ዛሬና አሁን ፤ ከመቅፅፈት ” የሦሥተኛው የአለም ጦርነት ይጀመራል ። ” እያልን እየሰጋን ነው ። ” ሦሥተኛው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ ፣ አራተኛ ብሎ ነገር የለም ። ” ከተባለ ቆየ ። ይኽ የተባለው አቶሚክ ቦንብ ፣ ከተፈለሰፈበት ጊዜ ጀምሮ ነው ። ከዛ በኋላ ደሞ የኒኩለር መሣሪያ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ተብሎ በመፈራቱ ነው ። ሥለሦሥተኛው የዓለም ጦርነት ካወራን አራተኛ ብሎ ነገር እንደሌለ እንረዳ ። የተባለው ። እናም ሦሥተኛው የዓለም ጦርነት ሁለተኛ ዕድል ለሰው ልጆች እንደማይሰጥ ተገንዘብ ።ሦሥተኘው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ ደግሞ ሰው በራሱ ጥበብ ፣ በጅልነቱ ግዝፈት መጥፋቱ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ይሆናል ።
ከዚህ እውነት አንፃር ፣ በቀድሞዋ የሶቬት ህብረት አካል ፣ በዩክሬን ሰበብ የሚጀመር ጦርነት ካለ ፣ ፍፃሜው ፣ የዋሽንግተንም ፣ የክራሚልን ና የምዕራብያኑን ጥፋት ማሥከተሉ የተረጋገጠ ነው ።
እናም ኃያላኑ ከእብሪት ሃሳባቸው ለሠከንድ ቆም ብለው እንዲያስቡ እንመክራለን ።እባካችሁ ፣ ለመዋጋት ያሰባችሁት የኒኩለር ጦር መሣሪያ ከታጠቀ ኃይል ጋራ ነው ። ኔቶ ቢሰባሰብ ፣ አሜሪካ ኒቶን ብትደግፍ ፣ ነገሩ “ ተልባ ቢጫጫ ፣ በአንድ ሙቀጫ ነው ። “ ይኽንን መገንዘብ ከልተገባ አካሄድ መራቅ ራሥን ማቀብ ያሥችላል ።
ኒቶም ሆነች አሜሪካ ለዩክሬን ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ፣ ለራሳቸው ጥቅም ብለው ነው ፤ “ ያዙኝ ። ልቀቁኝ ! በማለት ለገላጋይ የሚያሥቸግሩት ። ራሻ ግን የደህንነት ሥጋት ሥላለባትና በአሜሪካኖች የተነሳ ያቃጠላትን እና ግዛቶን ወደ 15 ትንንሽ ግዛት ትልቅየዳረገውን ትልቅ ጠባሳ በማየት ሁሌም መቆጨቶ ተገቢ ነው ። …
በሲአይ ኤ ተንኮል የቀድሞዋ ሶቬት ህብረትከ 1988 እኤአ ለሦሥት ተከታታይ ዓመታት ሥትገዘገዝ ሠንብታ ፣ ከ ዴሰምበር 31/ 1991 ጀምሮ 15 ቦታ መሸንሸኖንም ሞስኮ አትዘነጋም ። የእኛም የሶሻሊዝም ሥርዓት ከሶቬት ህብረት መፍረስ ጋር በ1983 እንዳልነበረ መሆኑን አሥታውስ ። ደጋፊና ተከላካዩ የነበረችው አገር በመፈራረሶ ደርግና የሶሻሊዝም ሥርዓቱ እንደ ኩይሳ በቀላሉ መፈረካከሱንም ተረዳ ።
ታላቋ ሩሲያንም ሆነ ፣ አገራችንን በምሥጢራዊ ሤራ ያፈራረሰው ሲአይ ኤ ከኬጂቪ በቴክኖሎጂ ና በዘዴ በልጦ ነው ። እርግጥ የነ ጎርባቾቭና የነየልሲን የዋህነትም ሲአይኤን አግዞታል ። በዛ ላይ በመንግሥት ውሥጥ የነበረው ሙሥና ህዝቡን ከኢኮኖሚ አንፃር ጎድቶት ነበር ።
ዛሬ ግን ይኼ ሤራ በራሻ ላይ ሊተገበር አይችልም ። ራሻ በህዝብ እጅግ በጣም ቅቡልነት ያለው መንግሥት ነው ፤ ዛሬ ያላት ። እናም ሲአይኤ በህዝብ ብሶት ሊጠቀም አይችልም ። ደሞም ኬጂቢ ና ሲአይ ኤ በአቻ ቴክኖሎጂ ሥለሚጠቀሙ የሲአይኤን የሴራ መንገድ ኬጂቪ ደቂቃ ሳይሞላ ሥለሚያውቀው እንደ ቀድሞ መበለጥ አይኖርምና በዩክሬን የኔቶም ሆነ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ዋጋ ስለሚያሥከፍል ፣ ኔቶም ሆነ አሜሪካኖች ለአለም ሰላም ሲሉ ከዩክሬን ቢወጡ መልካም ነው ። አሜሪካኖች ከሩሲያኖች የበለጠ ለዩክሬኖች ዘመድ አይደሉም ና ይህ የእልህ መንገድ ለአሜሪካ ና ለአውሮፓ ህዝብ እንደማይጠቅም አውቀው ከዩክሬን ቢወጡ ይመረጣል ። ሩሲያም ሆነች ዩክሬን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ። የሁለቱም ቋንቋ ሩሲያውኛ ነው ። ባህላቸውም ተመሳሳይ ነው ።
ለአንተ ለወገኔ ለአገሬ ልጅ ደሞ የምልህ አለኝ ።ወዳጄ ሆይ ! ሲአይኤም ሆነ ኬጂቢ ዛሬ የሚጠቀሙት ዘመናዊውን ቴክኖሎጂ በመሆኑ ሤራቸውን እንዲህ በቀላሉ አትደርስበትም ። ኬጂቢ የሲአይኤን ሴራ እግር በእግር ተከታትሎ የሚደርስበት በቴክኖሎጂው ረቂቅነት ነው ። አቻ ቴክኖሎጂ አለዋ ። አውሮፓም ሆነ አሜሪካ ፣ ዩክሬን በከርሰ ምድሮ ባላት ሀብት ጎምጅተው ነው ይኽንን የ43 ሚሊዮን ህዝብ አገር አለንልህ የሚሉት ።
ዩክሬን በመአድን የበለፀገች አገር ናት ። የዲንጋይ ከሰል ክምችቶ እጅግ ግዙፍ ነው ። የብረት ክምችቶሞ የዛን ያህል ኘው ። በነዳጅ ሀብቷም ትታወቃለች ። የሚነራል ሀብትም አላት ። ሰልፈር በብዛት የሚመረተው ከዩክሬን ነው ። የቀረውን ዊኪፒዲያን ጠይቀህ ተረዳ ።
የእኛ አገርንም ብጥብጥ ና የነሱን ጣልቃ ገብነት ከዚህ አንፃር ተረዳው ።እኛ ገና አዳጊ አገር በመሆናችንም የነሱን ድጋፍ እንደምንሻ ተገንዘብ ። ። ደሞም ሩሲያም ሆነች አሜሪካ ፤ ሁለቱም ከዓለም የደበቁት የረቀቀ የመረጃ መሰብሰቢያ የቴክኖሎጂ መሣሪያ ሊኖራቸው እንደሚችል ተረዳ ። “እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ ” ነው ። ነገሩ ። በዓለም ምን እየተከናወነ እንዳለ ፣ ሲአይኤም ፣ ኬጂቢም ፣ ሞሳድም በሰከንድ ውሥጥ ያውቃሉ ።
ወደ ሰማይ ቀና ብለህ ተመልከት ። ምንም አይታይኽም ? አዎ አይታይኽም ። እኔም የሚታየኝ ነገር የለም ። ሣተላይቶቹ እኮ በጨረቃ ሙሁዋር ውሥጥ ነው የሚሽከረከሩት ። እንዴት ልታያቸው ትችላለህ ። ነገሩ ያለው በምድር መቀበያ መሣሪያው ውሥጥ ነው ። እሱን ደሞ ለአንተ አይሰጡኽም ። የፔንታጎን ፣ የክሪሚሊን ፣ የቴልአቪቭ ጉዳይ ነው ። እናም የዙሆኖቹ መጣላት አንተን ሣሩን እንደሚጎዳህ ፣ በመገንዘብ ይኽንን የጥጋበኞች ጦርነት አውግዝ ። እውቀቱ ፣ ቴክኖሎጂው ና ብልሃቱ አለን ፤ በማለት እጅግ ወደ ሰማይ ሥትንጠራሩ የእግዘብሔርን አይን እንዳትወጉ ተጠንቀቁ ግን በላቸው ።
……