ሆኖም በአድርባይነት እና ሴራ ይሁን ሌላ ለጊዜዉ ባልታወቀ ምክነያት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጦር ከትግራይ መዉጣት እንደ ወርቃም አጋጣሚ በመዉሰድ የሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ አስተዳደር ( ዓማራ ክልል) በማዳከም ኢትዮጵያን ለማክሰም አጋጣሚዉን ለመጠቀም ትህነግ ፣መሰል እና ተባባሪ ጠላቶች ጊዜዉ አሁን ነዉ ብለዉ የጥፋት ዕሾህ በመዝራት ላይ ናቸዉ፡፡
ሆኖም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ኢትዮጵያዉያንን (በተለይም-ዓማራ ) ማሳደድ መነሻ እና መድረሻ በማድረግ በዚህ ሳምንት ያወጁት የጥፋት ዘመቻ “አጥፍቶ ጠፊ ” በኢትዮጵያ እና ህዝቦች ላይ ወረራ በማድረግ ላደረሱት ጥፋት ኃላፊነት ለመዉሰድ ፍላጎት የሌለዉ አካል መከላከል ሲደረግ ዞትር ከአፋቸዉ በጠላትነት የሚፈርጁት የዓማራ ህዝብ (የፀጥታ ኃይል ) እና ኤርትራን(የኤርትራን ጦር ኃይል ) ተስፋፊ ማለት ከአሁን በኋላ የሚያዋጣ አለመሆኑን ዛሬ ራሳቸዉ አጥፍቶ ጠፊዎች እና የዕነርሱ አባሪ ተባባሪ እንዲሁም አፈቀላጤ (አሜሪካ) ምን እንደምትል እንጠብቃለን ፡፡
በቅርብ ቀናት ዉስጥ ዕዉነተኛ የዉስጥ አስተዳደር ተጨባጭ ለዉጥ በማስመዝገብ በኢትዮጵያ ህዝባዊነት ግንባር ቀደም ተጠቃሹ የሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር መስጠፌ ሁላችንም አንድ አለን እንተሳሰብ ያልተወራረሰ ሂሳብ የዓማራ እና ትግራይ ብቻ ሳይሆን የመላዉ ኢትዮጵያ ነዉ እና የዕኛን (የሶማሊያን) ተረኝነት ንገሩን አትደልሉን ያሉት የዓማራ ብሎ ነገር ዳር ዳር ነዉ ነገሩ የእኛ (የኢትዮጵያ ) ጉዳይ በመሆኑ የዓማራ ክልል የመላ ኢትዮጵያን “ለህልዉና እና ሉዓላዊነት” በአንድነት ዘብ ዕንቁም የሚለዉን ጥሪ ከማቅረቡ በፊት በፈቃድኝነት ሂሳብ ለማወራረስ ት.ህ.ነ.ግ ባለህበት እኛ የገቢ እና ወጭ ሂሳብ ማስረጃ ይዘን እየመጠን ነዉ ያሉ ዕዉነተኛ ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ፡፡
ለሶማሊያ እና አፋር ህዝብ እና መስተዳደር ኢትዮጵያዊነት ከማንም በላይ ዓለም እና ታሪክ ስለሚያዉቁት ትርፉ ከንቱ ድካም ይሆናል ፡፡
ሆኖም በእነዘህ እና ሌሎች ኢትዮጵያዉያን በአገር ልዑላዊነት እና ህዝብ ህልዉና ለመከላከል እና ማስቀጠል በሚደረገዉ ሁለንተናዊ ዘመቻ ተሳትፎ መቀላቀል ለዓማራ እና የኤርትራ ፀጥታ ኃይሎች ዕፎይታ የሚፈጥር ከፍተኛ የስብከት (ፕሮፖጋንዳ) ሠለባ ከመሆን የሚታደግ እና የት.ህ.ነ.ግ የጡት አባት -አሜሪካ- አርትራ እና ዓማራ ገቡ ወጡ ከሚል ነጋ መሸ “የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ ” ወደ ኢትዮጵያ ሲዞሩ እናያለን ምን ይሉን ይሁን “ኢትዮጵያ ትግራይን ወይስ ኢትዮጵያን ወረረች” ይሉን ይሆን ? ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይኖርም /አይጠባም አይደል የሚባለዉ ፡፡
እንግዲህ የአሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንዲሉ ኢትዮጵያን ማክሰም ዓማራን ማዉደም የሚያስከትለዉ መዘዝ አሁንም “ት.ህ. ነ.ግ ሲገረፍ የአሜሪካ መለፍለፍ ”ምክነያት ግን በግልፅ ለኢትዮጵያ እና ዓለም ህዝብ ሊገለፅ ይገባል፡፡
“አንድነት ኃይል ነዉ !”
ማላጂ