተመተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የባንክ ፋይናንሻል ዘርፍ ውድቀት በተፈለፈሉት የዘር ባንኮች እየፈጠነ ወደ ግብዓተ መሬቱ መስረጉ አይቀሬ መሆኑን የባንክ ባለሙያዎች ተንብየዋል፡፡
{2} የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ዘመን፡- {1} ህወሓት የዘረፈው ሰማንያ ስድት ታንኮች (Tanks ) ሲሆኑ ከዚህ ውሰጥ ሃያ ዘጠኙ T-55: ሲሆኑ አንዱ ደግሞ T-55(A)MV: ሠላሳ ሦስቱ ደግሞ T-62: ሃያ ሁለቱ T-72B: አንዱ T-72UA1:መሆናቸው ታውቆል፡፡ {2} ህወሓት አንድ አርሞርድ ሪከቨሪ ቭኒክል (Armoured recovery vehicles ) አለው፡፡ {3} ህወሓት ሠላሣ አርሞርድ ፐርሶኔል ኬሪየርስ (Armoured personnel carriers ) ዘርፎል፡፡ ከዚህ ውስጥ ሃያ ስድስቱ Type 89A APC: ሲሆኑ፣ አራቱ WZ-551 APC:ደግሞ ናቸው፡፡ {4} ህወሓት ስልሣ አምስት ቶውድ አርቲለሪ (Towed artillery )ሲኖረው አንዱ 85mm D-44 divisional gun:፣ አርባ ስምንቱ 122mm D-30 howitzer 2A18: ሲሀኑ፣ ዘጠኙ 130mm M-46 field-gun:ሲሆኑ ቀሪው ሰባቱ ደግሞ 155mm AH-1 howitzer: ዓይነት ናቸው፡፡{5} ህወሓት አስራስድስት መልቲፕል ሮኬት ላውንቸርስ (Multiple rocket launchers ) ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ ስድስቱ 107mm Type-63: ዓይነት፣ ስምንቱ 122mm BM-21 ‘Grad’:ዓይነት፣ አንዱ 300mm AR2:ዓይነት፣ ሲሆን ቀሪው አንድ ደግሞ 300mm A200/M20 TEL: ናቸው፡፡ {6} ህወሓት አንድ M20/A200 TEL: ባሊስቲክ ሚሳኤል ላውንቸር (Ballistic missile launcher) የዘረፈ ው ሲሆን በኖቨምበር 2020 በባህር ዳር ዓየር ማረፍያ ላይ አስወንጭፎ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡ M20/A200 TEL: (Used in the missile strike on Bahir Dar airbase in November 2020) {7} ህወሓት አራት ሮኬትና ሚሳኤል ሰፖርት ቬኒክል ( Rocket and Missile support vehicles ) ሲኖረው ከዚህ ውስጥ አንዱ AR2 loader: ሲሆን ሦስቱ ደግሞ M20/A200 loader: ናቸው፡ {8} ህወሓት አስራ ሁለት ማን ፖረብል ኤር ዲፊንስ ሲስተም (Man-Portable Air Defence Systems ) ሲዘርፍ ዓይነቱ 9K310 Igla-1: ነው፡፡ {9} ህወሓት ሃያ ሰባት ፀረ አይሮፕላን (Anti-aircraft guns (27) ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ ሃያ አንዱ 23mm ZU-23: ሲሆኑ ስድስቱ 37mm Type-65/74: {10} ህወሓት ከምድር ወደ ዓየር ተወንጫፊ ሚሳኤል (13 ላውንቸር በ 4 ሳይትስ) Surface-to-air missile systems (13 launchers in 4 sites) ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ አንዱ S-75 ”SA-2” site: ሲሆኑ ሦስቱ S-125 ”SA-3” sites: {11} ህወሓት ሰባት ራዳሮች (Radars ) ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ አንዱ P-18 ‘Spoon Rest D’: ፤ሁለቱ ST86U/36D6 ‘Tin Shield’: አንዱ SNR-75 ‘Fan Song’ (for S-75): ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ SNR-125 ‘Low Blow’ (for S-125): መሆናቸውን መረጃው ያሳያል፡፡ ……………(3)
{3} የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፡- የኤሌትሪክ መሠረተ ልማት፡- ጨለማ ቀለባቸው የሆኑት ወገናችን በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች ውስጥ የሚገኙ የከተማ ህዝብ በጨለማ ውስጥ መኖር ከጀመሩ አመት ሁለት አመት እየተቆጠረ ነው፡፡ ህወሓት የጨለማ ንጉስ ነው፣ ወያኔ የኤሌትሪክ መሠረተ ልማት የዘረፈ ኮንዳክተሮች እየበጠሰ፣ የኤሌክትሪክ ታወሮች እየጣለ፣ ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያ ነቅሎ አየወሰደ፣ የኦፕቲካል ግራውንድ ፋይበር እየበጣጠሰ፣ ተሸከርካሪ መኪኖች እየዘረፈ፣ መንግሥታዊ ተቆማትን እያፈረሰ ያለ የጦር አበጋዝ ነው፡፡ ህወሓት በአማራና አፋር ክልሎች በፈፀመው ወረራ 53.3 በመቶ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ተዘርፈዎል ወይ ወድመዋል፡፡ የኤሌትሪክ መሠረተ ልማቶች አጠቃላይ ኪሳራ 1.64 ቢሊዮን እንደሚደርስ ተገምቶል፡፡ የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦቱን ለመቀጠል 29.5 ሚሊዮን ብርና 23 ሚሊዮን ዶላር የማቴሪያል ወጪ ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት አሸባሪ ሓይል ከወልዲያ ከተማ ነቅለው የወሰዱት የተንቀሳቃሽ ኤሌትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ነው፡፡ ………………..(4)
{4} የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ፡- ‹‹የኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው የአገልግሎት መቆረጥ ኩባንያው ከ3.6 (ሦስት ነጥብ ስድስት) ቢሊዮን ብር በላይ ማጣቱን አስረድተው፣ ጉዳት የደረሰባቸው ንብረቶች ዋጋና መልሶ ግንባታ ለማከናወን የወጣ ወጪ ደግሞ ከ328 (ሦስት መቶ ሃያ ስምንት) ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ በጦርነቱ ሳቢያ በአጠቃላይ አራት ቢሊዮን ብር ኪሳራ ደርሶል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የቴሌኮሙኒኬሽን መስሪያ ቤት ያስገነባው የየቴሌኮሙኒኬሽን ማከፋፈያ ቌት መሠረተ ልማት አስራአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ እንዲሁም የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ቌት ትህነግ እንዳወደመው ታውቆል፡፡ በዚህም የተነሳ የትግራይ ህዝብ በጨለማ ውስጥ እንዲኖር በትህነግ የጦር አበጋዞች ተፈርዶበታል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ካሉት 8000 (ስምንት ሽህ) የሞባይል ጣቢያዎች ውስጥ በጦርነቱ ሳቢያ 3473 (ሦስት ሽህ አራት መቶ ሰባ ሦስት) ያህሉ አገልግሎት አቆርጠው እንደነበርና የደረሰው ጉዳት በኢትዮ ቴሌኮም አደረጃጀት መሠረት ካሉት 17 ሪጀኖች ውስጥ አሥሩ ላይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ አሳድሮል፡፡ በተጨማሪም 34 የሽያጭ ማዕከሎች ላይ ሙሉ ለሙሉና በከፊል ጉዳት መድረሱን የተገለፀ ሲሆን፣ በታወሮችና በፋይበሮች የጥገና ጣቢያዎችና ሌሎች ንብረቶች ላይ ስርቆትና ጉዳት መድረሱን ተገልፆል፡፡››
በአጠቃላይ በ320 የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና ከዚህ ውስጥ 62 በመቶው በክልሎች፣ 38 በመቶው ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተከሰተ መሆኑ ተገልፆል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት በትግራይ ክልል፣ በሰሜን ጎንደር፣ ሰሜን ወሎና ከፊል አፋር ተቆርጦል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በአፋር፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና ሌሎች ክልሎች ጨምሮ በመቶ ወረዳዎች አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን አስታውቆል፡፡
{5} የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በህወኃት አሸባሪ ድርጅት በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 100 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ለፓርላማ አባላት ገልፀዋል፡፡ ከወደሙት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1200 ትምህርት ቤቶች በጦርነትና በሌሎች ምክንያት የወደሙ፣ 5000 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ ሶሰት ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፣ መቶ ሃምሳ ሽህ መምህራን ከመማር ማስተማር አገልግሎት ውጪ ሆነዋል፣ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች በከፊልና በሙሉ ወድመዋል በማለት የደረሰውን ጉዳት ገልጸዋል፡፡ በአማራ ክልል ብዙ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ብዙ 11.6 ሚሊዮን ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ ዜጎች ሆነዋል፡፡ ‹‹በትግራይ፣ በአማራና አፋር ክልሎች በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ከሰባት ሽህ በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉና አንዳንዶች ደግሞ በከፊል መውደማቸውን የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ አስታውቀዋል፡፡ በጦርነቱ ሳቢያ በትግራይ ክልል ከ 1.4 (አንድ አጥብ አራት) ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችንና ከ48000 (አርባ ስምንት) ሽህ በላይ መምህራን ከትምህርት ሥርዓት ውጪ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ጨምረውም በአንድ ወር ብቻ በአፋር ክልል 88000 (ሰማንያ ስምንት ሽህ) ተማሪዎች ይማሩባቸው የነበሩ 455 ትምህርት ቤቶች በአማፂው የህወሓት ኃይሎች መውደማቸውን እንደተናገሩ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ በተመሳሳይ በአማራ ክልል ውስጥ 140 ትምህርት ቤቶችና ሁለት የመምህራን ማሰልጠኛና ኮሌጆች ሙሉ በሙሉና በከፊል ለውድመት መዳረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ በሦስቱም ክልሎች የሚገኙ ከ1.42 (አንድ ነጥብ አርባ ሁለት) ሚሊዮን ተማሪዎች በተለያዩ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጪ ለመሆን ይገደዳሉ ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡ በዚህም በጦርነትቱ ሳቢያ በትግራይ ክልል ውስጥ ከተፈናቀሉትና ለችግር ከተጋለጡት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተጨማሪ በአፋርና በአማራ ክልል ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተናግረዋል፡፡››……….{5}
በሌላ በኩል የብአዴን/አዴፓ ብልጽግና ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች 60 ሚሊዮን ብር ተከፋፍለው ለመጥፋት በዝግጅት ላይ እንደነበሩና መቶ ሚሊዮን ብር እንደተዘረፈ ተገልፆል፡፡
{6} የጤና ሚኒስትሮ ዶክተር ሊያ ታደሰ በአማራና በአፋር ክልሎች ለተዘረፉና ለወደሙ 36 ቢሊዮን ብር መልሶ ለማቆቆም እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል በህወኃት የተዘረፉ የጤና ተቆማት ተፈታትተው የተዘረፉ የህክምና መሣሪያዎችና የላብራቶሪ እቃዎች ግምት 36 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ታውቆል፡፡ በአፍር ክልል እስከ አምስት መቶ ሽህ ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅሎ ይገኛል፡፡
{7} የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ዳግማዊት ሞገስ፡-ህወሓት በትራንስፖርት መሠረተ-ልማቶች ላይ በአማራና አፋር ክልሎች ውስጥ 1.75 (አንድ ነጥብ ሰባ አምስት) ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ውድመት ማድረሱ ተገልፆል፡፡ ህወሓትና ኦነግ ሸኔ ከአማራና አፋር ክልሎች ብዙ መኪኖች ፣ ባጃጆች፣ የኮንስትራክሽን ገልባጭ መኪኖች፣ ሎቤዶች፣ ሮሎዎች፣ ትራክተሮች ወዘተ እንደዘረፉ በማስረጃ ተሠንዶል፡፡
{8} የአማራ ክልላዊ መንግሥት መረጃ መሠረት በአማራ ክልል 380 (ሦስት መቶ ሰማንያ) ቢሊዮን ብር ንብረት መዘረፉንና መውደሙን ዳግም ለመገንባትም ብዙ አመታት እንደሚፈጅ በተደጋጋሚ አሳስበው ከፌዴራል መንግሥቱ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ የአማራ ክልላዊ መንግሥት ባለሥልጣናት በጦርነቱ ወቅት ቤተሰባቸውን ይዘው ለመሸሽ 60 (ስልሣ) ሚሊዮን ብር ተከፋፍለው ለመሸሽ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ በመረጃ ተረጋግጦል፡፡ በተጨማሪም መቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት በመጋዘን የተከማቸ የሰሊጥ ምርት ሸጠው እንደተከፋፈሉ መረጃው ጠቁሞል፡፡ በኦነግ ሸኔ በሁሩ ጉድሩና በምስራቅ ወለጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2563፣ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር 68፣ የተዘረፉ የቀንድ ከብቶች 145000፣ የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያኖች 68፣ የተቃጠሉ መስጊዶች 46፣ የተቃጠሉ ወፍጮዎች 84፣ የተቃጠሉና የተዘረፉ መኪኖች 18 መሆናቸው ተገልጾል፡፡ የህወሓትና ኦነግ ሸኔ ዘረፋና የመሠረተ-ልማቶች ውድመት ከፌዴራልና ክልሎች ጋር የተቀነባበረ ሴራ እንደሆነ ከፍተኛ ጥርጣሬና ማስረጃ እንዳለ ይታመናል፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጰያና ህዝቧን ይጠብቅ!!!
ምንጭ
(1) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትርፍ ምጣኔ ከዕጥፍ በላይ ማደጉ ተገለፀ/ሪፖርተር ጋዜጣ 14 ኖቨንበር 2021
(2) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሃብት 1.1 ትሪሊዮን ደረሰ/29 ኦግስት 2021
(3)The Tigray Defence Forces – Documenting Its Heavy Weaponry/ Oryx Wednesday, September 01, 2021 Ethiopia , By Stijn Mitzer and Joost Oliemans
(4) ሪፖርተር ጋዜጣ
(5) ኢትዮ ቴሌኮም በጦርነቱ ሳቢያ በሦስት ወራት 1.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማጣቱ ታወቀ/ሪፖርተር ጋዜጣ 14 November 2021