April 9, 2022
7 mins read

የአምንስቲ የወልቃይት ዘገባ፤ አሁን ለምን?

ምዕራባውያን ቅኝናፋቂወች (neocolonialists) በተለየም ደግሞ እንግሊዞች የአማራ ሕዝብ መሠረታዊና ዘላለማዊ ጠላቶች የመሆናቸውን ጉልህ ሐቅ የአማራ ሕዝብ እያነቀውም ቢሆን ውጦ፣ ከነዚህ ፀራማራ ምዕራባውያን የሚመነጭን ማናቸውንም ነገር በዚህ ሐቅ መሠረት ማስተናገድ አለበት፡፡  ዋና መሠረቱ እንግሊዝ ላይ የሆነው (በሰበአዊ መብት ሰበብ የምዕራባውያን ቅኝናፋቂወችን አጀንዳወች ለማራመድ የተቋቋመው) አምንስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty Internatioal) የሚባለው የቅኝናፋቂወች ድርጅት በወልቃይት ላይ ያቀረበው ፀራማራ ዘገባም ሌላ ምንም ሳይሆን የዚህ ጉልህ ሐቅ ጉልህ ነጸብራቅ ነው፡፡

ከአድዋ ድል በኋላ የምዐራባውያን ዋና ዓላማ ነጭን ነጫጭባ የሚሉትን፣ በማንነታቸው የሚኮሩትን አማሮችን ከኢትዮጵያ የፖለቲካ ጨዋታ ሙሉ በሙሉ በማስወጣት፣ ለነጭ የማጎብደድ ዝንባሌ በተጸናወታቸው የትግሬና የኦሮሞ ጎጠኛ ሎሌወቻቸው አማካኝነት አገሪቱን በበላይነት መቆጣጠር ነው፡፡  አሁን ላይ ደግሞ ወያኔ በአማራ ሕዝብ ላይ ይፈጽመው የነበረውን ዘርተኮር ጭፍጨፋ ከማስቀጠል አልፎ እጅግ የከፋ ባደረገው በኦነጋዊ ሎሌያቸው በዐብይ አሕመድ አማካኝነት ዘመናት ያስቆጠረውን ፀራማራ ዓላማቸውን ለማሳካት ከጫፍ ላይ ደርሰዋል፡፡  ስለዚህም (ቢያንስ ቢያንስ ፀራማራ ዓላማቸውን ባሽከራቸው በዐብይ አሕመድ ጉዳይ ፈጻሚነት ሙሉ በሙሉ እስከሚያሳኩ ድረስ) አማሮች ለዐብይ አሕመድ ፀራማራ መንግስት ሥጋት እንዳይሆኑ ለማድረግ የማይፈነቅሉት ዲንጋይ፣ የማይፈጥሩት ትርክት የለም፡፡

አማሮች የዐብይ አሕመድን ኦነጋዊ ፀራማራ መንግስት እንዳይገዳደሩ ለማድረግ ከሚጠቀሙባቸው ዘዴወች ውስጥ አንዱና ዋናው ደግሞ የወያኔ ተዋናዮችን ቀጥረው የዘር ጭፍጨፋ ተውኔት በመተወን፣ ተጨፍጫፊወቹን አማሮች በጨፍጫፊነት እየሳሉ ማሸማቀቅና፣ በጦር ወንጀለኝነት ትጠየቃላችሁ እያሉ ማስፈራራት ነው፡፡  አምንስቲ ኢንተርናሽናል በየጊዜው የሚዘግባቸው ዘገባወች፣ የአሜሪቃ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በየጊዜው የሚያወጣቸው ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መግለጫወች፣ እንዲሁም ቢቢሲ (BBC) እና ሲኤንኤን (CNN) ሳያሰልሱ የሚነዟቸው “ትግሬወች ባማሮች ተጨፈጨፉ” እያሉ ያዞ እንባ የሚያነቡባቸው አጭቤ ዜናወች (fake news) ዓላማቸው አንድና አንድ ሲሆን፣ እሱም አማሮችን በጦር ወንጀለኝነት በማሸማቀቅና በማስፈራራት የዐብይ አሕመድን ፀራማራ መንግስት እንዳይገረስሱት ማድረግ ነው፡፡  ለዚህ ማስረጃው ደግሞ እነዚህ ዘገባወቸ፣ መግለጫወችና አጭቤ ዜናወች ሁልጊዜም ሆነ ብለው የሚለቀቁት አማሮች ሆ ብለው ለመነሳት ፍንጭ ባሳዩ ቁጥር መሆኑ ነው፡፡

ለምሳሌ ያህል አምንስቲ ኢንተርናሽናል የአማራን ሕዝባዊ ሠራዊት (ፋኖ) “ትግሬ ጨፍጫፊ” በማለት የከሰሰበትን አጭቤ ዘገባውን (fake report) የለቀቀው፣ ይሄው የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት የዐብይ አሕመድን ወራሪ የኦነግ ሠራዊት ሚንጃር ላይ ድባቅ በመታው በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው፡፡  የዚህ የአምንስቲ መግለጫ ዋና ዓላማ ግን ባሜሪቃ መንግሥት አደራዳሪነት ዐብይ አሕመድና ደብረጺዮን የአማራን ክልል ለመቀራመት (scramble) የተስማሙትን በቅርብ ቅን ይፋ የሚሆን ስምምነት፣ በትግሬ ጨፍጫፊነት ተከሶ አንገቱን እንዲደፋ የተደረገው የአማራ ሕዝብ ያለ ምንም ማቅማማት አሚን ብሎ እንዲቀበል ማድረግ ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር የአምንስቲ መግለጫ አሁን ላይ የተለቀቀበት ዓላማ አንድና አንድ ሲሆን እሱም የወያኔና የኦነግ ስምምነት በቅርቡ ይፋ ሲደረግ የአማራ ሕዝብ መቃወም ቀርቶ እንዳያጉረመርም ለማድረግ ነው፡፡

ረዥም ዘመን ካስቆጠረው ፀራማራ አጀንዳቸው በተጨማሪ፣ አማሮች የሩሲያን ባንዲራ ይዘው አድዋን ማክበራቸው፣ አማረኛ ጥርት አድርገው የሚናገሩት የሩሲያ አምባሳደር የአማራን ክልል መጎብኘታቸውና ፋኖወች ባጠቃላይ የአፍሪቃ በተለይም ደግሞ ያገራቸው የጦበያ ዘላለማዊ ጠላት የሆኑትን ምዕራባውያንን ከሩሲያ ጎን ሁነው ለመዋጋት የሚዘምቱበት ዕድል ሊፈጠር የመቻሉ ጉዳይ ምዕራባውያንን ከማስቆጣት አልፎ አብግኗቸዋል፡፡  በዚህም ምክኒያት ሰርብያ (Serbia) እና ሰርቦች ላይ እንዳደረጉት በአማራ ክልልና በአማሮች ላይ የቦንብ ዶፍ ለማውረድ ቋምጠዋል፡፡  አምንስቲ ኢንተርናሽናልና መሰሎቹ እያደረጉ ያሉት ለዚህ ከኔቶ ጀቶች ለሚወርድ የቦንብ ዶፍ የዘር ጭፍጨፋ ሰበቦችን መፍጠር ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop