በሀገሬ ከሲአይኤ ድብቅ ና ህቡ ሴራ የሚሥተካከል ሴራ ድንገት እየተከሰተ ለህልውናችን እጅግ አሥጊ እየሆነ መጥቷል ። የሰሞኑ ከወቅታዊው የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ የፈነገጠ ድርጊት ሁሉ ፣ ይኽንኑ ሃቅ ያደምቁልናል ። የነጃሥ መፈታትት ፤ የፊልድ ማርሻሉ ሽልማትና የጀብዱ ሰሪዎች ሽልማት ፣ የመሥቀል አደባባይ ሥያሜን በመነካካት ኃይማኖታዊ ጠብ ለማሥነሳት መሞከር ፤ በግባር ያለው ፋኖ ሊሸለም ሲገባው ፣ ልቡን ለማሻከር ፣ ታቅዶ ታሥቦበት የተሰነዘረ ድፍን ያለ የማፍረሥና ትጥቅ የማሥፈታት ሃሳብ ፤ ሰሞነኛ ሴራዎች እንደነበሩ ይታወቃል ። …
ጥቂት የማይባሉ የፖለቲካ ና የኢኮኖሚ ጉዳይ ሤራዎችም ሲአዬኤ ከሚያበጃጃቸው ከአሜሪካ ሆሊውድ ፊልሞች የተኮረጁ ይመሥላሉ ። ” ልብ ሠቃይ ፤ (suspense ) በድርጊት የተሞላ ( Action )፤ አሥፈሪ ወይም ዘግናኝ ፣ ( Horror ) በሰው የሚሰሩ አሠቃቂ ፊልሞችን እና ብዙዎቹን የአኒሜሽን ፊልሞች ጨምሮ በተግባር በአፍሪካ ሲደገሙ ታያላችሁ ። በቤትናም ፣ በሱማሌ ፣ በግብፅ፣ በዩጋንዳ ፣ በደቡብ አፍሪካ ፤ በሊቢያ፤ በላይቤሪያ ፤ በደቡብ ሱዳን ፤ በሊባኖስ ፣ በፍሊሥጠም ፤ በኢራን ፤ በኢራቅ ፤ በአፍጋኒስታን ፤ በሶሪያ ፤ ወዘተ የአሜሪካኑ ሲአይኤ የፈፀመውን ገድል ና የወያኔ ዘራፊ ሠራዊት እየፈፀመ ያለውን እኩይ ድርጊት ሥታነፃፅሩ ፣ ያያችሁት የአሜሪካ አክሺን _ ሰስፔንስ ና ሆረር ፊልም ድቅን ይልባችኋል ። ( ትሪሲያ ጃንኪንሥም ቆየት ባለ ጥናታዊ ፅሑፏ ይህንኑ እውነት አረጋግጣለች ። Tricia Jenkins, The CIA in Hollywood: How the Agency Shapes Film and Television, Austin: University of Texas Press, 2012, 167 pages .)
በነገራችን ላይ ምንጫቸው ከአሜሪካ የሆነ አያሌ ዘግናኝ ና እጅግ አውሪያዊ አጫጭር ትዕይንቶችንም በኢንተርኔት አማካኝነት ማየት ይቻላል ። ሰብዓዊነት የተላበሰ ና የሞራል ልዕልና ያለው ሰው ግን እንደዛ ያለ ሴቶችና ወንዶች የሚሰቃዩበትን ፊልም ፈፅሞ ለማየት ህሊናው አይፈቅድለትም ። ገና ያንን የመረጃ ጣቢያ እንደከፈተ ሊጮኽ ይችላል ። ሆኖም የሚያይ ግለሰብ እንደማይጠፋም እወቁ ። ( ማነህ አንተ ? “ በቴንሺን ቦክሥ “ ውሥጥ ጥግህን ይዘህ ይህንን አሥፈሪ ድርጊት በፅሞና ሥታይ የነበርከው ? . . . )
ዛሬ የተገነዘብኩት ፣ “ እብዱ ኢሌ “ የማሰቃያ መንገዶችን ከዚህ ደረ ገፅ ኮርጆ እንደሆነ ተገንዝቤለሁ ። በሱማሊያ እሥርቤት የማሰቃያ መንገዶቹን ( Torture way ) ከግብረ አበሮቹ ፣ ወያኔዎች ጋር የተገበረው ከዚሁ ድረ ገፅ ኮርጆ ነው ለካ !
ትላንት ና ዛሬም ፤ በኢራቅ ፣ በሦርያ ፣ በየመን ፣ በሊቢያ ፣ በአፍጋኒሥታን ላይ አያሌ ተመሳሳይ ድርጊት የተፈፀመው ከሲአይኤ የማሰቃያ ዘዴ ተኮርጆ ነው ። የፀረ ቴሬሪሥት ቡድን እንቅሥቃሴን የሚተርከው ቲዌንቲ ፎር ሀወር ፊልምም በዋናው የሲአይ ኤ ቁንጮ በጃክ ፖዎር አማካኝነት የታየው የማሰቃያ ዘዴ ፣ በጎንተናሞ የተተገበረ ፣ ዛሬም በሥውር በሌላው ዓለም የሚፈፀም መሆኑንን ተረዳ ።
ወያኔም የዘርፎ በል ፣ ህሊና ቢሥ ሠራዊትን ፣ በመንጋነት ፈጥሮ ና ዘግናኝ የሆነ ድርጊት በመፈፀም ህዝብን የሚያሸብረው ከሆሊ ውድ ሆረር ፊልም ዘግናኝ ማሰቃያ ድርጊትን በቀጥታ ወስዶ ነው ። በተለይም የትግራይን ክልል ህዝብ በቁጥር ሦሥት እጥፍ የሚበልጠውን የአማራ ክልል ህዝብን ለማሥፈራራት ፣ ጭራቅ እንጂ ፣ እንደ እሱ ሥጋ ደምና እና አጥንት ያለው ሰው እየተዋጋው እንዳልሆነ ለማሳመን ወያኔ ፣ የሆረር ፊልምን በገሃዱ ዓለም ተግብሮታል ። የኽ ፣ በጭካኔ የተሞላ እጅግ የከፋ እና የከረፋ አሥፈሪ ድርጊቱንም ፣ ሰውን በህይወቱ እያለ ሰውን ቆዳውን በመግፍፍ አሳይቷል ። በመሆኑም የወያኔ መንጋ ሠራዊት ፣ በቃላት የማይገለፅ ፣ ህሊና ቢሥ ፣ ቦዶ ጭንቅላት ይዞ የሚጓዝ ፣ ከእንሥሣት በታች የሆነ ፣ ለሆድ ብቻ አሳቢ ሆኗል ። የሚመራው አካልም ነጭ ጅብ ሆኖበታል ። ለሠላም ፣ ለፍቅር ፣ ሰው ባለው አጭር ዕድሜ በሥቃይ እንዲኖር የሚፈልግ ከመሆኑም በላይ የትግራይ ጭቁን ህዝብን በሆዱ የሚገዛ አረመኔ ነው ። ዘላዓለም ዓለሙን ከችጋር ና ከችግር እንዳይወጣ በፈረንጅ ሥንዴ እየገዛው የዋህ ና ያልተማረውን ሥለ አለም ፖለቲካ ምንም እውቀት የሌለውን ፣ ህዝብ ከወንድም ና እህቱ ጋር ደም አቃብቶታል ።
በነገራችን ላይ ፣ በዚህ መራራ ና በግፍ የተሞላ ጦርነት የአማራ ና የአፋር ክልል ዜጎች ክፉኛ ተጎድተዋል ። ደግምም በዚህ ህሊና ቢሥ ነፍሰ ገዳይ የትግራይ ወራሪ ቡድን ጥቃት ና ውድመት እንዳይደርስበት በክልል መንግሥት ደረጃ ፣ በልዩ ኃይል ታቅፎ በሚገባ ሠልጥኖ ፣ የአማራ ፋኖ እና የአፋር ወጣት ራሱን ለመከላከል 24 ሰዓት ዝግጁ መሆነ አለበት ።” የመሐል አገር ሰው በሴትና በሥጋ ይታለላ ። ያለው ማነው ? “ ኦሮማይ !
የትግራይ ጭቁን ህዝብ በጨካኙ ነጭ ጅብ ( በደብረፅዮን እና ሰው አራጅ ጓዶቹ ) ታግቶ ፣ የጥይት ራት እየሆነ ነው ። ቀን በማይሰጠው ሆዱ መገዛት ፣ ወይም በርሃብ መሞት ምርጫው ሆኗል ። ሰብዓዊ ክብሩ ፣ ቢላ ይዞ በሚያሥፈራራው በጨካኙ የደብረ ፅዮን ገዳይ ቡድን ተገፏል ። ሳይወድ በግዱ ፣ ከአገራባች ወንድምና እህቱ ጋር ደም አቃብቶታል ። በርሃቡ ሰበብ ፣ ሆዱን እያየ ወደገደል እንዲጓዝ በሐሰተኛ ትርክት እየተደረገ ነው ። ወያኔ / ትህነግ የሆሊ ውድን ዘግናኝ የሆረር ፊልም ድርጊት በወጉ በመኮረጅ ፣ ይኽንን ቅን ህዝብ በሆዱ ገዝቶ ፣ ሳይወድ ሰውነቱን አሥረሥቶ ለሆዱ ና ለሆዱ ብቻ እንዲያሥብ በማደረግ በያዘው ቢላዋ እያሥፈራራ ባርያው አድርጎታል ።
የቢላውን ሥለት እያየ ፣ አንገቱ ላይ እንዳያርፍ እየፈራ ፣ ህዝብ ፀጥ ለጥ ብሎ የሤጣን ድርጊቱን የሚፈፅመው ፤ ደብረፅዮን ፣ በጭካኔው ከታወቀው ከአዶልፍ ሂትለር ፣ መቶ እጅ የከፋ መሆኑንን በመገንዘቡ ነው ። የተጨቆነው ፤ በአፈሙዝ ሥር ያለው ፤ የትግራይ ህዝብ ፤ ነፃ የሚያወጣው ጀግና ኢትዮጵያዊ ይፈልጋል ። እናም እንዲህ ይላል …
” እነ ‘ ጃሥን ‘ የሚፈታ ኢትዮጵያዊ መንግሥትን አናወድሥም ። ራሳችሁ ፣ በፍርሃት ቆፈን ተይዛችውና ለእናት አገራችሁ ፣ በጀግንነት ለመሞት ባለመፈለጋችሁ ፣ ለዚህ ድብቅ ፍርሃታችሁ ፣ የካድሬ ትንተና በመሥጠት ፣ባላለቀ ጦርነት በድል አድራጊነት በመሥከር ያለ ወቅቱ ከምትገባበዙ ና ጀግናውን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋለ ወኔውን ከምታቀዘቅዙት ፣ በታላቅ ሴራ እጃችን አልታሰረም ካላችሁ ፣ ወኔው ፈፅሞ ከመብረዱ ና እናንተም ውድቀታቸው ከመቃረቡ በፊት ፣ እሥቲ ወደ ትግራይ ግቡና እያንዳንዱ የደብረፅዮንን ልዩ አራጅ ሽፍታ ፣ ለቃቅማችሁ ተገቢውን ቅጣት ሥጡት !!! ያን ጊዜ እኛም ፣ በየቤቱ የተወሸቀውን የልጆቻችንን ለከንቱ ዓላማ አሥጨረሻ አጋልጠን እንሰጣችኋለን ።
አይ አንዋጋም ።በውሥጣችን የመሸጉትንም ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ አናቀርብም ብላችሁ ፣ ከደብረፅዮን ቡድን ጋር ውሥጥ ፣ለውሥጥ የምታደርጉት እርቅ ከቀጠላችሁ የእኛም ጠላቶች መሆናችሁን እወቁት ። እኛ የምንፈልገው ከጠመንጃ አፈሙዝ ነፃ መውጣት ነው ። እኛ ከጠመንጃ አፈሙዝ ነፃ ካልወጣን በሥተቀር በመላው ኢትዮጵያ የጠመንጃ አፈሙዝ አገዛዝ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለን እናምናለን ።እኛ የምንፈልገው ፍትህ እና እኩልነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ነው ። አማራ ወይም ኦሮሞ አልያም ትግሬ ትልቅ ሆኖ ሌላው ዜጋ ትንሽ የሚሆንባትን አልያም በአገሩ እንደ ሁለተኛ ና ሦሥተኛ ዜጋ የሚቆጠርባትን የዘውግ ሥርዓት የነገሰባት ኢትዮጵያን ዳግም በኦሮሙማ አማካኝነት ሲደገም ማየት አንፈልግም ። እኛ የምንፈልገው እንደ አሜሪካ ፣ ቻይና ፣ ሩሲያ ፣ አሜሪካ፣ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ኪኒያ ፣ ጋና ፣ ደቡብብ አፍሪካ ፣ እሥራኤል ፣ ስፔን ፣ ቱርክ ወዘተ ። የሠለጠነ የዜግነት ክብር ያለበት መንግሥት ነው ። ለሥጋ ምቾቱ ፤ ለሁሌም ብፊ ምግቡ ፤ ለቮድካ ና ለውሥኪው ፤ ወዘተ ። ሲል የነገድ ፣የዘውግ ና የወንዝ ፖለቲካን እንደዘመናዊነት ሊሰብከን የሚፈለግ ድንዙዝ ካድሬ በነጋ በጠባ ቁጥር በለከት አልባነት በምላሱ ሆዳችንን እየነፋ ፣ ኢትዮጵያን … እንዲያሥተዳደር አንሻም ። … የነደብረፅዮን ቡቹሎች በየሣተላይቱ በውሸታቸው የሚያደነቁሩን ይበቃናል ። “