March 27, 2022
7 mins read

HR6600 ፤ የ666 ተግበርን ከሳች ነውና መተግበር የለበትም ። መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊሰ

hr 6600 የአሜሪካ መንግሥት  HR 6600 የሚባል ኒኩለር በአገር ና በህዝብ ላይ ሊወረውር ተዘጋጅቶል ። የኢትዮጵያ ህዝብ ምን በድሎት ሊያጠፋው እንደተነሳ ግን የሚታወቅ ነገር የለም ።    በዚህ ሚሊዮኖችን በችግር ና በችጋር የሚጨርስ ፤ በሺ ማዕቀብ የተሞላ የ666 ቦንብ ይኽንን የእግዜር ፍጡር የአሜሪካ መንግሥት ለማጥፋት መነሳቱ በምን ሰበብ እንደሆነም ግልፅ አይደለም ።

የአሜሪካ መንግሥት የቆመው ለአሜሪካ ቱጃሮች በመሆኑ ለእነሱ ብዝበዛ ሲባል የአፍሪካን ህዝብ በድህነት በበሽታ  አማቆ መጨረስ ግቡ እሥካልሆነ ጊዜ ድረሥ ይኽን የመሠለ አረመኒያዊና ኢ ፍትሐዊ ፣ ኢ ዴሞክራሲያዊ ተግባር ለመፈፀም ባልተነሳሳ ነበር   ። ለአንድ ፐርሰንቱ ቱጃር አግበሥባሽነት ሲል  ኢትዮጵያን ከህዝቦ ውጪ እንጂ እሥከ ህዝቦ አልፈለጋትም ።  ዩክሬንን ከነ ህዝቦ እንደማይፈልጋት  ሁሉ ማለት ነው ። ዛሬም ሆነ ትላንት አሜሪካ በከፋ መልኩ ያልተሳተፈችበት ጦርነት በዓለም የለም ። …

በነገራችን ላይ ፣ ዩኩሬንን ከነህዝቧ ቢመለከት ኖሮ ፣ ዩክሬን ከነሙሉ ክብሮ ከሩሲያ ጋር ተከባብራ እንድትኖር ፣ የኔቶ አባል እንዳትሆን ትሁት ምክሩን ይለግሥ ነበር ። ከቶም ሩሲያን ለማሸነፍ በማይቻልበት መንገድ ዩክሬንን አጋፍጦ እንድትፈራረሥ ማድረግ፤ ለህዝብ ደንታ ቢሥነት ነው ። ሶቬቶችን አንድ ጊዜ ማታለል ችለናል ፣ ሁለተኛም እናሞኛቸዋለን ማለትም በኒኩለር መጫወት ነው ። ሩሲያ አሜሪካ በሄሮሽማ ና በናጋሳኪ እንዳደረገችው ብታደርግ ማነው ተጠያቂው ? አሜሪካንን እንደዓለም አለቃ የቆጠሩት ምእራባዊያን ናቸው ።

በዓለም የተካሄዱ ና የሚካሄዱ ጦርነቶች ሁሉ ፣ የአሜሪካ መንግሥት እጅ ያለባቸው ናቸው ። እነዚህ በአሜሪካ ቀጥተኛ ና ሥውረ ድጋፍ የሚደረግላቸው ጦርነቶች ፣ በዴሞክራሲ ሥም የሚካሄዱ ፤ በአሜሪካ ጥቅም ላይ ያነጣጠሩ  ፀረ ዴሞክራሲ ጦርነቶች ናቸው ። በአፍሪካ በተዘዋዋሪ በምትመራው ጦርነት  የአሜሪካንን የወደፊት ብዝበዛ ማፋጠን  እና ነጭ ዜጎቿን በአፍሪካ በማስፈር አፍሪካን መቀራመት ነው ።  አላማዋ ።

በዓላማዋ መሠረትም ፣ በኢትዮጵያ በመለሥ ዜናዊ አማካኝነት የጀመረችውን ኢትዮጵያን የመበታተን ልዩ ኦፕሬሽን ለማሳካት በዴሞክራሲና በሰብዓዊ መብት መሸቀጦን ገፍታበታለች ። በቢሊዮን ዶላር በእንግሊዝ ፣ በአሜሪካ እና በሌሎች የአውሮፓ አገራት ያሥቀመጡትን ዘራፊ የቀድሞ ባለሥልጣናትን  በማሥተባበር ፤ ተመልሰው በኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ ላይ እንዲፈናጠጡ በማድረግም ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር ለማድረግም በታላቅ ሴራ ላይ ተጠምዳለቾ ። ይህ ሴራዋ  የማይሳካ ከሆነ ግን የራሷን አሻጉሊት መንግሥት በኢትዮጵያ አሥቀምጣ በእጅ አዙር አገሪቱን በመቆጣጠር እንዳሻት በምድሪቱ ሀብት ላይ ለመፈንጨት ትፈልጋለች ። HR 6600 ሌላውም ተጎዳኝ የማአቀብ ህግ ፣ ከዚህ አንፃር ነው ፣ ዛሬ የመዘዘችው  ።

ይኽ ህግ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ፣ የአሜሪካ መንግሥት ፣ ከአሜሪካ ህዝብ ተነጥሎ ብቻውን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት መሆኑን በማሥመሥከሩ ከአሜሪካ ህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል ብዬ አሥባለሁ ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ወደፈቀደው ሰዖል ለመክተት ጫፍ ላይ ሲደርስ ፣ ወደትግራይ አትግቡ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑንን አሣምረው ያውቃሉ ። በአናቱም እጅግ የሚዘገንን ግፍ በአማራክልል ህዝብ እና በአፋር ክልል ህዝብ የፈፀመው ወያኔ / ትህነግ እንደሆነ ከአሜሪካ ህዝብ የተሰወረ አይደለም ።

ከዚህ አንፃር የአሜሪካ መንግሥትን እኩይነት የአሜሪኬ ዜጎች ግምግመው  የዓለም ፖሊሥነትህ  ይበቃል እንደሚሉት አሥባለሁ   ።

የአውሮፓ ህዝብም የአሜሪካንን የእብድ ፣ እብድ ጫወታን ማሥቆሞ ይኖርበታል ። በበኩሌ ኒኩለር ከታጠቀ መንግሥት ጋር እልህ ውሥጥ መግባት የእብድ ጫወታ ነው ።

በመጨረሻም ፣ በኢትዮጵያ ላይ ሊተገብረው ያሰበው ፣ በእብድ ሴኔት የተረቀቀ ድህነትን አባባሽ  ኒኩሌር ነውና ወደ ተግባር ሳይገባ  በፊትመታገድ አለበት ።  HR6600 ማለት ፣ ሁለቱ ዜሮ ጠፍቶ አንድ 6 ቢጨመርበት 666 የሚሆን የሤጣንን ተግባር አመላካች  ነው ። ለሤጣናት የተመቻመቸ ዕድል በመፍጠርም ከዚህ በፊት ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የእርስ በእርስ ጦርነት ማዋለድ   ነው ። ኢትዮጵያ ላይ ኒኩለር እንደመተኮስም  ይቆጠራል ።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop